Amharic: New Testament

聖經新譯本

Luke

20

1አንድ ቀንም ሕዝቡን በመቅደስ ሲያስተምር ወንጌልንም ሲሰብክላቸው፥ የካህናት አለቆችና ጻፎች ከሽማግሌዎች ጋር ወደ እርሱ ቀረቡና።
1質問耶穌憑甚麼權柄作事(太21:23~27;可11:27~33)有一天,耶穌在殿裡教導人,宣講福音,眾祭司長、經學家和長老上前來,
2እስኪ ንገረን፤ እነዚህን በምን ሥልጣን ታደርጋለህ ወይስ ይህን ሥልጣን የሰጠህ ማን ነው? ብለው ተናገሩት።
2對他說:“告訴我們,你憑著甚麼權柄作這些事?給你這權柄的是誰?”
3መልሶም። እኔ ደግሞ አንዲት ነገር እጠይቃችኋለሁ፥ እናንተም ንገሩኝ፤
3他回答他們:“我也要問你們一句話,你們告訴我:
4የዮሐንስ ጥምቀት ከሰማይ ነበረችን ወይስ ከሰው? አላቸው።
4約翰的洗禮是從天上來的,還是從人來的呢?”
5እርስ በርሳቸውም ሲነጋገሩ። ከሰማይ ብንል። ስለ ምን አላመናችሁበትም? ይለናል፤
5他們就彼此議論說:“如果我們說:‘是從天上來的’,他就會問:‘那你們為甚麼不相信他呢?’
6ከሰው ብንል ግን ሕዝቡ ሁሉ ይወግሩናል፤ ዮሐንስ ነቢይ እንደ ነበረ ሁሉ ያምኑ ነበርና አሉ።
6如果我們說:‘是從人來的’,眾人都會用石頭打我們,因為他們都認定約翰是先知。”
7መልሰውም። ከወዴት እንደ ሆነ አናውቅም አሉት።
7於是他們回答耶穌:“我們不知道是從哪裡來的。”
8ኢየሱስም። እኔም በምን ሥልጣን እነዚህን እንዳደርግ አልነግራችሁም አላቸው።
8耶穌說:“我也不告訴你們,我憑著甚麼權柄作這些事。”
9ይህንም ምሳሌ ለሕዝቡ ይላቸው ጀመር። አንድ ሰው የወይን አትክልት ተከለ ለገበሬዎችም አከራይቶ ለብዙ ዘመን ወደ ሌላ አገር ሄደ።
9佃戶的比喻(太21:33~46;可12:1~12)於是耶穌向眾人講了這個比喻:“有一個人栽種了一個葡萄園,租給佃戶,就遠行去了很久。
10በጊዜውም ከወይኑ አትክልት ፍሬ እንዲሰጡት አንድ ባሪያ ወደ ገበሬዎች ላከ፤ ገበሬዎቹ ግን ደበደቡት ባዶውንም ሰደዱት።
10到了時候,園主派了一個僕人到佃戶那裡,叫他們把葡萄園當納的果子交給他。佃戶卻打了他,放他空手回去。
11ጨምሮም ሌላውን ባሪያ ላከ፤ እነርሱም ያን ደግሞ ደበደቡት አዋርደውም ባዶውን ሰደዱት።
11園主又派另一個僕人去,佃戶又打了他,並且侮辱他,也叫他空手回去。
12ጨምሮም ሦስተኛውን ላከ፤ እነርሱም ይህን ደግሞ አቍሰለው አወጡት።
12於是他又派第三個去,佃戶把他打傷,趕他走了。
13የወይኑም አትክልት ጌታ። ምን ላድርግ? የምወደውን ልጄን እልካለሁ፤ ምናልባት እርሱን አይተው ያፍሩታል አለ።
13葡萄園的主人說:‘怎麼辦呢?我要派我的愛子去,也許這一個他們會尊敬的。’
14ገበሬዎቹ ግን አይተውት እርስ በርሳቸው ሲነጋገሩ። ወራሹ ይህ ነው፤ ርስቱ ለእኛ እንዲሆን ኑ እንግደለው አሉ።
14佃戶一看他,就彼此商議說:‘這是繼承產業的,讓我們殺了他,那麼,產業就成為我們的了。’
15ከወይኑም አትክልት ወደ ውጭ አውጥተው ገደሉት። እንግዲህ የወይኑ አትክልት ጌታ ምን ያደርጋቸዋል?
15於是他們把園主的愛子推出葡萄園外殺了。主人要怎樣對待他們呢?
16ይመጣል እነዚህንም ገበሬዎች ያጠፋል፥ የወይኑንም አትክልት ለሌሎች ይሰጣል። ይህንም በሰሙ ጊዜ። ይህስ አይሁን አሉ።
16他要來除掉這些佃戶,把葡萄園租給別人。”他們聽見了就說:“千萬不要有這樣的事發生!”
17እርሱ ግን ወደ እነርሱ ተመልክቶ። እንግዲህ። ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ ተብሎ የተጻፈው ይህ ምንድር ነው?
17耶穌看著他們,說:“那麼,‘建築工人所棄的石頭,成了房角的主要石頭’,這經文是甚麼意思呢?
18በዚያም ድንጋይ ላይ የሚወድቅ ሁሉ ይቀጠቀጣል፤ የሚወድቅበትን ሁሉ ግን ይፈጨዋል አለ።
18凡是跌在那石頭上的,就必摔碎;那石頭掉在誰的身上,就必把他壓得粉碎。”
19የካህናት አለቆችና ጻፎችም ይህን ምሳሌ በእነርሱ ላይ እንደ ተናገረ አውቀው በዚያች ሰዓት እጃቸውን ሊጭኑበት ፈለጉ ነገር ግን ሕዝቡን ፈሩ።
19經學家和祭司長知道這比喻是針對他們說的,當時就想動手拿他,可是又害怕群眾。
20ሲጠባበቁም ወደ ገዢ ግዛትና ሥልጣን አሳልፈው እንዲሰጡት ጻድቃን መስለው በቃሉ የሚያጠምዱትን ሸማቂዎች ሰደዱበት።
20以納稅的事問難耶穌(太22:15~22;可12:13~17)經學家和祭司長差派奸細偽裝好人去窺探耶穌,要抓著他的把柄,好把他交由總督全權裁決。
21ጠይቀውም። መምህር ሆይ፥ እውነትን እንድትናገርና እንድታስተምር ለሰው ፊትም እንዳታደላ እናውቃለን፥ በእውነት የእግዚአብሔርን መንገድ ታስተምራለህ እንጂ፤
21奸細問他:“老師,我們知道你所說所教的都對,並且不講情面,只照著真理把 神的道教導人。
22ለቄሣር ግብር ልንሰጥ ተፈቅዶአልን? ወይስ አልተፈቀደም? አሉት።
22我們納稅給凱撒可以不可以?”
23እርሱ ግን ተንኰላቸውንም ተመልክቶ። ስለ ምን ትፈትኑኛላችሁ? አንድ ዲናር አሳዩኝ፤
23耶穌看透他們的詭計,就對他們說:
24መልኩ ጽሕፈቱስ የማን ነው? አላቸው። መልሰውም። የቄሣር ነው አሉት።
24“給我一個銀幣看看,上面是誰的像,誰的名號?”他們說:“凱撒的。”
25እርሱም። እንኪያስ የቄሣርን ለቄሣር የእግዚአብሔርንም ለእግዚአብሔር አስረክቡ አላቸው።
25耶穌說:“這樣,凱撒的應當歸給凱撒, 神的應當歸給 神。”
26በሕዝቡም ፊት በቃሉ ሊያጠምዱት አልቻሉም በመልሱም እየተደነቁ ዝም አሉ።
26他們在群眾面前,不能抓住耶穌的把柄,又希奇他的回答,就沉默下來。
27ትንሣኤ ሙታንንም የሚክዱ ከሰዱቃውያን አንዳንዶቹ ቀርበው ጠየቁት፥
27人復活後不娶不嫁(太22:23~33;可12:18~27)撒都該人向來否認有復活的事,他們當中有幾個人來問耶穌:
28እንዲህ ሲሉ። መምህር ሆይ፥ ሙሴ። ሚስት ያለችው የአንድ ሰው ወንድም ልጅ ሳይወልድ ቢሞት፥ ወንድሙ ሚስቱን አግብቶ ለወንድሙ ዘር ይተካ ብሎ ጻፈልን።
28“老師,摩西曾寫給我們說:‘如果一個人娶了妻子,還沒有兒女就死了,他弟弟就應當娶他的妻子,為哥哥立後。’
29እንግዲያስ ሰባት ወንድማማች ነበሩ፤ የፊተኛውም ሚስት አግብቶ ልጅ ሳይወልድ ሞተ፤
29從前有兄弟七人,頭一個娶了妻子,沒有孩子就死了。
30ሁለተኛውም አገባት፥ ሦስተኛውም፥ እንዲሁም ሰባቱ ደግሞ ልጅ ሳይተዉ ሞቱ።
30第二個、
32ከሁሉም በኋላ ሴቲቱ ደግሞ ሞተች።
31第三個,也娶過她;七個都是這樣,都沒有留下孩子就死了。
33እንግዲህ ሰባቱ አግብተዋታልና ሴቲቱ በትንሣኤ ከእነርሱ ለማንኛቸው ሚስት ትሆናለች?
32後來那女人也死了。
34ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው። የዚህ ዓለም ልጆች ያገባሉ ይጋባሉም፥
33那麼,這女人在復活的時候,要作哪一個的妻子呢?因為七個人都娶過她。”
35ያን ዓለምና ከሙታን ትንሣኤ ሊያገኙ የሚገባቸው እነዚያ ግን አያገቡም አይጋቡምም፥ እንደ መላእክት ናቸውና፥
34耶穌說:“這世界的人又娶又嫁,
36ሊሞቱም ወደ ፊት አይቻላቸውም፥ የትንሣኤም ልጆች ስለ ሆኑ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው።
35但配得那世界的,又配從死人中復活的人,也不娶也不嫁。
37ሙታን እንዲነሡ ግን ሙሴ ደግሞ በቍጥቋጦው ዘንድ ጌታን የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ በማለቱ አስታወቀ፤
36他們和天使一樣,不能再死;既然是復活了的人,就是 神的兒女了。
38ሁሉ ለእርሱ ሕያዋን ስለ ሆኑ፥ የሕያዋን አምላክ ነው እንጂ የሙታን አይደለም።
37至於死人復活的事,摩西在荊棘篇上提過,他稱主是亞伯拉罕的 神、以撒的 神、雅各的 神;
39ከጻፎችም አንዳንዶቹ መልሰው። መምህር ሆይ፥ መልካም ተናገርህ አሉት።
38 神不是死人的 神,而是活人的 神,因為在他那裡的人都是活的。”
40ወደ ፊትም አንድ ነገር ስንኳ ሊጠይቁት አልደፈሩም።
39經學家中有幾個說:“老師,你說得好。”
41እንዲህም አላቸው። ክርስቶስ የዳዊት ልጅ ነው እንዴት ይላሉ?
40從此他們再不敢問他甚麼了。
42ዳዊትም ራሱ በመዝሙራት መጽሐፍ። ጌታ ጌታዬን። ጠላቶችህን ለእግርህ መርገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው ይላል።
41大衛稱基督為主(太22:41~45;可12:35~37)耶穌問他們:“人怎麼能說基督是大衛的子孫呢?
44እንግዲህ ዳዊት። ጌታ ብሎ ይጠራዋል፥ እንዴትስ ልጁ ይሆናል?
42大衛自己在詩篇上說:‘主對我的主說:你坐在我的右邊,
45ሕዝቡም ሁሉ ሲሰሙ ደቀ መዛሙርቱን።
43等我使你的仇敵作你的腳凳。’
46ረጃጅም ልብስ ለብሰው መዞር ከሚፈልጉ፥ በገበያም ሰላምታ፥ በምኵራብም የከበሬታ ወንበር፥ በምሳም የከበሬታ ስፍራ ከሚወዱ ከጻፎች ተጠበቁ፤
44大衛既然稱他為主,他又怎會是大衛的子孫呢?”
47የመበለቶችን ቤት የሚበሉ ጸሎታቸውንም በማስረዘም የሚያመካኙ፥ እነዚህ የባሰ ፍርድ ይቀበላሉ አለ።
45提防經學家(太23:1~36;可12:38~40)眾人聽著的時候,耶穌對門徒說:
46“你們要提防經學家,他們好穿長袍走來走去,喜歡人在巿中心向他們問安,並且喜歡會堂裡的高位、筵席上的首座。
47他們吞沒了寡婦的房產,又用冗長的禱告作掩飾。這等人必受更重的刑罰。”