Lithuanian

Amharic: New Testament

1 Peter

2

1Taigi, atmetę visokį blogį, visokią klastą ir veidmainystes, pavyduliavimus ir visokias apkalbas,
1እንግዲህ ክፋትን ሁሉ ተንኰልንም ሁሉ ግብዝነትንም ቅንዓትንም ሐሜትንም ሁሉ አስወግዳችሁ፥
2lyg naujagimiai trokškite tyro žodžio pieno, kad nuo jo augtumėte išgelbėjimui,
2ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እንደ ሆነ፥ ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ተንኰል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ።
3jeigu tikrai paragavote, koks Viešpats yra maloningas.
4በሰውም ወደ ተጣለ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ወደ ተመረጠና ክቡር ወደ ሆነው ወደ ሕያው ድንጋይ ወደ እርሱ እየቀረባችሁ፥
4Ženkite prie Jo, gyvojo akmens, tiesa, žmonių atmesto, bet Dievo išrinkto, brangaus,
5እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።
5ir patys, kaip gyvieji akmenys, statydinkitės į dvasinius namus, kad būtumėte šventa kunigystė ir atnašautumėte dvasines aukas, priimtinas Dievui per Jėzų Kristų.
6በመጽሐፍ። እነሆ፥ የተመረጠና የከበረን የማዕዘን ራስ ድንጋይ በጽዮን አኖራለሁ በእርሱም የሚያምን አያፍርም ተብሎ ተጽፎአልና።
6Todėl Rašte pasakyta: “Štai dedu Sione kertinį akmenį, rinktinį, brangų; ir kas tiki Jį, nebus sugėdintas”.
7እንግዲህ ክብሩ ለእናንተ ለምታምኑት ነው፤ ለማያምኑ ግን አናጢዎች የጣሉት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ የዕንቅፋትም ድንጋይ የማሰናከያም ዓለት ሆነ፤
7Tad jums, kurie tikite, Jis yra brangus, o nepaklūstantiems “tas statytojų atmestas akmuo tapo kertiniu akmeniu,
8የማያምኑ ስለ ሆኑ በቃሉ ይሰናከሉበታልና፤ ለዚህ ደግሞ የተመደቡ ናቸው።
8suklupimo akmeniu ir papiktinimo uola”. Jie suklumpa, neklausydami žodžio; tam jie ir skirti.
9እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤
9O jūs esate “išrinktoji giminė, karališkoji kunigystė, šventoji tauta, ypatingi žmonės, kad skelbtumėte dorybes” To, kuris pašaukė jus iš tamsybių į savo nuostabią šviesą.
10እናንተ ቀድሞ ወገን አልነበራችሁም አሁን ግን የእግዚአብሔር ወገን ናችሁ፤ እናንተ ምሕረት ያገኛችሁ አልነበራችሁም አሁን ግን ምሕረትን አግኝታችኋል።
10Seniau ne tauta, dabar Dievo tauta, seniau neradę gailestingumo, dabar jį suradę.
11ወዳጆች ሆይ፥ ነፍስን ከሚዋጋ ሥጋዊ ምኞት ትርቁ ዘንድ እንግዶችና መጻተኞች እንደ መሆናችሁ እለምናችኋለሁ፤
11Mylimieji, maldauju jus kaip svečius ir ateivius: susilaikykite nuo kūno geidulių, kurie kovoja prieš sielą.
12ስለሚመለከቱት ስለ መልካም ሥራችሁ፥ ክፉ እንደምታደርጉ በዚያ እናንተን በሚያሙበት ነገር፥ በሚጎበኝበት ቀን እግዚአብሔርን ያከብሩት ዘንድ በአሕዛብ መካከል ኑሮአችሁ መልካም ይሁን።
12Jūsų elgesys tarp pagonių tebūna kilnus, kad jie už tai, už ką šmeižia jus kaip piktadarius, pamatę jūsų gerus darbus, imtų šlovinti Dievą aplankymo dieną.
13ስለ ጌታ ብላችሁ ለሰው ሥርዓት ሁሉ ተገዙ፤ ለንጉሥም ቢሆን፥ ከሁሉ በላይ ነውና፤
13Būkite klusnūs kiekvienai žmonių valdžiai dėl Viešpaties: tiek karaliui, kaip vyriausiajam,
14ለመኳንንትም ቢሆን፥ ክፉ የሚያደርጉትን ለመቅጣት በጎም የሚያደርጉትን ለማመስገን ከእርሱ ተልከዋልና ተገዙ።
14tiek valdytojams, kaip jo pasiųstiems bausti piktadarių ir pagirti geradarių.
15በጎ እያደረጋችሁ፥ የማያውቁትን ሞኞች ዝም ታሰኙ ዘንድ እንዲህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነውና፤
15Mat tokia Dievo valia, kad, darydami gera, nutildytumėte neprotingų žmonių neišmanymą.
16አርነት ወጥታችሁ እንደ እግዚአብሔር ባሪያዎች ሁኑ እንጂ ያ አርነት ለክፋት መሸፈኛ እንዲሆን አታድርጉ።
16Elkitės kaip laisvi; ne kaip tie, kurie laisve pridengia blogį, bet kaip Dievo tarnai.
17ሁሉን አክብሩ፥ ወንድሞችን ውደዱ፥ እግዚአብሔርን ፍሩ፥ ንጉሥን አክብሩ።
17Gerbkite visus, mylėkite broliją, bijokite Dievo, gerbkite karalių.
18ሎሌዎች ሆይ፥ ለበጎዎችና ለገሮች ጌቶቻችሁ ብቻ ሳይሆን ለጠማሞች ደግሞ በፍርሃት ሁሉ ተገዙ።
18Tarnai, su visa baime būkite klusnūs šeimininkams, ne tik geriems ir švelniems, bet ir rūstiems.
19በግፍ መከራን የሚቀበል ሰው እግዚአብሔርን እያሰበ ኃዘንን ቢታገሥ ምስጋና ይገባዋልና።
19Girtina, jeigu kas dėl Dievo pažinimo pakelia skausmus, nekaltai kentėdamas.
20ኃጢአት አድርጋችሁ ስትጎሰሙ ብትታገሡ፥ ምን ክብር አለበት? ነገር ግን መልካም አድርጋችሁ መከራን ስትቀበሉ ብትታገሡ፥ ይህ ነገር በእግዚአብሔር ዘንድ ምስጋና ይገባዋል።
20Menka garbė, jei jūs kantrūs, kai esate plakami už nusikaltimus. Bet kai esate kantrūs, darydami gera ir kentėdami, Dievo akyse tai verta pagyrimo.
21የተጠራችሁለት ለዚህ ነውና፤ ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአልና።
21Juk jūs tam pašaukti; ir Kristus kentėjo už mus, palikdamas mums pavyzdį, kad eitumėte Jo pėdomis.
22እርሱም ኃጢአት አላደረገም፥ ተንኰልም በአፉ አልተገኘበትም፤
22Jis “nepadarė nuodėmės, ir Jo lūpose nerasta klastos”.
23ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም መከራንም ሲቀበል አልዛተም፥ ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤
23Šmeižiamas neatsakė tuo pačiu, kentėdamas negrasino, bet pavedė save Tam, kuris teisia teisingai.
24ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤*ፍ1*
24Jis pats savo kūne užnešė mūsų nuodėmes ant medžio, kad mirę nuodėmėms, gyventume teisumui. “Jo žaizdomis jūs buvote išgydyti”.
25በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ። እንደ በጎች ትቅበዘበዙ ነበርና፥ አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመልሳችኋል።
25Jūs buvote tarsi klaidžiojančios avys, o dabar sugrįžote pas savo sielų Ganytoją ir Sargą.