Latvian: New Testament

Amharic: New Testament

1 Thessalonians

1

1Pāvils un Silvāns, un Timotejs tesalonīkiešu draudzei Dievā Tēvā un Kungā Jēzū Kristū:
1ጳውሎስና ስልዋኖስ ጢሞቴዎስም፥ በእግዚአብሔር አብ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስም ወደምትሆን ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች ቤተ ክርስቲያን፤ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስም ጸጋ ሰላምም ለእናንተ ይሁን።
2Žēlastība jums un miers! Mēs vienmēr pateicamies Dievam par jums visiem, pieminēdami jūs bez mitēšanās savās lūgšanās.
2በጸሎታችን ጊዜ ስለ እናንተ ስናሳስብ፥ የእምነታችሁን ስራ የፍቅራችሁንም ድካም በጌታችንም በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን የተስፋችሁን መጽናት በአምላካችንና በአባታችን ፊት ሳናቋርጥ እያሰብን፥ እግዚአብሔርን ሁል ጊዜ በሁላችሁ ምክንያት እናመሰግናለን፤
3Mēs atminamies jūsu ticības darbu un pūles, un mīlestību, un izturību cerībā uz mūsu Kungu Jēzu Kristu Dieva un mūsu Tēva priekšā.
4በእግዚአብሔር የምትወደዱ ወንድሞች ሆይ፥ እንደ ተመረጣችሁ አውቀናልና።
4Mēs zinām, Dieva mīlētie brāļi, ka jūs esat izredzēti,
5ወንጌላችን በኃይልና በመንፈስ ቅዱስ በብዙ መረዳትም እንጂ በቃል ብቻ ወደ እናንተ አልመጣምና፤ በእናንተ ዘንድ ስለ እናንተ እንዴት እንደ ነበርን ታውቃላችሁ።
5Jo mūsu evaņģēlijs bija pie jums ne tikvien vārdos, bet arī spēkā un Svētajā Garā, un visā pilnībā, kā jau jūs zināt, kādi mēs bijām pie jums jūsu dēļ.
6ደግሞ እናንተ ቃሉን በብዙ መከራ ከመንፈስ ቅዱስ ደስታ ጋር ተቀብላችሁ፥ እኛንና ጌታን የምትመስሉ ሆናችሁ፤
6Svētā Gara priekā pieņemdami vārdu daudzās apspiešanās, jūs kļuvāt mūsu un Kunga sekotāji.
7ስለዚህም በመቄዶንያና በአካይያ ላሉት ምእመናን ሁሉ ምሳሌ ሆናችሁላቸው።
7Un tā jūs esat priekšzīme visiem ticīgajiem Maķedonijā un Ahajā.
8ከእናንተ ወጥቶ የጌታ ቃል በመቄዶንያና በአካይያ ብቻ አልተሰማምና፥ ነገር ግን ምንም እንድንናገር እስከማያስፈልግ ድረስ፥ በእግዚአብሔር ዘንድ የሚሆን እምነታችሁ በሁሉ ስፍራ ተወርቶአል።
8Jo no jums izpaudās Kunga mācība ne tikai Maķedonijā un arī Ahajā, bet jūsu ticība uz Dievu izplatījusies visur, tā ka mums nekas vairs nav jāstāsta.
9እነርሱ ራሳቸው ወደ እናንተ መግባታችን እንዴት እንደነበረ ስለ እኛ ይናገራሉና፤ ለሕያውና ለእውነተኛ አምላክም ታገለግሉ ዘንድ፥ ከሙታንም ያስነሳውን ልጁን እርሱንም ኢየሱስን ከሚመጣው ቍጣ የሚያድነንን ከሰማይ ትጠብቁ ዘንድ፥ ከጣዖቶች ወደ እግዚአብሔር እንዴት ዘወር እንዳላችሁ ይናገራሉ።
9Jo viņi īpaši stāsta par mums, kā jūs uzņēmāt mūs un kā jūs no elkiem atgriezāties pie Dieva, lai kalpotu dzīvajam un patiesajam Dievam
10Un gaidītu no debesīm Viņa Dēlu Jēzu (ko Viņš uzmodināja no miroņiem), kas mūs izglāba no nākamajām dusmām.