Amharic: New Testament

聖經新譯本

Revelation

4

1ከዚያ በኋላም አየሁ፥ እነሆም በሰማይ የተከፈተ ደጅ፥ እንደ መለከትም ሆኖ ሲናገረኝ የሰማሁት ፊተኛው ድምፅ። ወደዚህ ውጣና ከዚህ በኋላ ሊሆን የሚያስፈልገውን ነገር አሳይሃለሁ አለ።
1天上的敬拜這些事以後,我觀看,見天上有一道門開著;並且有我第一次聽見的那個好像號筒的聲音,對我說:“你上這裡來!我要把以後必定發生的事指示你。”
2ወዲያው በመንፈስ ነበርሁ፤ እነሆም፥ ዙፋን በሰማይ ቆሞአል በዙፋኑም ላይ ተቀማጭ ነበረ፤
2立刻,我在靈裡,就看見有一個寶座,設立在天上,有一位坐在寶座上。
3ተቀምጦም የነበረው በመልኩ የኢያስጲድንና የሰርዲኖን ዕንቍ ይመስል ነበር። በመልኩም መረግድን የመሰለ ቀስተ ደመና በዙፋኑ ዙሪያ ነበረ።
3那位坐著的,看來好像碧玉和紅寶石,又有彩虹圍繞著寶座,看來好像綠寶石。
4በዙፋኑ ዙሪያም ሀያ አራት ዙፋኖች ነበሩ፥ በዙፋኖቹም ላይ ነጭ ልብስ ለብሰው በራሳቸውም የወርቅ አክሊል ደፍተው ሀያ አራት ሽማግሌዎች ተቀምጠው ነበር።
4寶座的周圍有二十四個座位,上面坐著二十四位長老,身穿白衣,頭戴金冠。
5ከዙፋኑም መብረቅና ድምፅ ነጐድጓድም ይወጣል፤ በዙፋኑም ፊት ሰባት የእሳት መብራቶች ይበሩ ነበር፥ እነርሱም ሰባቱ የእግዚአብሔር መናፍስት ናቸው።
5有閃電、響聲、雷轟從寶座中發出;又有七枝火炬在寶座前點著,這就是 神的七靈。
6በዙፋኑም ፊት ብርሌ የሚመስል የብርጭቆ ባሕር ነበረ። በዙፋኑም መካከል በዙፋኑም ዙሪያ፥ በፊትና በኋላ ዓይኖች የሞሉአቸው አራት እንስሶች ነበሩ።
6寶座前有一個看來好像水晶的玻璃海。在寶座中間和寶座周圍有四個活物,前後布滿了眼睛。
7ፊተኛውም እንስሳ አንበሳን ይመስላል፥ ሁለተኛውም እንስሳ ጥጃን ይመስላል፥ ሦስተኛውም እንስሳ እንደ ሰው ፊት ነበረው፥ አራተኛውም እንስሳ የሚበረውን ንስር ይመስላል።
7第一個活物像獅子,第二個活物像牛犢,第三個活物的臉面像人,第四個活物像飛鷹。
8አራቱም እንስሶች እያንዳንዳቸው ስድስት ክንፎች አሉአቸው፥ በዙሪያቸውና በውስጣቸውም ዓይኖች ሞልተውባቸዋል፤ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የነበረውና ያለ የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ እያሉ ቀንና ሌሊት አያርፉም።
8四個活物各有六個翅膀,裡外布滿了眼睛。他們晝夜不停地說:“聖哉!聖哉!聖哉!主、全能的 神,昔在、今在、以後永在的那一位。”
9እንስሶቹም በዙፋን ላይ ለተቀመጠው ከዘላለምም እስከ ዘላለም በሕይወት ለሚኖረው ለእርሱ ክብርና ውዳሴ ምስጋናም በሰጡት ጊዜ፥
9每逢四個活物把榮耀、尊貴、感謝獻給那坐在寶座上,活到永永遠遠的那一位的時候,
10ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በዙፋን ላይ በተቀመጠው ፊት ወድቀው፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም በሕይወት ለሚኖረው እየሰገዱ። ጌታችንና አምላካችን ሆይ፥ አንተ ሁሉን ፈጥረሃልና ስለ ፈቃድህም ሆነዋልና ተፈጥረውማልና ክብር ውዳሴ ኃይልም ልትቀበል ይገባሃል እያሉ በዙፋኑ ፊት አክሊላቸውን ያኖራሉ።
10二十四位長老就俯伏在坐在寶座上那一位的面前,敬拜那活到永永遠遠的,又把他們的冠冕放在寶座前,說:
11“主、我們的 神,你是配得榮耀、尊貴、權能的,因為你創造了萬有,萬有都是因著你的旨意而存在,而被造的。”