1የከበርህ ቴዎፍሎስ ሆይ፥ ከመጀመሪያው በዓይን ያዩትና የቃሉ አገልጋዮች የሆኑት እንዳስተላለፉልን፥ በኛ ዘንድ ስለ ተፈጸመው ነገር ብዙዎች ታሪክን በየተራው ለማዘጋጀት ስለ ሞከሩ፥ እኔ ደግሞ ስለ ተማርኸው ቃል እርግጡን እንድታውቅ በጥንቃቄ ሁሉን ከመጀመሪያው ተከትዬ በየተራው ልጽፍልህ መልካም ሆኖ ታየኝ።
1序言(參徒1:1)尊敬的提阿非羅先生,因為有許多人,已經把在我們中間成就了的事,
5በይሁዳ ንጉሥ በሄሮድስ ዘመን ከአብያ ክፍል የሆነ ዘካርያስ የሚባል አንድ ካህን ነበረ፤ ሚስቱም ከአሮን ልጆች ነበረች፥ ስምዋም ኤልሳቤጥ ነበረ።
2按照起初親眼看見的傳道人所傳給我們的,編著成書;
6ሁለቱም በጌታ ትእዛዝና ሕግጋት ሁሉ ያለ ነቀፋ እየሄዱ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ነበሩ።
3我已經把這些事從頭考查過,認為也應該按著次序寫給你,
7ኤልሳቤጥም መካን ነበረችና ልጅ አልነበራቸውም፤ ሁለቱም በዕድሜያቸው አርጅተው ነበር።
4讓你曉得所學到的道理,都是確實的。
8እርሱም በክፍሉ ተራ በእግዚአብሔር ፊት ሲያገለግል፥
5天使預言施洗約翰出生猶太王希律在位的日子,亞比雅班裡有一個祭司,名叫撒迦利亞,他妻子是亞倫的後代,名叫以利沙伯。
9እንደ ካህናት ሥርዓት ወደ ጌታ ቤተ መቅደስ ገብቶ ለማጠን ዕጣ ደረሰበት።
6他們在 神面前都是義人,遵行主的一切誡命規條,無可指摘,
10በዕጣንም ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ በውጭ ቆመው ይጸልዩ ነበር።
7只是沒有孩子,因為以利沙伯不生育,二人又都上了年紀。
11የጌታም መልአክ በዕጣኑ መሠዊያ ቀኝ ቆሞ ታየው።
8有一次,撒迦利亞在 神面前按著班次執行祭司的職務,
12ዘካርያስም ባየው ጊዜ ደነገጠ፥ ፍርሃትም ወደቀበት።
9照祭司的慣例抽中了籤,進入主的聖殿燒香。
13መልአኩም እንዲህ አለው። ዘካርያስ ሆይ፥ ጸሎትህ ተሰምቶልሃልና አትፍራ ሚስትህ ኤልሳቤጥም ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፥ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ።
10燒香的時候,眾人都在外面祈禱。
14ደስታና ተድላም ይሆንልሃል፥ በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል።
11有主的使者站在香壇右邊,向他顯現。
15በጌታ ፊት ታላቅ ይሆናልና፥ የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣም፤ ገናም በእናቱ ማኅፀን ሳለ መንፈስ ቅዱስ ይሞላበታል፤
12撒迦利亞一見就驚慌起來,十分害怕。
16ከእስራኤልም ልጆች ብዙዎችን ወደ ጌታ ወደ አምላካቸው ይመልሳል።
13天使說:“撒迦利亞,不要怕,因為你的祈求已蒙垂聽,你妻子以利沙伯要給你生一個兒子,你要給他起名叫約翰。
17እርሱም የተዘጋጁትን ሕዝብ ለጌታ እንዲያሰናዳ፥ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች የማይታዘዙትንም ወደ ጻድቃን ጥበብ ይመልስ ዘንድ በኤልያስ መንፈስና ኃይል በፊቱ ይሄዳል።
14你必歡喜快樂,許多人因他出生,也必喜樂。
18ዘካርያስም መልአኩን። እኔ ሽማግሌ ነኝ ምስቴም በዕድሜዋ አርጅታለችና ይህን በምን አውቃለሁ? አለው።
15他在主面前要被尊為大,淡酒濃酒都不喝,未出母腹就被聖靈充滿。
19መልአኩም መልሶ። እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፥ እንድናገርህም ይህችንም የምሥራች እንድሰብክልህ ተልኬ ነበር፤
16他要使許多以色列人轉向主他們的 神。
20እነሆም፥ በጊዜው የሚፈጸመውን ቃሌን ስላላመንህ፥ ይህ ነገር እስከሚሆን ቀን ድረስ ዲዳ ትሆናለህ መናገርም አትችልም አለው።
17他必有以利亞的靈和能力,行在主的前面,叫父親的心轉向兒女,叫悖逆的轉向義人的意念,為主安排那預備好了的人民。”
21ሕዝቡም ዘካርያስን ይጠብቁት ነበር፤ በቤተ መቅደስም ውስጥ ስለ ዘገየ ይደነቁ ነበር።
18撒迦利亞對天使說:“我怎麼能知道這事呢?我已經老了,我妻子也上了年紀。”
22በወጣም ጊዜ ሊነግራቸው አልቻለም፥ በቤተ መቅደስም ራእይ እንዳየ አስተዋሉ፤ እርሱም ይጠቅሳቸው ነበር፤ ድዳም ሆኖ ኖረ።
19天使回答:“我是站在 神面前的加百列,奉差遣向你說話,報給你這好消息。
23የማገልገሉም ወራት ሲፈጸም ወደ ቤቱ ሄደ።
20看吧!到了時候我的話必要應驗;因為你不信我的話,你必成為啞巴,直到這些事成就的那一天,才能說話。”
24ከዚህም ወራት በኋላ ሚስቱ ኤልሳቤጥ ፀነሰችና። ነቀፌታዬን ከሰው መካከል ያስወግድልኝ ዘንድ ጌታ በተመለከተበት ወራት እንዲህ አድርጎልኛል ስትል ራስዋን አምስት ወር ሰወረች።
21眾人等候撒迦利亞;因他在聖殿裡遲遲不出來,覺得奇怪。
26በስድስተኛውም ወር መልአኩ ገብርኤል ናዝሬት ወደምትባል ወደ ገሊላ ከተማ፥
22等到他出來,卻不能講話,竟成了啞巴,不斷地向他們打手式,他們就知道他在聖殿裡見了異象。
27ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ፥ የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ።
23供職的日子滿了,他就回家去。
28መልአኩም ወደ እርስዋ ገብቶ። ደስ ይበልሽ፥ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ አላት።
24過了幾天,他妻子以利沙伯懷了孕,隱藏了五個月,說:
29እርስዋም ባየችው ጊዜ ከንግግሩ በጣም ደነገጠችና። ይህ እንዴት ያለ ሰላምታ ነው? ብላ አሰበች።
25“主在眷顧的日子,這樣看待我,要把我在人間的羞恥除掉。”
30መልአኩም እንዲህ አላት። ማርያም ሆይ፥ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋ አግኝተሻልና አትፍሪ።
26天使預言耶穌降生到了第六個月,天使加百列奉 神差遣,往加利利的拿撒勒城去,
31እነሆም፥ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ።
27到了一個童貞女那裡,她已經和大衛家一個名叫約瑟的人訂了婚,童貞女的名字是馬利亞。
32እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፥ ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል፤
28天使進去,對她說:“恭喜!蒙大恩的女子,主與你同在!”
33በያዕቆብ ቤትም ላይ ለዘለላም ይነግሣል፥ ለመንግሥቱም መጨረሻ የለውም።
29她卻因這話驚慌起來,反覆思想這樣祝賀是甚麼意思。
34ማርያምም መልአኩን። ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል? አለችው።
30天使說:“馬利亞,不要怕!因你已從 神那裡蒙了恩。
35መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት። መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል።
31你將懷孕生子,要給他起名叫耶穌。
36እነሆም ዘመድሽ ኤልሳቤጥ፥ እርስዋ ደግሞ በእርጅናዋ ወንድ ልጅ ፀንሳለች፥ ለእርስዋም መካን ትባል ለነበረችው ይህ ስድስተኛ ወር ነው፤
32他將要被尊為大,稱為至高者的兒子,主 神要把他祖大衛的王位賜給他,
37ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና።
33他要作王統治雅各家,直到永遠,他的國沒有窮盡。”
38ማርያምም። እነሆኝ የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ አለች። መልአኩም ከእርስዋ ሄደ።
34馬利亞對天使說:“我還沒有出嫁,怎能有這事呢?”
39ማርያምም በዚያ ወራት ተነሥታ ወደ ተራራማው አገር ወደ ይሁዳ ከተማ ፈጥና ወጣች፥
35天使回答:“聖靈要臨到你,至高者的能力要覆庇你,因此那將要出生的聖者,必稱為 神的兒子。
40ወደ ዘካርያስም ቤት ገብታ ኤልሳቤጥን ተሳለመቻት።
36你看,你親戚以利沙伯,被稱為不生育的,在老年也懷了男胎,現在已是第六個月了,
41ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ፅንሱ በማኅፀንዋ ውስጥ ዘለለ፤ በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት፥
37因為在 神沒有一件事是不可能的。”
42በታላቅ ድምፅም ጮኻ እንዲህ አለች። አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው።
38馬利亞說:“我是主的婢女,願照你的話成就在我身上!”天使就離開她去了。
43የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?
39馬利亞往見以利沙伯後來,馬利亞就起身,急忙向山地去,來到猶大的一座城,
44እነሆ፥ የሰላምታሽ ድምጽ በጆሮዬ በመጣ ጊዜ ፅንሱ በማኅፀኔ በደስታ ዘሎአልና።
40進了撒迦利亞的家,向以利沙伯問安。
45ከጌታ፤ የተነገረላት ቃል ይፈጸማልና ያመነች ብፅዕት ናት።
41以利沙伯一聽見馬利亞的問安,腹中的胎兒就跳動,以利沙伯也被聖靈充滿,
46ማርያምም እንዲህ አለች።
42就高聲說:“你在女子中是有福的!你腹中的胎兒也是有福的!
47ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፥ መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች፤
43我主的母親竟然到我這裡來。這事怎會臨到我呢?
48የባሪያይቱን ውርደት ተመልክቶአልና። እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤
44你看,你問安的聲音一進我的耳朵,我腹中的胎兒就歡喜跳躍。
49ብርቱ የሆነ እርሱ በእኔ ታላቅ ሥራ አድርጎአልና፤ ስሙም ቅዱስ ነው።
45這相信主傳給她的話必要成就的女子是有福的。”
50ምሕረቱም ለሚፈሩት እስከ ትውልድና ትውልድ ይኖራል።
46馬利亞尊主為大(參撒上2:1~10)馬利亞說:“我心尊主為大,
51በክንዱ ኃይል አድርጎአል፤ ትዕቢተኞችን በልባቸው አሳብ በትኖአል፤
47我靈以 神我的救主為樂,
52ገዥዎችን ከዙፋናቸው አዋርዶአል፤ ትሑታንንም ከፍ አድርጎአል፤
48因為他垂顧他使女的卑微,看哪!今後萬代都要稱我為有福。
53የተራቡትን በበጎ ነገር አጥግቦአል፤ ባለ ጠጎችንም ባዶአቸውን ሰዶአቸዋል።
49全能者為我行了大事,他的名為聖;
54ለአባቶቻችን እንደ ተናገረ፥ ለአብርሃምና ለዘሩ ለዘላለም ምሕረቱ ትዝ እያለው እስራኤልን ብላቴናውን ረድቶአል።
50他的憐憫世世代代歸與敬畏他的人。
56ማርያምም ሦስት ወር የሚያህል በእርስዋ ዘንድ ተቀመጠች ወደ ቤትዋም ተመለሰች።
51他用膀臂施展大能,驅散心裡妄想的狂傲人。
57የኤልሳቤጥም የመውለጃዋ ጊዜ ደረሰ፥ ወንድ ልጅም ወለደች።
52他使有權能的失位,叫卑微的升高,
58ጎረቤቶችዋም ዘመዶችዋም ጌታ ምሕረቱን እንዳገነነላት ሰምተው ከእርስዋ ጋር ደስ አላቸው።
53讓飢餓的得飽美食,使富足的空手回去。
59በስምንተኛውም ቀን ሕፃኑን ሊገርዙት መጡ፥ በአባቱም ስም ዘካርያስ ሊሉት ወደዱ።
54他扶助了他的僕人以色列,為要記念他的憐憫,
60እናቱ ግን መልሳ። አይሆንም፥ ዮሐንስ ይባል እንጂ አለች።
55正如他向我們列祖所說的,恩待亞伯拉罕和他的後裔,直到永遠。”
61እነርሱም። ከወገንሽ ማንም በዚህ ስም የተጠራ የለም አሉአት።
56馬利亞和以利沙伯同住約有三個月,就回家去了。
62አባቱንም ማን ሊባል እንዲወድ ጠቀሱት።
57施洗約翰出生以利沙伯的產期到了,生了一個兒子。
63ብራናም ለምኖ። ስሙ ዮሐንስ ነው ብሎ ጻፈ። ሁሉም አደነቁ።
58鄰里親戚,聽見主向她大施憐憫,都和她一同歡樂。
64ያንጊዜም አፉ ተከፈተ መላሱም ተፈታ እግዚአብሔርንም እየባረከ ተናገረ።
59到了第八天,他們來給孩子行割禮,要照他父親的名字,叫他撒迦利亞。
65ለጎረቤቶቻቸውም ሁሉ ፍርሃት ሆነ፤ ይህም ሁሉ ነገር በይሁዳ በተራራማው አገር ሁሉ ተወራ፤
60但他母親說:“不可,要叫他約翰。”
66የሰሙትም ሁሉ። እንኪያ ይህ ሕፃን ምን ይሆን? እያሉ በልባቸው አኖሩት፤ የጌታ እጅ ከእርሱ ጋር ነበረችና።
61他們說:“你親族裡沒有叫這名字的。”
67አባቱ ዘካርያስም መንፈስ ቅዱስ ሞላበትና ትንቢት ተናገረ እንዲህም አለ።
62他們就向孩子的父親打手式,看他要叫他甚麼。
68የእስራኤል ጌታ አምላክ ይባረክ፥ ጐብኝቶ ለሕዝቡ ቤዛ አድርጎአልና፤
63他要了一塊寫字版,寫上說:“他的名字是約翰。”眾人都希奇。
69ከጥንት ጀምሮ በነበሩት በቅዱሳን ነቢያት አፍ እንደ ተናገረ፥ በብላቴናው በዳዊት ቤት የመዳን ቀንድን አስነስቶልናል፤
64撒迦利亞的口舌立刻開了,就出聲稱頌 神。
71ማዳኑም ከወደረኞቻችንና ከሚጠሉን ሁሉ እጅ ነው፤
65住在周圍的人都害怕,這一切事傳遍了整個猶太山地,
72እንደዚህ ለአባቶቻችን ምሕረት አደረገ፤ ለአባታችን ለአብርሃምም የማለውን መሐላውን ቅዱሱን ኪዳን አሰበ፤
66凡聽見的就把這些事放在心裡,說:“這孩子將會成為怎樣的人呢?因為主的手與他同在。”
74በእርሱም ከጠላቶቻችን እጅ ድነን በዘመናችን ሁሉ ያለ ፍርሃት በቅድስናና በጽድቅ በፊቱ እንድናገለግለው ሰጠን።
67撒迦利亞的預言他的父親撒迦利亞被聖靈充滿,預言說:
76ደግሞም አንተ ሕፃን ሆይ፥ የልዑል ነቢይ ትባላለህ፥ መንገዱን ልትጠርግ በጌታ ፊት ትሄዳለህና፤
68“主,以色列的 神,是應當稱頌的,因他眷顧自己的子民,施行救贖,
77እንደዚህም የኃጢአታቸው ስርየት የሆነውን የመዳን እውቀት ለሕዝቡ ትሰጣለህ፤
69在他僕人大衛家中,為我們興起救恩的角,
78ይህም ከላይ የመጣ ብርሃን በጐበኘበት በአምላካችን ምሕረትና ርኅራኄ ምክንያት ነው፤
70正如主自古以來藉聖先知口中所說的,
79ብርሃኑም በጨለማና በሞት ጥላ ተቀምጠው ላሉት ያበራል እግሮቻችንንም በሰላም መንገድ ያቀናል።
71救我們脫離仇敵,和恨我們的人的手;
80ሕፃኑም አደገ በመንፈስም ጠነከረ፥ ለእስራኤልም እስከ ታየበት ቀን ድረስ በምድረ በዳ ኖረ።
72向我們列祖施憐憫,記念他的聖約,
74把我們從仇敵手中救拔出來,叫我們可以坦然無懼,用聖潔公義,在他面前一生一世敬拜他。
76孩子啊,你要稱為至高者的先知,因為你要行在主的面前,預備他的路,
78因我們 神的憐憫,使清晨的陽光從高天臨到我們,
79光照那坐在黑暗中死蔭裡的人,引導我們的腳,走上平安的路。”
80這孩子漸漸長大,心靈健壯,住在曠野,直到他在以色列人中公開露面的日子。