Lithuanian

Amharic: New Testament

Matthew

1

1Jėzaus Kristaus, Dovydo Sūnaus, Abraomo Sūnaus, kilmės knyga.
1የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ትውልድ መጽሐፍ።
2Abraomui gimė Izaokas, Izaokui gimė Jokūbas, Jokūbui gimė Judas ir jo broliai.
2አብርሃም ይስሐቅን ወለደ፤ ይስሐቅም ያዕቆብን ወለደ፤ ያዕቆብም ይሁዳንና ወንድሞቹን ወለደ፤
3Judui gimė Faras ir Zara iš Tamaros, Farui gimė Esromas, Esromui gimė Aramas.
3ይሁዳም ከትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደ፤ ፋሬስም ኤስሮምን ወለደ፤
4Aramui gimė Aminadabas, Aminadabui gimė Naasonas, Naasonui gimė Salmonas.
4ኤስሮምም አራምን ወለደ፤ አራምም አሚናዳብን ወለደ፤ አሚናዳብም ነአሶንን ወለደ፤ ነአሶንም ሰልሞንን ወለደ፤
5Salmonui gimė Boozas iš Rahabos, Boozui gimė Jobedas iš Rūtos, Jobedui gimė Jesė.
5ሰልሞንም ከራኬብ ቦኤዝን ወለደ፤ ቦኤዝም ከሩት ኢዮቤድን ወለደ፤ ኢዮቤድም እሴይን ወለደ፤
6Jesei gimė karalius Dovydas. Dovydui gimė Saliamonas iš Ūrijos žmonos.
6እሴይም ንጉሥ ዳዊትን ወለደ።
7Saliamonui gimė Roboamas, Roboamui gimė Abija, Abijai gimė Asa.
7ሰሎሞንም ሮብዓምን ወለደ፤ ሮብዓምም አቢያን ወለደ፤ አቢያም አሣፍን ወለደ፤
8Asai gimė Juozapatas, Juozapatui gimė Joramas, Joramui gimė Ozijas.
8አሣፍም ኢዮሣፍጥን ወለደ፤ ኢዮሣፍጥም ኢዮራምን ወለደ፤ ኢዮራምም ዖዝያንን ወለደ፤
9Ozijui gimė Joatamas, Joatamui gimė Achazas, Achazui gimė Ezekijas.
9ዖዝያንም ኢዮአታምን ወለደ፤ ኢዮአታምም አካዝን ወለደ፤
10Ezekijui gimė Manasas, Manasui gimė Amonas, Amonui gimė Jozijas.
10አካዝም ሕዝቅያስን ወለደ፤ ሕዝቅያስም ምናሴን ወለደ፤ ምናሴም አሞፅን ወለደ፤
11Jozijui gimė Jechonijas ir jo broliai ištrėmimo į Babiloniją laikais.
11አሞፅም ኢዮስያስን ወለደ፤ ኢዮስያስም በባቢሎን ምርኮ ጊዜ ኢኮንያንንና ወንድሞቹን ወለደ።
12Po ištrėmimo į Babiloniją Jechonijui gimė Salatielis, Salatieliui gimė Zorobabelis.
12ከባቢሎንም ምርኮ በኋላ ኢኮንያን ሰላትያልን ወለደ፤ ሰላትያልም ዘሩባቤልን ወለደ፤
13Zorobabeliui gimė Abijudas, Abijudui gimė Eliakimas, Eliakimui gimė Azoras.
13ዘሩባቤልም አብዩድን ወለደ፤ አብዩድም ኤልያቄምን ወለደ፤ ኤልያቄምም አዛርን ወለደ፤
14Azorui gimė Sadokas, Sadokui gimė Achimas, Achimui gimė Elijudas.
14አዛርም ሳዶቅን ወለደ፤ ሳዶቅም አኪምን ወለደ፤ አኪምም ኤልዩድን ወለደ፤
15Elijudui gimė Eleazaras, Eleazarui gimė Matanas, Matanui gimė Jokūbas.
15ኤልዩድም አልዓዛርን ወለደ፤ አልዓዛርም ማታንን ወለደ፤ ማታንም ያዕቆብን ወለደ፤
16Jokūbui gimė Juozapas­vyras Marijos, iš kurios gimė Jėzus, vadinamas Kristumi.
16ያዕቆብም ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን የወለደች የማርያምን እጮኛ ዮሴፍን ወለደ።
17Taigi nuo Abraomo iki Dovydo iš viso keturiolika kartų, nuo Dovydo iki ištrėmimo į Babiloniją keturiolika kartų ir nuo ištrėmimo į Babiloniją iki Kristaus keturiolika kartų.
17እንግዲህ ትውልድ ሁሉ ከአብርሃም እስከ ዳዊት አሥራ አራት ትውልድ፥ ከዳዊትም እስከ ባቢሎን ምርኮ አሥራ አራት ትውልድ፥ ከባቢሎንም ምርኮ እስከ ክርስቶስ አሥራ አራት ትውልድ ነው።
18Jėzaus Kristaus gimimas buvo toksai. Jo motina Marija buvo susižadėjusi su Juozapu; dar nepradėjus jiems kartu gyventi, ji tapo nėščia iš Šventosios Dvasios.
18የኢየሱስ ክርስቶስም ልደት እንዲህ ነበረ። እናቱ ማርያም ለዮሴፍ በታጨች ጊዜ ሳይገናኙ ከመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች።
19Jos vyras Juozapas, būdamas teisus ir nenorėdamas daryti jai nešlovės, sumanė tylomis ją atleisti.
19እጮኛዋ ዮሴፍም ጻድቅ ሆኖ ሊገልጣት ስላልወደደ በስውር ሊተዋት አሰበ።
20Kai jis nusprendė taip padaryti, sapne pasirodė jam Viešpaties angelas ir tarė: “Juozapai, Dovydo sūnau, nebijok parsivesti į namus savo žmonos Marijos, nes jos vaisius yra iš Šventosios Dvasios.
20እርሱ ግን ይህን ሲያስብ፥ እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ታየው፥ እንዲህም አለ። የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፥ ከእርስዋ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ።
21Ji pagimdys Sūnų, kuriam tu duosi vardą Jėzus, nes Jis išgelbės savo tautą iš jos nuodėmių”.
21ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።
22Visa tai įvyko, kad išsipildytų, kas buvo Viešpaties pasakyta per pranašą:
22በነቢይ ከጌታ ዘንድ።
23“Štai mergelė pradės įsčiose ir pagimdys Sūnų, ir Jį pavadins Emanueliu”, tai reiškia: “Dievas su mumis”.
23እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።
24Atsikėlęs Juozapas padarė taip, kaip Viešpaties angelas jam įsakė, ir parsivedė žmoną pas save.
24ዮሴፍም ከእንቅልፉ ነቅቶ የጌታ መልአክ እንዳዘዘው አደረገ፤ እጮኛውንም ወሰደ፤
25Jam negyvenus su ja kaip vyrui, ji pagimdė Sūnų, kurį jis pavadino Jėzumi.
25የበኩር ልጅዋንም እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም፤ ስሙንም ኢየሱስ አለው።