1Anomis dienomis pasirodė Jonas Krikštytojas ir pamokslavo Judėjos dykumoje,
1በዚያም ወራት መጥምቁ ዮሐንስ። መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ ብሎ በይሁዳ ምድረ በዳ እየሰበከ መጣ።
2skelbdamas: “Atgailaukite, nes prisiartino dangaus karalystė”.
3በነቢዩ በኢሳይያስ። የጌታን መንገድ አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ በዳ የሚጮህ ሰው ድምፅ የተባለለት ይህ ነውና።
3O jis buvo tas, apie kurį pranašas Izaijas yra pasakęs: “Dykumoje šaukiančiojo balsas: ‘Paruoškite Viešpačiui kelią! Ištiesinkite Jam takus!’ ”
4ራሱም ዮሐንስ የግመል ጠጉር ልብስ ነበረው፥ በወገቡም ጠፍር ይታጠቅ ነበር፤ ምግቡም አንበጣና የበረሀ ማር ነበረ።
4Pats Jonas vilkėjo kupranugario vilnų apdaru, o strėnas buvo susijuosęs odiniu diržu. Jis maitinosi skėriais ir lauko medumi.
5ያን ጊዜ ኢየሩሳሌም ይሁዳም ሁሉ በዮርዳኖስም ዙሪያ ያለ አገር ሁሉ ወደ እርሱ ይወጡ ነበር፤
5Tuomet Jeruzalė, visa Judėja ir visa Pajordanė ėjo pas jį.
6ኃጢአታቸውንም እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ ከእርሱ ይጠመቁ ነበር።
6Žmonės buvo jo krikštijami Jordano upėje ir išpažindavo savo nuodėmes.
7ዳሩ ግን ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ብዙዎች ወደ ጥምቀቱ ሲመጡ ባየ ጊዜ፥ እንዲህ አላቸው። እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ከሚመጣው ቍጣ እንድትሸሹ ማን አመለከታችሁ?
7Pamatęs daug fariziejų ir sadukiejų, einančių pas jį krikštytis, jis jiems sakė: “Angių išperos, kas perspėjo jus bėgti nuo ateinančios rūstybės?
8እንግዲህ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ፤
8Duokite vaisių, vertų atgailos!
9በልባችሁም። አብርሃም አባት አለን እንደምትሉ አይምሰላችሁ፤ እላችኋለሁና። ከነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆች ሊያስነሣለት እግዚአብሔር ይችላል።
9Ir nebandykite ramintis: ‘Mūsų tėvasAbraomas’. Aš jums sakau, kad Dievas gali pažadinti Abraomui vaikų iš šitų akmenų.
10አሁንስ ምሳር በዛፎች ሥር ተቀምጦአል፤ እንግዲህ መልካም ፍሬ የማያደርግ ዛፍ ሁሉ ይቈረጣል ወደ እሳትም ይጣላል።
10Štai kirvis jau prie medžių šaknų, ir kiekvienas medis, kuris neduoda gerų vaisių, yra nukertamas ir įmetamas į ugnį.
11እኔስ ለንስሐ በውኃ አጠምቃችኋለሁ፤ ጫማውን እሸከም ዘንድ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስ በእሳትም ያጠምቃችኋል፤
11Aš jus krikštiju vandeniu atgailai, bet Tas, kuris ateina po manęs,galingesnis už mane, aš nevertas net Jo sandalų nuauti. Jis krikštys jus Šventąja Dvasia ir ugnimi.
12መንሹም በእጁ ነው፥ አውድማውንም ፈጽሞ ያጠራል፥ ስንዴውንም በጎተራው ይከታል፥ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።
12Jo rankoje vėtyklė, ir Jis kruopščiai išvalys savo kluoną. Kviečius surinks į klėtį, o pelus sudegins neužgesinama ugnimi”.
13ያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ።
13Tuomet Jėzus iš Galilėjos atėjo prie Jordano pas Joną krikštytis.
14ዮሐንስ ግን። እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን? ብሎ ይከለክለው ነበር።
14Jonas Jį atkalbinėjo: “Aš turėčiau būti Tavo pakrikštytas, o Tu ateini pas mane!”
15ኢየሱስም መልሶ። አሁንስ ፍቀድልኝ፤ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና አለው። ያን ጊዜ ፈቀደለት።
15Bet Jėzus jam atsakė: “Šį kartą paklausyk! Taip mudviem dera įvykdyti visą teisumą”. Tada Jonas sutiko.
16ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ ወጣ፤ እነሆም፥ ሰማያት ተከፈቱ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ፤
16Pakrikštytas Jėzus tuoj išbrido iš vandens. Ir štai Jam atsivėrė dangus, ir Jis pamatė Dievo Dvasią, sklendžiančią žemyn it balandį ir nusileidžiančią ant Jo.
17እነሆም፥ ድምፅ ከሰማያት መጥቶ። በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ።
17Ir štai balsas iš dangaus prabilo: “Šitas yra mano mylimas Sūnus, kuriuo Aš gėriuosi”.