1ክርስቶስ ነው ብሎ በኢየሱስ የሚያምን ሁሉ ከእግዚአብሔር ተወልዶአል፥ ወላጁንም የሚወድ ሁሉ ከእርሱ የተወለደውን ደግሞ ይወዳል።
1Every one that believes that Jesus is the Christ is begotten of God; and every one that loves him that has begotten loves also him that is begotten of him.
2እግዚአብሔርን ስንወድ ትእዛዛቱንም ስናደርግ የእግዚአብሔርን ልጆች እንድንወድ በዚህ እናውቃለን።
2Hereby know we that we love the children of God, when we love God and keep his commandments.
3ትእዛዛቱን ልንጠብቅ የእግዚአብሔር ፍቅር ይህ ነውና፤ ትእዛዛቱም ከባዶች አይደሉም።
3For this is the love of God, that we keep his commandments; and his commandments are not grievous.
4ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋልና፤ ዓለምንም የሚያሸንፈው እምነታችን ነው።
4For all that has been begotten of God gets the victory over the world; and this is the victory which has gotten the victory over the world, our faith.
5ኢየሱስም የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ከሚያምን በቀር ዓለምን የሚያሸንፍ ማን ነው?
5Who is he that gets the victory over the world, but he that believes that Jesus is the Son of God?
6በውኃና በደም የመጣ ይህ ነው እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ፤ በውኃውና በደሙ እንጂ በውኃው ብቻ አይደለም።
6This is he that came by water and blood, Jesus [the] Christ; not by water only, but by water and blood. And it is the Spirit that bears witness, for the Spirit is the truth.
7መንፈስም እውነት ነውና የሚመሰክረው መንፈስ ነው።
7For they that bear witness are three:
8የሚመሰክሩት መንፈሱና ውኃው ደሙም ሦስት ናቸውና፤ ሦስቱም በአንድ ይስማማሉ።
8the Spirit, and the water, and the blood; and the three agree in one.
9የሰውን ምስክር ብንቀበል የእግዚአብሔር ምስክር ከእርሱ ይልቅ ይበልጣል፤ ስለ ልጁ የመሰከረው የእግዚአብሔር ምስክር ይህ ነውና።
9If we receive the witness of men, the witness of God is greater. For this is the witness of God [which] he has witnessed concerning his Son.
10በእግዚአብሔር ልጅ የሚያምን በነፍሱ ምስክር አለው፤ በእግዚአብሔር የማያምን እግዚአብሔር ስለ ልጁ የመሰከረውን ምስክር ስላላመነ ሐሰተኛ አድርጎታል።
10He that believes on the Son of God has the witness in himself; he that does not believe God has made him a liar, because he has not believed in the witness which God has witnessed concerning his Son.
11እግዚአብሔርም የዘላለምን ሕይወት እንደ ሰጠን ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ ምስክሩ ይህ ነው።
11And this is the witness, that God has given to us eternal life; and this life is in his Son.
12ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም።
12He that has the Son has life: he that has not the Son of God has not life.
13የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ታውቁ ዘንድ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ለምታምኑ ይህን ጽፌላችኋለሁ።
13These things have I written to you that ye may know that ye have eternal life who believe on the name of the Son of God.
14በእርሱ ዘንድ ያለን ድፍረት ይህ ነው፤ እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ይሰማናል።
14And this is the boldness which we have towards him, that if we ask him anything according to his will he hears us.
15የምንለምነውንም ሁሉ እንዲሰማልን ብናውቅ ከእርሱ የለመነውን ልመና እንደ ተቀበልን እናውቃለን።
15And if we know that he hears us, whatsoever we ask, we know that we have the petitions which we have asked of him.
16ማንም ወንድሙን ሞት የማይገባውን ኃጢአት ሲያደርግ ቢያየው ይለምን፥ ሞትም የማይገባውን ኃጢአት ላደረጉት ሕይወት ይሰጥለታል። ሞት የሚገባው ኃጢአት አለ፤ ስለዚያ እንዲጠይቅ አልልም።
16If any one see his brother sinning a sin not unto death, he shall ask, and he shall give him life, for those that do not sin unto death. There is a sin to death: I do not say of that that he should make a request.
17ዓመፃ ሁሉ ኃጢአት ነው፥ ሞትም የማይገባው ኃጢአት አለ።
17Every unrighteousness is sin; and there is a sin not to death.
18ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢአትን እንዳያደርግ፥ ነገር ግን ከእግዚአብሔር የተወለደው ራሱን እንዲጠብቅ ክፉውም እንዳይነካው እናውቃለን።
18We know that every one begotten of God does not sin, but he that has been begotten of God keeps himself, and the wicked [one] does not touch him.
19ከእግዚአብሔር እንደ ሆንን ዓለምም በሞላው በክፉው እንደ ተያዘ እናውቃለን።
19We know that we are of God, and the whole world lies in the wicked [one].
20የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።
20And we know that the Son of God has come, and has given us an understanding that we should know him that [is] true; and we are in him that [is] true, in his Son Jesus Christ. He is the true God and eternal life.
21ልጆች ሆይ፥ ከጣዖታት ራሳችሁን ጠብቁ።
21Children, keep yourselves from idols.