1በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ለሕዝቡና ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ብሎ ነገራቸው።
1Then Jesus spoke to the crowds and to his disciples,
2ጻፎችና ፈሪሳውያን በሙሴ ወንበር ተቀምጠዋል።
2saying, The scribes and the Pharisees have set themselves down in Moses' seat:
3ስለዚህ ያዘዙአችሁን ሁሉ አድርጉ ጠብቁትም፥ ነገር ግን እየተናገሩ አያደርጉትምና እንደ ሥራቸው አታድርጉ።
3all things therefore, whatever they may tell you, do and keep. But do not after their works, for they say and do not,
4ከባድና አስቸጋሪ ሸክም ተብትበው በሰው ትከሻ ይጭናሉ፥ እነርሱ ግን በጣታቸው ስንኳ ሊነኩት አይወዱም።
4but bind burdens heavy and hard to bear, and lay them on the shoulders of men, but will not move them with their finger.
5ለሰውም እንዲታዩ ሥራቸውን ሁሉ ያደርጋሉ፤ ስለዚህ አሽንክታባቸውን ያሰፋሉ ዘርፉንም ያስረዝማሉ፥
5And all their works they do to be seen of men: for they make broad their phylacteries and enlarge the borders [of their garments],
6በምሳም የከበሬታ ስፍራ፥ በምኵራብም የከበሬታ ወንበር፥
6and love the chief place in feasts and the first seats in the synagogues,
7በገበያም ሰላምታና። መምህር ሆይ መምህር ሆይ ተብለው እንዲጠሩ ይወዳሉ።
7and salutations in the market-places, and to be called of men, Rabbi, Rabbi.
8እናንተ ግን። መምህር ተብላችሁ አትጠሩ፤ መምህራችሁ አንድ ስለ ሆነ እናንተም ሁላችሁ ወንድማማች ናችሁ።
8But *ye*, be not ye called Rabbi; for one is your instructor, and all *ye* are brethren.
9አባታችሁ አንዱ እርሱም የሰማዩ ነውና በምድር ላይ ማንንም። አባት ብላችሁ አትጥሩ።
9And call not [any one] your father upon the earth; for one is your Father, he who is in the heavens.
10ሊቃችሁ አንድ እርሱም ክርስቶስ ነውና። ሊቃውንት ተብላችሁ አትጠሩ።
10Neither be called instructors, for one is your instructor, the Christ.
11ከእናንተም የሚበልጠው አገልጋያችሁ ይሆናል።
11But the greatest of you shall be your servant.
12ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳል፥ ራሱንም የሚያዋርድ ሁሉ ከፍ ይላል።
12And whoever shall exalt himself shall be humbled, and whoever shall humble himself shall be exalted.
13እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት ስለምትዘጉ፥ ወዮላችሁ እናንተ አትገቡም የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።
13But woe unto you, scribes and Pharisees, hypocrites, for ye shut up the kingdom of the heavens before men; for *ye* do not enter, nor do ye suffer those that are entering to go in.
14እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ በጸሎት ርዝመት እያመካኛችሁ የመበለቶችን ቤት ስለምትበሉ፥ ወዮላችሁ፤ ስለዚህ የባሰ ፍርድ ትቀበላላችሁ።
15Woe to you, scribes and Pharisees, hypocrites, for ye compass the sea and the dry [land] to make one proselyte, and when he is become [such], ye make him twofold more [the] son of hell than yourselves.
15እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ አንድ ሰው ልታሳምኑ በባሕርና በደረቅ ስለምትዞሩ፥ በሆነም ጊዜ ከእናንተ ይልቅ ሁለት እጥፍ የባሰ የገሃነም ልጅ ስለምታደርጉት፥ ወዮላችሁ።
16Woe to you, blind guides, who say, Whosoever shall swear by the temple, it is nothing; but whosoever shall swear by the gold of the temple, he is a debtor.
16እናንተ። ማንም በቤተ መቅደስ የሚምል ምንም የለበትም፤ ማንም በቤተ መቅደስ ወርቅ የሚምል ግን በመሐላው ይያዛል የምትሉ፥ ዕውሮች መሪዎች፥ ወዮላችሁ።
17Fools and blind, for which is greater, the gold, or the temple which sanctifies the gold?
17እናንተ ደንቆሮዎችና ዕውሮች፥ ማናቸው ይበልጣል? ወርቁ ነውን? ወይስ ወርቁን የቀደሰው ቤተ መቅደስ?
18And, Whosoever shall swear by the altar, it is nothing; but whosoever shall swear by the gift that is upon it is a debtor.
18ደግማችሁም። ማንም በመሠዊያው የሚምል ምንም የለበትም፤ ማንም በላዩ ባለው መባ የሚምል ግን በመሐላው ይያዛል ትላላችሁ።
19[Fools and] blind ones, for which is greater, the gift, or the altar which sanctifies the gift?
19እናንተ ደንቆሮዎችና ዕውሮች፥ ማናቸው ይበልጣል? መባው ነውን? ወይስ መባውን የሚቀድሰው መሠዊያው?
20He therefore that swears by the altar swears by it and by all things that are upon it.
20እንግዲህ በመሠዊያው የሚምለው በእርሱና በእርሱ ላይ ባለው ሁሉ ይምላል፤
21And he that swears by the temple swears by it and by him that dwells in it.
21በቤተ መቅደስም የሚምለው በእርሱና በእርሱ በሚኖረው ይምላል፤
22And he that swears by heaven swears by the throne of God and by him that sits upon it.
22በሰማይም የሚምለው በእግዚአብሔር ዙፋንና በእርሱ ላይ በተቀመጠው ይምላል።
23Woe to you, scribes and Pharisees, hypocrites, for ye pay tithes of mint and anise and cummin, and ye have left aside the weightier matters of the law, judgment and mercy and faith: these ye ought to have done and not have left those aside.
23እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ ከአዝሙድና ከእንስላል ከከሙንም አሥራት ስለምታወጡ፥ ፍርድንና ምሕረትን ታማኝነትንም፥ በሕግ ያለውን ዋና ነገር ስለምትተዉ፥ ወዮላችሁ፤ ሌላውን ሳትተዉ ይህን ልታደርጉ ይገባችሁ ነበር።
24Blind guides, who strain out the gnat, but drink down the camel.
24እናንተ ዕውሮች መሪዎች፥ ትንኝን የምታጠሩ ግመልንም የምትውጡ።
25Woe to you, scribes and Pharisees, hypocrites, for ye make clean the outside of the cup and of the dish, but within they are full of rapine and intemperance.
25እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ በውስጡ ቅሚያና ስስት ሞልቶ ሳለ የጽዋውንና የወጭቱን ውጭ ስለምታጠሩ፥ ወዮላችሁ።
26Blind Pharisee, make clean first the inside of the cup and of the dish, that their outside also may become clean.
26አንተ ዕውር ፈሪሳዊ፥ ውጭው ደግሞ ጥሩ እንዲሆን አስቀድመህ የጽዋውንና የወጭቱን ውስጡን አጥራ።
27Woe to you, scribes and Pharisees, hypocrites, for ye are like whited sepulchres, which appear beautiful outwardly, but within are full of dead men's bones and all uncleanness.
27እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ በውጭ አምረው የሚታዩ በውስጡ ግን የሙታን አጥንት ርኩሰትም ሁሉ የተሞሉ በኖራ የተለሰኑ መቃብሮችን ስለምትመስሉ፥ ወዮላችሁ።
28Thus also *ye*, outwardly ye appear righteous to men, but within are full of hypocrisy and lawlessness.
28እንዲሁ እናንተ ደግሞ በውጭ ለሰው እንደ ጻድቃን ትታያላችሁ፥ በውስጣችሁ ግን ግብዝነትና ዓመፀኝነት ሞልቶባችኋል።
29Woe to you, scribes and Pharisees, hypocrites, for ye build the sepulchres of the prophets and adorn the tombs of the just,
29እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ የነቢያትን መቃብር ስለምትሠሩ የጻድቃንንም መቃብር ስለምታስጌጡና።
30and ye say, If we had been in the days of our fathers we would not have been partakers with them in the blood of the prophets.
30በአባቶቻችን ዘመን ኖረን በሆነስ በነቢያት ደም ባልተባበርናቸውም ነበር ስለምትሉ፥ ወዮላችሁ።
31So that ye bear witness of yourselves that ye are sons of those who slew the prophets:
31እንግዲያስ የነቢያት ገዳዮች ልጆች እንደሆናችሁ በራሳችሁ ላይ ትመሰክራላችሁ።
32and *ye*, fill ye up the measure of your fathers.
32እናንተ ደግሞ የአባቶቻችሁን መስፈሪያ ሙሉ።
33Serpents, offspring of vipers, how should ye escape the judgment of hell?
33እናንተ እባቦች፥ የእፉኝት ልጆች፥ ከገሃነም ፍርድ እንዴት ታመልጣላችሁ?
34Therefore, behold, *I* send unto you prophets, and wise men, and scribes; and [some] of them ye will kill and crucify, and [some] of them ye will scourge in your synagogues, and will persecute from city to city;
34ስለዚህ፥ እነሆ፥ ነቢያትንና ጥበበኞችን ጻፎችንም ወደ እናንተ እልካለሁ፤ ከእነርሱም ትገድላላችሁ ትሰቅሉማላችሁ፥ ከእነርሱም በምኵራባችሁ ትገርፋላችሁ ከከተማም ወደ ከተማ ታሳድዳላችሁ፤
35so that all righteous blood shed upon the earth should come upon *you*, from the blood of righteous Abel to the blood of Zacharias son of Barachias, whom ye slew between the temple and the altar.
35ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ በቤተ መቅደስና በመሠዊያው መካከል እስከ ገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ የፈሰሰው የጻድቅ ደም ሁሉ ይደርስባችሁ ዘንድ።
36Verily I say unto you, All these things shall come upon this generation.
36እውነት እላችኋለሁ፥ ይህ ሁሉ በዚህ ትውልድ ላይ ይደርሳል።
37Jerusalem, Jerusalem, [the city] that kills the prophets and stones those that are sent unto her, how often would I have gathered thy children as a hen gathers her chickens under her wings, and ye would not!
37ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ነቢያትን የምትገድል ወደ እርስዋ የተላኩትንም የምትወግር፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ! አልወደዳችሁምም።
38Behold, your house is left unto you desolate;
38እነሆ፥ ቤታችሁ የተፈታ ሆኖ ይቀርላችኋል።
39for I say unto you, Ye shall in no wise see me henceforth until ye say, Blessed [be] he that comes in the name of [the] Lord.
39እላችኋለሁና፥ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው እስክትሉ ድረስ ከእንግዲህ ወዲህ አታዩኝም።