1Sekojiet Dievam kā mīļi bērni!
1እንግዲህ እንደ ተወደዱ ልጆች እግዚአብሔርን የምትከተሉ ሁኑ፥
2Un dzīvojiet mīlestībā, kā arī Kristus mūs mīlējis un mūsu dēļ sevi atdevis Dievam par dāvanu un upuri jaukai smaržai.
2ክርስቶስም ደግሞ እንደ ወደዳችሁ ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እናንተ ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ በፍቅር ተመላለሱ።
3Bet netiklība un visāda veida nekrietnība vai mantkārība lai pat netiek pieminētas starp jums, kā tas pieklājas svētajiem!
3ለቅዱሳን እንደሚገባ ግን ዝሙትና ርኵሰት ሁሉ ወይም መመኘት በእናንተ ዘንድ ከቶ አይሰማ፤
4Arī bezkaunība, muļķīgas un tukšas runas, kas nepiedienas, bet vairāk pateicības.
4የሚያሳፍር ነገርም የስንፍና ንግግርም ወይም ዋዛ የማይገቡ ናቸውና አይሁኑ፥ ይልቁን ምስጋና እንጂ።
5Jo tas jums jāzina un jāsaprot, ka nevienam izvirtulim vai nešķīstam, vai mantrausim, jo tā ir kalpošana elkiem, nav mantojuma Kristus un Dieva valstībā.
5ይህን እወቁ፤ አመንዝራም ቢሆን ወይም ርኵስ ወይም የሚመኝ እርሱም ጣዖትን የሚያመልክ በክርስቶስና በእግዚአብሔር መንግሥት ርስት የለውም።
6Neviens lai jūs nepieviļ tukšiem vārdiem, jo to dēļ Dieva dusmas nāk pār netaisnības bērniem.
6ከዚህ የተነሣ በማይታዘዙት ልጆች ላይ የእግዚአብሔር ቁጣ ይመጣልና ማንም በከንቱ ንግግር አያታልላችሁ።
7Nekļūstiet par viņu līdzdalībniekiem!
7እንግዲህ ከእነርሱ ጋር ተካፋዮች አትሁኑ፤
8Jo reiz jūs bijāt tumsa, bet tagad gaisma Kungā. Dzīvojiet kā gaismas bērni!
8ቀድሞ ጨለማ ነበራችሁና፥ አሁን ግን በጌታ ብርሃን ናችሁ፤
9Gaismas augļi ir labums un taisnība, un patiesība.
9የብርሃኑ ፍሬ በበጎነትና በጽድቅ በእውነትም ሁሉ ነውና ለጌታ ደስ የሚያሰኘውን እየመረመራችሁ፥ እንደ ብርሃን ልጆች ተመላለሱ፤
10Pārbaudiet, kas Dievam patīk!
11ፍሬም ከሌለው ከጨለማ ሥራ ጋር አትተባበሩ፥ ይልቁን ግለጡት እንጂ፥
11Nepiedalieties neauglīgajos tumsības darbos, bet labāk nopeliet tos!
12እነርሱ በስውር ስለሚያደርጉት መናገር እንኳ ነውር ነውና፤
12Jo ko viņi slepenībā dara, par to pat kauns runāt.
13ሁሉ ግን በብርሃን ሲገለጥ ይታያል፤ የሚታየው ሁሉ ብርሃን ነውና።
13Visu, kas peļams, gaisma atklās, bet viss, kas gaismā celts, ir gaisma.
14ስለዚህ። አንተ የምትተኛ ንቃ ከሙታንም ተነሣ ክርስቶስም ያበራልሃል ይላል።
14Tāpēc tiek sacīts: Uzmosties, kas guli un celies augšām no miroņiem, un Kristus tevi apgaismos.
15እንግዲህ እንደ ጥበበኞች እንጂ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንዴት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ፤
15Tāpēc, brāļi, pielūkojiet, ka jūs apdomīgi dzīvotu, - nevis kā negudri,
16ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ።
16Bet kā gudri! Izmantojiet laiku, jo šīs dienas ir ļaunas!
17ስለዚህ የጌታ ፈቃድ ምን እንደ ሆነ አስተውሉ እንጂ ሞኞች አትሁኑ።
17Nekļūstiet neprātīgi, bet izprotiet Dieva gribu!
18መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ ይህ ማባከን ነውና፤
18Neapreibinieties ar vīnu, jo tanī slēpjas izvirtība, bet pildiet sevi ar Svēto Garu!
19በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ፤ ለጌታ በልባችሁ ተቀኙና ዘምሩ፤
19Dziedādami un gavilēdami skandiniet savās sirdīs Kungam psalmus un slavas dziesmas, un garīgās dziesmas,
20ሁልጊዜ ስለ ሁሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አምላካችንንና አባታችንን ስለ ሁሉ አመስግኑ።
20Pateikdamies vienmēr par visu Dievam un Tēvam mūsu Kunga Jēzus Kristus vārdā!
21ለእያንዳንዳችሁ በክርስቶስ ፍርሃት የተገዛችሁ ሁኑ።
21Kristus bijībā esiet viens otram padevīgi!
22ሚስቶች ሆይ፥ ለጌታ እንደምትገዙ ለባሎቻችሁ ተገዙ፤
22Sievas lai ir paklausīgas saviem vīriem kā Kungam,
23ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ እርሱም አካሉን የሚያድን እንደ ሆነ ባል የሚስት ራስ ነውና።
23Jo vīrs ir sievas galva, tāpat kā Kristus - Baznīcas galva, būdams savas miesas Pestītājs.
24ዳሩ ግን ቤተ ክርስቲያን ለክርስቶስ እንደምትገዛ እንዲሁ ሚስቶች ደግሞ በሁሉ ለባሎቻቸው ይገዙ።
24Bet kā Baznīca Kristum, tā sievas visā padotas saviem vīriem.
25ባሎች ሆይ፥ ክርስቶስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤ በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት ስለ እርስዋ ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤
25Vīri, mīliet savas sievas, tāpat kā arī Kristus mīlējis Baznīcu un sevi atdevis par viņu.
27እድፈት ወይም የፊት መጨማደድ ወይም እንዲህ ያለ ነገር ሳይሆንባት ቅድስትና ያለ ነውር ትሆን ዘንድ ክብርት የሆነችን ቤተ ክርስቲያን ለራሱ እንዲያቀርብ ፈለገ።
26Lai viņu darītu svētu, šķīstot to ūdens kristībā un dzīvības vārdiem.
28እንዲሁም ባሎች ደግሞ እንደ ገዛ ሥጋቸው አድርገው የገዛ ሚስቶቻቸውን ሊወዱአቸው ይገባቸዋል። የገዛ ሚስቱን የሚወድ ራሱን ይወዳል፤
27Sagatavodams sev krāšņu Baznīcu, kurai nav ne traipa, ne grumbas, ne cita kā tamlīdzīga, bet lai tā būtu svēta un bez vainas.
29ማንም የገዛ ሥጋውን የሚጠላ ከቶ የለምና፥ ነገር ግን የአካሉ ብልቶች ስለሆንን፥ ክርስቶስ ደግሞ ለቤተ ክርስቲያን እንዳደረገላት፥ ይመግበዋል ይከባከበውማል።
28Tā arī vīriem jāmīl savas sievas kā sava miesa. Kas savu sievu mīl, tas mīl pats sevi,
31ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይተባበራል ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።
29Jo neviens vēl nekad nav ienīdis savu miesu, bet to kopj un saudzē tāpat kā Kristus - Baznīcu.
32ይህ ምሥጢር ታላቅ ነው፥ እኔ ግን ይህን ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተ ክርስቲያን እላለሁ።
30Jo mēs esam Viņa miesas locekļi: no Viņa miesas un no Viņa kauliem.
33ሆኖም ከእናንተ ደግሞ እያንዳንዱ የገዛ ሚስቱን እንዲህ እንደ ራሱ አድርጎ ይውደዳት፥ ሚስቱም ባልዋን ትፍራ።
31Tāpēc cilvēks atstās tēvu un savu māti un pievienosies savai sievai, un abi būs viena miesa.
32Šis noslēpums ir liels, bet es saku: Kristū un Baznīcā.
33Tiešām, arī katram no jums jāmīl sava sieva, tāpat kā mīl pats sevi, bet sieva lai jūt bijību pret savu vīru!