1በእኛ ስለሚኖርና ከእኛ ጋር ለዘላለም ስለሚሆን እውነት፥ እኔ ሽማግሌው በእውነት ለምወዳቸውና እኔ ብቻ ሳልሆን እውነትን የሚያውቁ ሁሉ ደግሞ ለሚወዱአቸው ለተመረጠች እመቤትና ለልጆችዋ፤
1The elder to [the] elect lady and her children, whom *I* love in truth, and not *I* only but also all who have known the truth,
3ከእግዚአብሔር አብና ከአብ ልጅ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ምሕረት ሰላምም በእውነትና በፍቅር ከእኛ ጋር ይሆናሉ።
2for the truth's sake which abides in us and shall be with us to eternity.
4ትእዛዝን ከአብ እንደ ተቀበልን ከልጆችሽ በእውነት የሚሄዱ አንዳንዶችን ስለ አገኘኋቸው እጅግ ደስ ብሎኛል።
3Grace shall be with you, mercy, peace from God [the] Father, and from [the] Lord Jesus Christ, the Son of the Father, in truth and love.
5አሁንም፥ እመቤት ሆይ፥ እርስ በርሳችን እንድንዋደድ እለምንሻለሁ፤ ይህች ከመጀመሪያ በእኛ ዘንድ የነበረች ትእዛዝ ናት እንጂ አዲስ ትእዛዝን እንደምጽፍልሽ አይደለም።
4I rejoiced greatly that I have found of thy children walking in truth, as we have received commandment from the Father.
6እንደ ትእዛዛቱም እንሄድ ዘንድ ይህ ፍቅር ነው፤ ከመጀመሪያ እንደ ሰማችሁ፥ በእርስዋ ትሄዱ ዘንድ ትእዛዙ ይህች ናት።
5And now I beseech thee, lady, not as writing to thee a new commandment, but that which we have had from [the] beginning, that we should love one another.
7ብዙ አሳቾች ወደ ዓለም ገብተዋልና እነርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የማያምኑ ናቸው፤ ይህ አሳቹና የክርስቶስ ተቃዋሚው ነው።
6And this is love, that we should walk according to his commandments. This is the commandment, according as ye have heard from the beginning, that ye might walk in it.
8ሙሉ ደመወዝን እንድትቀበሉ እንጂ የሠራችሁትን እንዳታጠፉ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።
7For many deceivers have gone out into the world, they who do not confess Jesus Christ coming in flesh -- this is the deceiver and the antichrist.
9ለሚወጣ ሁሉ በክርስቶስም ትምህርት ለማይኖር ሰው አምላክ የለውም፤ በክርስቶስ ትምህርት ለሚኖር አብና ወልድ አሉት።
8See to yourselves, that we may not lose what we have wrought, but may receive full wages.
10ማንም ወደ እናንተ ቢመጣ ይህንም ትምህርት ባያመጣ በቤታችሁ አትቀበሉት ሰላምም አትበሉት፤
9Whosoever goes forward and abides not in the doctrine of the Christ has not God. He that abides in the doctrine, *he* has both the Father and the Son.
11ሰላም የሚለው ሰው በክፉ ሥራው ይካፈላልና።
10If any one come to you and bring not this doctrine, do not receive him into [the] house, and greet him not;
12እንድጽፍላችሁ የምፈልገው ብዙ ነገር ሳለኝ በወረቀትና በቀለም ልጽፈው አልወድም፥ ዳሩ ግን ደስታችሁ ፍጹም እንዲሆን ወደ እናንተ ልመጣ አፍ ለአፍም ልናገራችሁ ተስፋ አደርጋለሁ።
11for he who greets him partakes in his wicked works.
13የተመረጠችው የእኅትሽ ልጆች ሰላምታ ያቀርቡልሻል።
12Having many things to write to you, I would not with paper and ink; but hope to come to you, and to speak mouth to mouth, that our joy may be full.
13The children of thine elect sister greet thee.