1Vai mēs atkal sākam sevi ieteikt? Vai mums vajadzīgi ieteikšanas raksti pie jums vai no jums kā dažiem citiem?
1እንደ ገና ራሳችንን ልናመሰግን እንጀምራለንን? ወይስ እንደ ሌሎች የማመስገኛ መልእክት ወደ እናንተ ወይስ ከእናንተ ያስፈልገን ይሆንን?
2Jūs esat mūsu vēstule, kas ierakstīta mūsu sirdīs un ko pazīst un lasa visi cilvēki.
2ሰዎች ሁሉ የሚያውቁትና የሚያነቡት በልባችን የተጻፈ መልእክታችን እናንተ ናችሁ።
3Ir redzams, ka jūs esat Kristus vēstule, ko mēs esam sastādījuši un uzrakstījuši ne ar tinti, bet ar dzīvā Dieva Garu, ne uz akmens, bet uz miesīgām sirds plāksnēm.
3እናንተም በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ እንጂ በቀለም አይደለም፥ ሥጋ በሆነ በልብ ጽላት እንጂ በድንጋይ ጽላት ያልተጻፈ፥ በእኛም የተገለገለ የክርስቶስ መልእክት እንደ ሆናችሁ የተገለጠ ነው።
4Bet tāda paļāvība mums ir uz Dievu caur Kristu;
4በክርስቶስም በኩል ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ያለ እምነት አለን።
5Ne tāpēc, ka mēs būtu no sevis spējīgi domāt it kā no sevis, bet mūsu spējas ir no Dieva.
5ብቃታችን ከእግዚአብሔር ነው እንጂ፥ በገዛ እጃችን እንደሚሆን አንዳችን እንኳ ልናስብ ራሳችን የበቃን አይደለንም፤
6Viņš arī mums devis spējas kalpot Jaunajai derībai, ne burtam, bet garam, jo burts nokauj, bet gars atdzīvina.
6እርሱም ደግሞ በመንፈስ እንጂ በፊደል ለማይሆን ለአዲስ ኪዳን አገልጋዮች እንሆን ዘንድ አበቃን፤ ፊደል ይገድላልና መንፈስ ግን ሕይወትን ይሰጣል።
7Bet ja kalpošanai nāvei, kas burtiem bija iekalta akmenī, bija tāda godība, ka Izraēļa bērni nevarēja skatīties Mozus sejā viņa vaiga spožuma dēļ, kas bija pārejošs,
7ዳሩ ግን የእስራኤል ልጆች ስለዚያ ስለ ተሻረው ስለ ፊቱ ክብር የሙሴን ፊት ትኩር ብለው መመልከት እስኪሳናቸው ድረስ፥ ያ በፊደላት በድንጋዮች ላይ የተቀረጸ የሞት አገልግሎት በክብር ከሆነ፥
8Vai tad gara kalpošanai nebūs daudz lielāka godība?
8የመንፈስ አገልግሎት እንዴት ይልቅ በክብር አይሆንም?
9Ja jau pazudināšanas kalpošanai ir sava godība, tad daudz vairāk šī godība pārpilnībā ir taisnības kalpošanai.
9የኵነኔ አገልግሎት ክብር ከሆነ፥ ይልቅ የጽድቅ አገልግሎት በክብር አብዝቶ ይበልጣልና።
10Toreizējā godība vairs nav godība šīs pārlieku lielās godības dēļ.
10ያ የከበረ እንኳ እጅግ በሚበልጠው ክብር ምክንያት በዚህ ነገር ክብሩን አጥቶአልና።
11Ja jau iznīcīgajam ir sava godība, tad jo vairāk godība ir tam, kas paliek.
11ያ ይሻር የነበረው በክብር ከሆነ፥ ጸንቶ የሚኖረውማ እጅግ ይልቅ በክብር ሆኖአልና።
12Tā kā mums ir tāda cerība, mēs rīkojamies lielā paļāvībā
12እንግዲህ እንዲህ ያለ ተስፋ ካለን እጅግ ገልጠን እንናገራለን፥
13Un ne kā Mozus, kas apsedza savu vaigu, lai Izraēļa bērni neredzētu viņa sejā to, kam jāizzūd.
13የዚያንም ይሻር የነበረውን መጨረሻ ትኵር ብለው የእስራኤል ልጆች እንዳይመለከቱ፥ በፊቱ መጋረጃ እንዳደረገ እንደ ሙሴ አይደለንም።
14Bet viņu prāts ir nocietināts. Jo līdz pat šai dienai, lasot Veco Derību, tas pats aizsegs paliek neatsegts (jo ar Kristu tas izzūd).
14ነገር ግን አሳባቸው ደነዘዘ። ብሉይ ኪዳን ሲነበብ ያ መጋረጃ ሳይወሰድ እስከ ዛሬ ድረስ ይኖራልና፤ በክርስቶስ ብቻ የተሻረ ነውና።
15Bet līdz šai dienai, kad lasa Mozu, sega paliek pārklāta pār viņu sirdīm.
15ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ የሙሴ መጻሕፍት በተነበቡ ጊዜ ሁሉ ያ መጋረጃ በልባቸው ይኖራል፤
16Bet tikko kāds atgriežas pie Kunga, sega tiek noņemta.
16ወደ ጌታ ግን ዘወር ባለ ጊዜ ሁሉ መጋረጃው ይወሰዳል።
17Kungs ir Gars; bet kur Kunga Gars, tur brīvība.
17ጌታ ግን መንፈስ ነው፤ የጌታም መንፈስ ባለበት በዚያ አርነት አለ።
18Un mēs visi, kad atklātām sejām skatāmies Kunga godībā, it kā no Kunga Gara tiekam pārveidoti tanī pat attēlā no spožuma spožumā.
18እኛም ሁላችን በመጋረጃ በማይከደን ፊት የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያብለጨለጭን መንፈስ ከሚሆን ጌታ እንደሚደረግ ያን መልክ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን።