Amharic: New Testament

聖經新譯本

Revelation

6

1በጉም ከሰባቱ ማኅተም አንዱን በፈታ ጊዜ አየሁ፥ ከአራቱም እንስሶች አንዱ ነጐድጓድ በሚመስል ድምፅ። መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ።
1羊羔揭開六個印羊羔揭開了七印的第一個印的時候,我觀看,就聽見四個活物中的一個,發出好像雷轟的聲響,說:“你來!”
2አየሁም፥ እነሆም፥ አምባላይ ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ የተቀመጠው ቀስት ነበረው፥ አክሊልም ተሰጠው፥ ድልም እየነሣ ወጣ ድል ለመንሣት።
2我觀看,見有一匹白馬;騎在馬上的拿著弓,有冠冕賜給他,他就出去,得勝並且要再得勝。
3ሁለተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ ሁለተኛው እንስሳ። መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ።
3羊羔揭開了第二個印的時候,我聽見第二個活物說:“你來!”
4ሌላም ዳማ ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ ለተቀመጠው ሰላምን ከምድር ይወስድ ዘንድ ሰዎችም እርስ በርሳቸው እንዲተራረዱ ሥልጣን ተሰጠው፥ ታላቅም ሰይፍ ተሰጠው።
4就另有一匹紅馬出來,騎在馬上的得了權柄,可以從地上奪去和平,使人互相殘殺,又有一把大刀賜給他。
5ሦስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ ሦስተኛው እንስሳ። መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ። አየሁም፥ እነሆም፥ ጕራቻ ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ የተቀመጠው በእጁ ሚዛን ያዘ።
5羊羔揭開了第三個印的時候,我聽見第三個活物說:“你來!”我觀看,見有一匹黑馬;騎在馬上的,手中拿著天平。
6በአራቱም እንስሶች መካከል ድምፅ። አንድ እርቦ ስንዴ በዲናር ሦስት እርቦ ገብስም በዲናር፥ ዘይትንና ወይንንም አትጕዳ ሲል ሰማሁ።
6我聽見在四個活物中間,仿佛有聲音說:“一公升小麥賣一個銀幣,三公升大麥賣一個銀幣,油和酒也不可糟蹋。”
7አራተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ የአራተኛው እንስሳ ድምፅ። መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ።
7羊羔揭開了第四個印的時候,我聽見第四個活物的聲音說:“你來!”
8አየሁም፥ እነሆም፥ ሐመር ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ የተቀመጠው ስሙ ሞት ነበረ። ሲኦልም ተከተለው፤ በሰይፍና በራብም በሞትም በምድርም አራዊት ይገድሉ ዘንድ ከምድር በአራተኛዋ እጅ ላይ ሥልጣን ተሰጣቸው።
8我觀看,見有一匹灰馬;騎在馬上的,名字叫作“死”。陰間也跟隨著他。他們得了權柄可以管轄地上的四分之一,又要用刀劍、饑荒、瘟疫和地上的野獸去殺人。
9አምስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ፥ ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ጠበቁት ምስክር የታረዱትን የሰዎች ነፍሳት ከመሠዊያ በታች አየሁ።
9羊羔揭開了第五個印的時候,我看見祭壇底下,有為了 神的道,並且為了自己所作的見證而被殺的人的靈魂。
10በታላቅ ድምፅም እየጮኹ። ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም? አሉ።
10他們大聲喊叫,說:“聖潔真實的主啊!你不審判住在地上的人,給我們伸流血的冤,要到幾時呢?”
11ለእያንዳንዳቸውም ነጭ ልብስ ተሰጣቸው፥ እንደ እነርሱም ደግሞ ይገደሉ ዘንድ ያላቸው የባሪያዎች ባልንጀራዎቻቸውና የወንድሞቻቸው ቍጥር እስኪፈጸም ድረስ፥ ገና ጥቂት ዘመን እንዲያርፉ ተባለላቸው።
11於是有白袍賜給他們各人,又有話吩咐他們要安息一會兒,等到那些與他們同作僕人和弟兄,像他們一樣將要被殺的人,湊滿了數目的時候。
12ስድስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ አየሁ፥ ታላቅም የምድር መናወጥ ሆነ፥ ፀሐይም እንደ ማቅ ጠጕር ጥቁር ሆነ፥ ጨረቃም በሞላው እንደ ደም ሆነ፥
12羊羔揭開了第六個印的時候,我觀看,大地震就發生了。太陽變黑,像粗糙的黑毛布;整個月亮變紅,像血一樣;
13በለስም በብርቱ ነፋስ ተናውጣ ቃርያዋን ፍሬ እንደምትጥል የሰማይ ከዋክብት ወደ ምድር ወደቁ፥
13天上的星辰墜落在地上,像無花果樹被大風搖動,落下還沒有成熟的果子。
14ሰማይም እንደ መጽሐፍ ተጠቅልሎ አለፈ፥ ተራራዎችና ደሴቶችም ሁሉ ከስፍራቸው ተወሰዱ።
14天隱退了,像書被捲起來一樣;山嶺和海島都從原處移去了。
15የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ፥
15地上的君王、大臣、軍長、財主、勇士和所有作奴隸的、自由的,都藏在山洞和巖穴裡。
16ተራራዎችንና ዓለቶችንም። በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን፤
16他們向山嶺和巖石說:“倒在我們身上吧!把我們藏起來,躲避坐在寶座上那位的面,和羊羔的震怒!
17ታላቁ የቁጣው ቀን መጥቶአልና፥ ማንስ ሊቆም ይችላል? አሉአቸው።
17因為他們震怒的大日子來到了,誰能站立得住呢?”