1ሐናንያም የተባለ አንድ ሰው ሰጲራ ከተባለች ከሚስቱ ጋር መሬት ሸጠ፥
1But a certain man, Ananias by name, with Sapphira his wife, sold a possession,
2ሚስቱም ደግሞ ስታውቅ ከሽያጩ አስቀረና እኩሌታውን አምጥቶ በሐዋርያት እግር አጠገብ አኖረው።
2and put aside for himself part of the price, [his] wife also being privy to it; and having brought a certain part, laid it at the feet of the apostles.
3ጴጥሮስም። ሐናንያ ሆይ፥ መንፈስ ቅዱስን ታታልልና ከመሬቱ ሽያጭ ታስቀር ዘንድ ሰይጣን በልብህ ስለ ምን ሞላ?
3But Peter said, Ananias, why has Satan filled thy heart that thou shouldest lie to the Holy Spirit, and put aside for thyself a part of the price of the estate?
4ሳትሸጠው የአንተ አልነበረምን? ከሸጥኸውስ በኋላ በሥልጣንህ አልነበረምን? ይህን ነገር ስለ ምን በልብህ አሰብህ? እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን አልዋሸህም አለው።
4While it remained did it not remain to *thee*? and sold, was [it not] in thine own power? Why is it that thou hast purposed this thing in thine heart? Thou hast not lied to men, but to God.
5ሐናንያም ይህን ቃል ሰምቶ ወደቀ ሞተም፤ በሰሙትም ሁሉ ላይ ታላቅ ፍርሃት ሆነ።
5And Ananias, hearing these words, fell down and expired. And great fear came upon all who heard [it].
6ጐበዞችም ተነሥተው ከፈኑት አውጥተውም ቀበሩት።
6And the young men, rising up, swathed him up for burial, and having carried him out, buried him.
7ከሦስት ሰዓት ያህል በኋላም ሚስቱ የሆነውን ሳታውቅ ገባች።
7And it came to pass about three hours afterwards, that his wife, not knowing what had happened, came in.
8ጴጥሮስም መልሶ። እስቲ ንገሪኝ፥ መሬታችሁን ይህን ለሚያህል ሸጣችሁትን? አላት። እርስዋም። አዎን፥ ይህን ለሚያህል ነው አለች።
8And Peter answered her, Tell me if ye gave the estate for so much? And she said, Yes, for so much.
9ጴጥሮስም። የጌታን መንፈስ ትፈታተኑ ዘንድ ስለ ምን ተስማማችሁ? እነሆ፥ ባልሽን የቀበሩት ሰዎች እግር በደጅ ነው አንቺንም ያወጡሻል አላት።
9And Peter said to her, Why [is it] that ye have agreed together to tempt the Spirit of [the] Lord? Lo, the feet of those that have buried thy husband [are] at the door, and they shall carry thee out.
10ያን ጊዜም በእግሩ አጠገብ ወደቀች ሞተችም፤ ጐበዞችም ሲገቡ ሞታ አገኙአት አውጥተውም በባልዋ አጠገብ ቀበሩአት።
10And she fell down immediately at his feet and expired. And when the young men came in they found her dead; and, having carried her out, they buried her by her husband.
11በቤተ ክርስቲያን ሁሉና ይህንም በሰሙ ሁሉ ላይ ታላቅ ፍርሃት ሆነ።
11And great fear came upon all the assembly, and upon all who heard these things.
12በሐዋርያትም እጅ ብዙ ምልክትና ድንቅ በሕዝብ መካከል ይደረግ ነበር፤ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው በሰሎሞን ደጅ መመላለሻ ነበሩ።
12And by the hands of the apostles were many signs and wonders done among the people; (and they were all with one accord in Solomon's porch,
13ከሌሎችም አንድ ስንኳ ሊተባበራቸው የሚደፍር አልነበረም፥
13but of the rest durst no man join them, but the people magnified them;
14ሕዝቡ ግን ያከብሩአቸው ነበር፤ የሚያምኑትም ከፊት ይልቅ ለጌታ ይጨመሩለት ነበር፤ ወንዶችና ሴቶችም ብዙ ነበሩ።
14and believers were more than ever added to the Lord, multitudes both of men and women;)
15ስለዚህም ጴጥሮስ ሲያልፍ ጥላውም ቢሆን ከእነርሱ አንዱን ይጋርድ ዘንድ ድውያንን ወደ አደባባይ አውጥተው በአልጋና በወሰካ ያኖሩአቸው ነበር።
15so that they brought out the sick into the streets and put [them] on beds and couches, that at least the shadow of Peter, when he came, might overshadow some one of them.
16ደግሞም በኢየሩሳሌም ዙሪያ ካለችው ከተማ ድውያንንና በርኵሳን መናፍስት የተሣቀዩትን እያመጡ ብዙ ሰዎች ይሰበስቡ ነበር፤ ሁሉም ይፈወሱ ነበር።
16And the multitude also of the cities round about came together to Jerusalem, bringing sick persons and persons beset by unclean spirits, who were all healed.
17ሊቀ ካህናቱ ግን የሰዱቃውያን ወገን ሆነውም ከእርሱ ጋር የነበሩት ሁሉ ተነሡ ቅንዓትም ሞላባቸው።
17And the high priest rising up, and all they that were with him, which is the sect of the Sadducees, were filled with wrath,
18በሐዋርያትም ላይ እጃቸውን ጭነው በሕዝቡ ወኅኒ ውስጥ አኖሩአቸው።
18and laid hands on the apostles and put them in the public prison.
19የጌታ መልአክ ግን በሌሊት የወኅኒውን ደጅ ከፍቶ አወጣቸውና።
19But an angel of [the] Lord during the night opened the doors of the prison, and leading them out, said,
20ሂዱና ቆማችሁ የዚህን ሕይወት ቃል ሁሉ ለሕዝብ በመቅደስ ንገሩ አላቸው።
20Go ye and stand and speak in the temple to the people all the words of this life.
21በሰሙም ጊዜ ማልደው ወደ መቅደስ ገብተው አስተማሩ። ግን ሊቀ ካህናቱና ከእርሱ ጋር የነበሩት መጥተው ሸንጎውንና የእስራኤልን ልጆች ሽማግሌዎች ሁሉ በአንድነት ጠሩ፥ ያመጡአቸውም ዘንድ ወደ ወኅኒ ላኩ።
21And when they heard it, they entered very early into the temple and taught. And when the high priest was come, and they that were with him, they called together the council and all the elderhood of the sons of Israel, and sent to the prison to have them brought.
22ሎሌዎችም መጥተው በወኅኒው አላገኙአቸውም፤ ተመልሰውም። ወኅኒው በጣም በጥንቃቄ ተዘግቶ ጠባቂዎችም በደጁ ፊት ቆመው አገኘን፥ በከፈትን ጊዜ ግን በውስጡ አንድ ስንኳ አላገኘንም አሉአቸው።
22And when the officers were come, they did not find them in the prison; and returned and reported
24የመቅደስ አዛዥና የካህናት አለቆችም ይህን ነገር በሰሙ ጊዜ። እንጃ ይህ ምን ይሆን? እያሉ ስለ እነርሱ አመነቱ።
23saying, We found the prison shut with all security, and the keepers standing at the doors; but when we had opened [them], within we found no one.
25አንድ ሰውም መጥቶ። እነሆ፥ በወኅኒ ያኖራችኋቸው ሰዎች እየቆሙ ሕዝቡንም እያስተማሩ በመቅደስ ናቸው ብሎ አወራላቸው።
24And when they heard these words, both the priest and the captain of the temple and the chief priests were in perplexity as to them, what this would come to.
26በዚያን ጊዜ አዛዡ ከሎሌዎች ጋር ሄዶ አመጣቸው፥ በኃይል ግን አይደለም፤ ሕዝቡ እንዳይወግሩአቸው ይፈሩ ነበርና።
25And some one coming reported to them, Lo, the men whom ye put in the prison are in the temple, standing and teaching the people.
27አምጥተውም በሸንጎ አቆሙአቸው።
26Then the captain, having gone with the officers, brought them, not with violence, for they feared the people, lest they should be stoned.
28ሊቀ ካህናቱም። በዚህ ስም እንዳታስተምሩ አጥብቀን አላዘዝናችሁምን? እነሆም፥ ኢየሩሳሌምን በትምህርታችሁ ሞልታችኋል፤ የዚያንም ሰው ደም በእኛ ታመጡብን ዘንድ ታስባላችሁ ብሎ ጠየቃቸው።
27And they bring them and set them in the council. And the high priest asked them,
29ጴጥሮስና ሐዋርያትም መልሰው አሉ። ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል።
28saying, We strictly enjoined you not to teach in this name: and lo, ye have filled Jerusalem with your doctrine, and purpose to bring upon us the blood of this man.
30እናንተ በእንጨት ላይ ሰቅላችሁ የገደላችሁትን ኢየሱስን የአባቶቻችን አምላክ አስነሣው፤
29But Peter answering, and the apostles, said, God must be obeyed rather than men.
31ይህን እግዚአብሔር፥ ለእስራኤል ንስሐን የኃጢአትንም ስርየት ይሰጥ ዘንድ፥ ራስም መድኃኒትም አድርጎ በቀኙ ከፍ ከፍ አደረገው።
30The God of our fathers has raised up Jesus, whom *ye* have slain, having hanged on a cross.
32እኛም ለዚህ ነገር ምስክሮች ነን፥ ደግሞም እግዚአብሔር ለሚታዘዙት የሰጠው መንፈስ ቅዱስ ምስክር ነው።
31Him has God exalted by his right hand as leader and saviour, to give repentance to Israel and remission of sins.
33እነርሱም ሲሰሙ በጣም ተቈጡ ሊገድሉአቸውም አሰቡ።
32And *we* are [his] witnesses of these things, and the Holy Spirit also, which God has given to those that obey him.
34ነገር ግን በሕዝብ ሁሉ ዘንድ የከበረ የሕግ መምህር ገማልያል የሚሉት አንድ ፈሪሳዊ በሸንጎ ተነሥቶ ሐዋርያትን ጥቂት ፈቀቅ እንዲያደርጉአቸው አዘዘ፥
33But they, when they heard [these things], were cut to the heart, and took counsel to kill them.
35እንዲህም አላቸው። የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ ስለ እነዚህ ሰዎች ምን እንደምታደርጉ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።
34But a certain [man], a Pharisee, named Gamaliel, a teacher of the law, held in honour of all the people, rose up in the council, and commanded to put the men out for a short while,
36ከዚህ ወራት አስቀድሞ ቴዎዳስ። እኔ ታላቅ ነኝ ብሎ ተነሥቶ ነበርና፥ አራት መቶ የሚያህሉ ሰዎችም ከእርሱ ጋር ተባበሩ፤ እርሱም ጠፋ የሰሙትም ሁሉ ተበተኑ እንደ ምናምንም ሆኑ።
35and said to them, Men of Israel, take heed to yourselves as regards these men what ye are going to do;
37ከዚህ በኋላ ሰዎች በተጻፉበት ዘመን የገሊላው ይሁዳ ተነሣ ብዙ ሰዎችንም አሸፍቶ አስከተለ፤ እርሱም ጠፋ የሰሙትም ሁሉ ተበታተኑ።
36for before these days Theudas rose up, alleging himself to be somebody, to whom a number of men, about four hundred, were joined; who was slain, and all, as many as obeyed him, were dispersed and came to nothing.
38አሁንም እላችኋለሁ። ከእነዚህ ሰዎች ተለዩ ተዉአቸውም፤ ይህ አሳብ ወይም ይህ ሥራ ከሰው እንደ ሆነ ይጠፋልና፤
37After him rose Judas the Galilean in the days of the census, and drew away [a number of] people after him; and *he* perished, and all, as many as obeyed him, were scattered abroad.
39ከእግዚአብሔር እንደ ሆነ ግን ታጠፉአቸው ዘንድ አይቻላችሁም፥ በእርግጥ ከእግዚአብሔር ጋር ስትጣሉ ምናልባት እንዳትገኙ።
38And now I say to you, Withdraw from these men and let them alone, for if this counsel or this work have its origin from men, it will be destroyed;
40ሰሙትም፥ ሐዋርያትንም ወደ እነርሱ ጠርተው ገረፉአቸው፥ በኢየሱስም ስም እንዳይናገሩ አዝዘው ፈቱአቸው።
39but if it be from God, ye will not be able to put them down, lest ye be found also fighters against God.
41እነርሱም ስለ ስሙ ይናቁ ዘንድ የተገባቸው ሆነው ስለ ተቈጠሩ ከሸንጎው ፊት ደስ እያላቸው ወጡ፤
40And they listened to his advice; and having called the apostles, they beat them, and enjoined them not to speak in the name of Jesus, and dismissed them.
42ዕለት ዕለትም በመቅደስና በቤታቸው ስለ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ ማስተማርንና መስበክን አይተዉም ነበር።
41They therefore went their way from [the] presence of the council, rejoicing that they were counted worthy to be dishonoured for the name.
42And every day, in the temple and in the houses, they ceased not teaching and announcing the glad tidings that Jesus [was] the Christ.