Amharic: New Testament

聖經新譯本

Revelation

5

1በዙፋኑ ላይም በተቀመጠው በቀኝ እጁ ላይ በውስጥና በኋላ የተጻፈበት በሰባትም ማኅተም የተዘጋ መጽሐፍን አየሁ።
1得勝的羊羔配展開書卷我看見那位坐在寶座上的,右手拿著書卷,這書卷的兩面都寫滿了字,用七個印封著。
2ብርቱም መልአክ። መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ማኅተሞቹንም ይፈታ ዘንድ የሚገባው ማን ነው? ብሎ በታላቅ ድምፅ ሲያውጅ አየሁ።
2我又看見一位大力的天使,大聲宣告說:“誰配展開那書卷,拆開它的封印呢?”
3በሰማይም ቢሆን በምድርም ላይ ቢሆን ከምድርም በታች ቢሆን መጽሐፉን ሊዘረጋ ወይም ሊመለከተው ማንም አልተቻለውም።
3在天上、地上、地底下,沒有一個能夠展開書卷觀看的。
4መጽሐፉን ሊዘረጋ ወይም ሊመለከተው የሚገባው ማንም ስላልተገኘ እጅግ አለቀስሁ።
4因為沒有人配展開觀看書卷,我就大哭。
5ከሽማግሌዎቹም አንዱ። አታልቅስ፤ እነሆ፥ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ እርሱም የዳዊት ሥር መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ሰባቱንም ማኅተም ይፈታ ዘንድ ድል ነሥቶአል አለኝ።
5長老中有一位對我說:“不要哭!看哪,那從猶大支派出來的獅子,大衛的根,他已經得勝了,他能夠展開那書卷,拆開它的七印。”
6በዙፋኑና በአራቱ እንስሶች መካከልም በሽማግሌዎችም መካከል እንደ ታረደ በግ ቆሞ አየሁ፥ ሰባትም ቀንዶችና ሰባት ዓይኖች ነበሩት እነርሱም ወደ ምድር ሁሉ የተላኩ የእግዚአብሔር መናፍስት ናቸው።
6我又看見在寶座和四個活物中間,並且在眾長老中間,有羊羔站著,像是被殺過的。他有七角七眼,就是 神的七靈,奉差遣到全地去的。
7መጥቶም በዙፋን ላይ ከተቀመጠ ከዚያ ከቀኝ እጁ መጽሐፉን ወሰደው።
7羊羔走過去,從坐在寶座上那位的右手中取了書卷。
8መጽሐፉንም በወሰደ ጊዜ አራቱ እንስሶችና ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት ወደቁ፥ እያንዳንዳቸውም በገናንና የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ዕቃ ያዙ።
8他拿了書卷之後,四個活物和二十四位長老就俯伏在羊羔面前,各拿著琴和盛滿了香的金爐,這香就是眾聖徒的祈禱。
9መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፥ ታርደሃልና፥ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፥ በምድርም ላይ ይነግሣሉ እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።
9他們唱著新歌,說:“你配取書卷,配拆開封印,因為你曾被殺,曾用你的血,從各支派、各方言、各民族、各邦國,把人買了來歸給 神,
11አየሁም፥ በዙፋኑም በእንስሶቹም በሽማግሌዎቹም ዙሪያ የብዙ መላእክትን ድምፅ ሰማሁ፤ ቍጥራቸውም አእላፋት ጊዜ አእላፋትና ሺህ ጊዜ ሺህ ነበር፥
10使他們成為我們 神的國度和祭司,他們要在地上執掌王權。”
12በታላቅም ድምፅ። የታረደው በግ ኃይልና ባለ ጠግነት ጥበብም ብርታትም ክብርም ምስጋናም በረከትም ሊቀበል ይገባዋል አሉ።
11我又觀看,聽見了千千萬萬天使的聲音,他們都在寶座、活物和長老的四周,
13በሰማይና በምድርም ከምድርም በታች በባሕርም ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ። በረከትና ክብር ምስጋናም ኃይልም ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው፥ ለበጉም ይሁን ሲሉ ሰማሁ።
12大聲說:“被殺的羊羔是配得權能、豐富、智慧、力量、尊貴、榮耀、頌讚的!”
14አራቱም እንስሶች። አሜን አሉ፥ ሽማግሌዎቹም ወድቀው ሰገዱ።
13我又聽見在天上、地上、地底下和海裡的一切被造之物,以及天地間的萬有,都說:“願頌讚、尊貴、榮耀、能力,都歸給坐在寶座上的那一位和羊羔,直到永永遠遠!”
14四個活物就說:“阿們!”眾長老也俯伏敬拜。