Amharic: New Testament

Darby's Translation

Acts

6

1በዚህም ወራት ደቀ መዛሙርት እየበዙ ሲሄዱ ከግሪክ አገር መጥተው የነበሩት አይሁድ በይሁዳ ኖረው በነበሩት አይሁድ አንጐራጐሩባቸው፥ በየቀኑ በተሠራው አገልግሎት መበለቶቻቸውን ችላ ይሉባቸው ነበርና።
1But in those days, the disciples multiplying in number, there arose a murmuring of the Hellenists against the Hebrews because their widows were overlooked in the daily ministration.
2አሥራ ሁለቱም ደቀ መዛሙርት ሁሉን ጠርተው እንዲህ አሉአቸው። የእግዚአብሔር ቃል ትተን ማዕድን እናገለግል ዘንድ የሚገባ ነገር አይደለም።
2And the twelve, having called the multitude of the disciples to [them], said, It is not right that we, leaving the word of God, should serve tables.
3ወንድሞች ሆይ፥ በመልካም የተመሰከረላቸውን መንፈስ ቅዱስና ጥበብም የሞላባቸውን ሰባት ሰዎች ከእናንተ ምረጡ፥ ለዚህም ጉዳይ እንሾማቸዋለን፤
3Look out therefore, brethren, from among yourselves seven men, well reported of, full of [the] [Holy] Spirit and wisdom, whom we will establish over this business:
4እኛ ግን ለጸሎትና ቃሉን ለማገልገል እንተጋለን።
4but *we* will give ourselves up to prayer and the ministry of the word.
5ይህም ቃል ሕዝብን ሁሉ ደስ አሰኛቸው፤ እምነትና መንፈስ ቅዱስም የሞላበትን ሰው እስጢፋኖስን ፊልጶስንም ጵሮኮሮስንም ኒቃሮናንም ጢሞናንም ጳርሜናንም ወደ ይሁዲነት ገብቶ የነበረውን የአንጾኪያውን ኒቆላዎስንም መረጡ።
5And the saying pleased the whole multitude: and they chose Stephen, a man full of faith and [the] Holy Spirit, and Philip, and Prochorus, and Nicanor, and Timon, and Parmenas, and Nicolas, a proselyte of Antioch,
6በሐዋርያትም ፊት አቆሙአቸው፥ ከጸለዩም በኋላ እጃቸውን ጫኑባቸው።
6whom they set before the apostles; and, having prayed, they laid their hands on them.
7የእግዚአብሔርም ቃል እየሰፋ ሄደ፥ በኢየሩሳሌምም የደቀ መዛሙርት ቍጥር እጅግ እየበዛ ሄደ፤ ከካህናትም ብዙ ሰዎች ለሃይማኖት የታዘዙ ሆኑ።
7And the word of God increased; and the number of the disciples in Jerusalem was very greatly multiplied, and a great crowd of the priests obeyed the faith.
8እስጢፋኖስም ጸጋንና ኃይልን ተሞልቶ በሕዝቡ መካከል ድንቅንና ታላቅ ምልክትን ያደርግ ነበር።
8And Stephen, full of grace and power, wrought wonders and great signs among the people.
9የነፃ ወጪዎች ከተባለችው ምኵራብም ከቀሬናና ከእስክንድርያም ሰዎች ከኪልቅያና ከእስያም ከነበሩት አንዳንዶቹ ተነሥተው እስጢፋኖስን ይከራከሩት ነበር፤
9And there arose up certain of those of the synagogue called of freedmen, and of Cyrenians, and of Alexandrians, and of those of Cilicia and Asia, disputing with Stephen.
10ይናገርበት የነበረውንም ጥበብና መንፈስ ይቃወሙ ዘንድ አልቻሉም።
10And they were not able to resist the wisdom and the Spirit with which he spoke.
11በዚያን ጊዜ። በሙሴ ላይ በእግዚአብሔርም ላይ የስድብን ነገር ሲናገር ሰምተነዋል የሚሉ ሰዎችን አስነሡ።
11Then they suborned men, saying, We have heard him speaking blasphemous words against Moses and God.
12ሕዝቡንና ሽማግሌዎችንም ጻፎችንም አናደዱ፥ ቀርበውም ያዙት ወደ ሸንጎም አመጡትና።
12And they roused the people, and the elders, and the scribes. And coming upon [him] they seized him and brought [him] to the council.
13ይህ ሰው በዚህ በተቀደሰው ስፍራ በሕግም ላይ የስድብን ነገር ለመናገር አይተውም፤
13And they set false witnesses, saying, This man does not cease speaking words against the holy place and the law;
14ይህ የናዝሬቱ ኢየሱስ ይህን ስፍራ ያፈርሰዋል ሙሴም ያስተላለፈልንን ሥርዓት ይለውጣል ሲል ሰምተነዋልና የሚሉ የሐሰት ምስክሮችን አቆሙ።
14for we have heard him saying, This Jesus the Nazaraean shall destroy this place, and change the customs which Moses taught us.
15በሸንጎም የተቀመጡት ሁሉ ትኵር ብለው ሲመለከቱት እንደ መልአክ ፊት ሆኖ ፊቱን አዩት።
15And all who sat in the council, looking fixedly on him, saw his face as [the] face of an angel.