Lithuanian

Amharic: New Testament

Mark

10

1Jėzus, iškeliavęs iš ten, atvyksta į Judėją ir Užjordanę. Žmonių būriai vėl susirinko pas Jį, ir Jis vėl mokė, kaip buvo pratęs.
1ከዚያም ተነሥቶ በዮርዳኖስ ማዶ ወደ ይሁዳ አገር መጣ፥ ደግሞም ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ ተሰበሰቡ እንደ ልማዱም ደግሞ ያስተምራቸው ነበር።
2Tada atėjo fariziejų, kurie, mėgindami Jį, klausė, ar galima vyrui atleisti žmoną.
2ፈሪሳውያንም ቀርበው። ሰው ሚስቱን ሊፈታ ተፈቅዶለታልን? ብለው ሊፈትኑት ጠየቁት።
3Jis jiems atsakė: “O ką jums įsakė Mozė?”
3እርሱ ግን መልሶ። ሙሴ ምን አዘዛችሁ? አላቸው።
4Jie tarė: “Mozė leido parašyti skyrybų raštą ir atleisti”.
4እነርሱም። ሙሴስ የፍችዋን ጽሕፈት ጽፎ እንዲፈታት ፈቀደ አሉ።
5Tuomet Jėzus pasakė: “Dėl jūsų širdies kietumo parašė jums Mozė tokį nuostatą.
5ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው። ስለ ልባችሁ ጥንካሬ ይህችን ትእዛዝ ጻፈላችሁ።
6O nuo sutvėrimo pradžios Dievas ‘sukūrė juos, vyrą ir moterį’.
6ከፍጥረት መጀመሪያ ግን እግዚአብሔር ወንድና ሴት አደረጋቸው፤
7‘Todėl vyras paliks savo tėvą ir motiną ir susijungs su savo žmona,
7ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይተባበራል፥
8ir du taps vienu kūnu’. Taigi jie jau nebėra du, o vienas kūnas.
8ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ፤ ስለዚህ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ወደ ፊት ሁለት አይደሉም።
9Todėl ką Dievas sujungė, žmogus teneperskiria”.
9እግዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለየው።
10Namie mokiniai vėl klausė Jį apie tai.
10በቤትም ደግሞ ደቀ መዛሙርቱ ስለዚህ ነገር ጠየቁት።
11Jis atsakė: “Kas atleidžia savo žmoną ir veda kitą, tas nusikalsta pirmajai svetimavimu.
11እርሱም። ሚስቱን ፈትቶ ሌላ የሚያገባ ሁሉ በእርስዋ ላይ ያመነዝራል፤
12Ir jei moteris palieka savo vyrą ir išteka už kito, ji svetimauja”.
12እርስዋም ባልዋን ፈትታ ሌላ ብታገባ ታመነዝራለች አላቸው።
13Jam nešė vaikučius, kad juos palytėtų, bet mokiniai jiems draudė.
13እንዲዳስሳቸውም ሕፃናትን ወደ እርሱ አመጡ፤ ደቀ መዛሙርቱም ያመጡአቸውን ገሠጹአቸው።
14Tai pamatęs, Jėzus pyktelėjo ir tarė jiems: “Leiskite mažutėliams ateiti pas mane ir netrukdykite, nes tokių yra Dievo karalystė.
14ኢየሱስ ግን አይቶ ተቈጣና። ሕፃናትን ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ ተዉ አትከልክሉአቸው፤ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደነዚህ ላሉት ናትና።
15Iš tiesų sakau jums: kas nepriims Dievo karalystės kaip mažas vaikas,­niekaip neįeis į ją”.
15እውነት እላችኋለሁ፤ የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደ ሕፃን የማይቀበላት ሁሉ ከቶ አይገባባትም አላቸው።
16Ir Jis laimino juos, apkabindamas ir dėdamas ant jų rankas.
16አቀፋቸውም እጁንም ጭኖ ባረካቸው።
17Jėzui išeinant į kelią, vienas žmogus pribėgęs puolė prieš Jį ant kelių ir klausė: “Gerasis Mokytojau, ką turiu daryti, kad paveldėčiau amžinąjį gyvenimą?”
17እርሱም በመንገድ ሲወጣ አንድ ሰው ወደ እርሱ ሮጦ ተንበረከከለትና። ቸር መምህር ሆይ፥ የዘላለም ሕይወትን እወርስ ዘንድ ምን ላድርግ? ብሎ ጠየቀው።
18Jėzus jam tarė: “Kam vadini mane geru? Nė vieno nėra gero, tik vienas Dievas.
18ኢየሱስም። ስለ ምን ቸር ትለኛለህ? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ቸር ማንም የለም።
19Žinai įsakymus: ‘Nesvetimauk, nežudyk, nevok, melagingai neliudyk, neapgaudinėk, gerbk savo tėvą ir motiną’ ”.
19ትእዛዛትን ታውቃለህ፤ አታመንዝር፥ አትግደል፥ አትስረቅ፥ በሐሰት አትመስክር፥ አታታልል፥ አባትህንና እናትህን አክብር አለው።
20Tas atsakė: “Mokytojau, aš viso to laikausi nuo savo jaunystės”.
20እርሱም መልሶ። መምህር ሆይ፥ ይህን ሁሉ ከሕፃንነቴ ጀምሬ ጠብቄአለሁ አለው።
21Jėzus, pažvelgęs į jį, jį pamilo ir tarė: “Vieno dalyko tau trūksta: eik, parduok visa, ką turi, išdalink vargšams ir turėsi turtą danguje. Tada ateik, paimk kryžių ir sek paskui mane”.
21ኢየሱስም ወደ እርሱ ተመልክቶ ወደደውና። አንድ ነገር ጐደለህ፤ ሂድ፥ ያለህን ሁሉ ሽጠህ ለድሆች ስጥ፥ በሰማይም መዝገብ ታገኛለህ፥ መስቀሉንም ተሸክመህ ና፥ ተከተለኝ አለው።
22Po šitų žodžių jis nuliūdo ir nusiminęs pasitraukė, nes turėjo daug turto.
22ነገር ግን ስለዚህ ነገር ፊቱ ጠቈረ፥ ብዙ ንብረት ነበረውና እያዘነም ሄደ።
23Jėzus apsidairė ir prabilo į mokinius: “Kaip sunkiai turtingi įeis į Dievo karalystę!”
23ኢየሱስም ዘወር ብሎ አይቶ ደቀ መዛሙርቱን። ገንዘብ ላላቸው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት እንዴት ጭንቅ ይሆናል አላቸው።
24Mokiniai buvo priblokšti Jo žodžių. Tada Jėzus vėl jiems tarė: “Vaikeliai, kaip sunku tiems, kurie pasitiki turtais, įeiti į Dievo karalystę!
24ደቀ መዛሙርቱም እነዚህን ቃሎች አደነቁ። ኢየሱስም ደግሞ መልሶ። ልጆች ሆይ፥ በገንዘብ ለሚታመኑ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት እንዴት ጭንቅ ነው።
25Lengviau kupranugariui išlįsti pro adatos ausį, negu turtingam įeiti į Dievo karalystę”.
25ባለ ጠጋ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል አላቸው።
26Mokiniai dar labiau nustebo ir kalbėjosi: “Kas tada gali būti išgelbėtas?”
26እነርሱም ያለ መጠን ተገረሙና እርስ በርሳቸው። እንግዲያ ማን ሊድን ይችላል? ተባባሉ።
27Jėzus pažvelgė į juos ir tarė: “Žmonėms tai neįmanoma, bet ne Dievui, nes Dievui viskas įmanoma”.
27ኢየሱስም ተመለከታቸውና። ይህ በእግዚአብሔር ዘንድ እንጂ በሰው ዘንድ አይቻልም፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ሁሉ ይቻላልና አለ።
28Tada Petras sakė Jam: “Štai mes viską palikome ir sekame paskui Tave!”
28ጴጥሮስም። እነሆ፥ እኛ ሁሉን ትተን ተከተልንህ ይለው ጀመር።
29Jėzus tarė: “Iš tiesų sakau jums: nėra nė vieno, kuris paliktų namus ar brolius, ar seseris, ar motiną, ar tėvą, ar vaikus, ar laukus dėl manęs ir dėl Evangelijos
29ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለ። እውነት እላችኋለሁ፥ ስለ እኔና ስለ ወንጌል ቤትን ወይም ወንድሞችን ወይም እኅቶችን ወይም አባትን ወይም እናትን ወይም ሚስትን ወይም ልጆችን ወይም እርሻን የተወ፥
30ir kuris jau dabar, šiuo metu, negautų šimteriopai namų, brolių, seserų, motinų, vaikų ir laukų kartu su persekiojimais ir būsimajame amžiuje­amžinojo gyvenimo.
30አሁን በዚህ ዘመን ከስደት ጋር ቤቶችን ወንድሞችንና እኅቶችንም እናቶችንም ልጆችንም እርሻንም መቶ እጥፍ፥ በሚመጣውም ዓለም የዘላለም ሕይወት የማይቀበል ማንም የለም።
31Tačiau daug pirmųjų bus paskutiniai, ir paskutiniai­pirmi”.
31ግን ብዙ ፊተኞች ኋለኞች ኋለኞችም ፊተኞች ይሆናሉ።
32Jiems bekeliaujant į Jeruzalę, Jėzus ėjo priekyje, o mokiniai stebėjosi. Sekdami iš paskos, jie nuogąstavo. Vėl pasišaukęs dvylika, pradėjo jiems sakyti, kas Jo laukia:
32ወደ ኢየሩሳሌምም ሊወጡ በመንገድ ነበሩ፥ ኢየሱስም ይቀድማቸው ነበርና ተደነቁ፤ የተከተሉትም ይፈሩ ነበር። ደግሞም አሥራ ሁለቱን ወደ እርሱ አቅርቦ ይደርስበት ዘንድ ያለውን ይነግራቸው ጀመር።
33“Štai einame į Jeruzalę, ir Žmogaus Sūnus bus išduotas aukštiesiems kunigams ir Rašto žinovams. Jie nuteis Jį mirti ir atiduos pagonims,
33እነሆ፥ ወደ ኢየሩሳሌም እንወጣለን፥ የሰው ልጅም ለካህናት አለቆችና ለጻፎች አልፎ ይሰጣል፥ የሞት ፍርድም ይፈርዱበታል፥ ለአሕዛብም አሳልፈው ይሰጡታል፥
34tie tyčiosis iš Jo, apspjaudys, nuplaks ir nužudys, ir trečią dieną Jis prisikels”.
34ይዘብቱበትማል ይተፉበትማል ይገርፉትማል ይገድሉትማል፥ በሦስተኛውም ቀን ይነሣል አላቸው።
35Prie Jėzaus priėjo Zebediejaus sūnūs Jokūbas ir Jonas ir kreipėsi: “Mokytojau, mes norime, kad padarytum mums viską, ko tik prašysime”.
35የዘብዴዎስ ልጆች ያዕቆብና ዮሐንስም ወደ እርሱ ቀርበው። መምህር ሆይ፥ የምንለምንህን ሁሉ እንድታደርግልን እንወዳለን አሉት።
36Jis atsakė: “Ko norite, kad jums padaryčiau?”
36እርሱም። ምን ላደርግላችሁ ትወዳላችሁ? አላቸው።
37Jie tarė: “Leisk mums sėdėti vienam Tavo dešinėje, kitam­kairėje, Tavo šlovėje!”
37እነርሱም። በክብርህ ጊዜ አንዳችን በቀኝ አንዳችንም በግራህ መቀመጥን ስጠን አሉት።
38Jėzus atsakė: “Nežinote, ko prašote. Ar galite gerti taurę, kurią Aš geriu, ir būti pakrikštyti krikštu, kuriuo Aš krikštijamas?”
38ኢየሱስ ግን። የምትለምኑትን አታውቁም። እኔ የምጠጣውን ጽዋ ልትጠጡ፥ እኔ የምጠመቀውንስ ጥምቀት ልትጠመቁ ትችላላችሁን? አላቸው።
39Jie sakė: “Galime”. Jėzus jiems tarė: “Tiesa, taurę, kurią Aš geriu, jūs gersite, ir krikštu, kuriuo Aš krikštijamas, jūs irgi būsite pakrikštyti.
39እነርሱም። እንችላለን አሉት። ኢየሱስም። እኔ የምጠጣውን ጽዋ ትጠጣላችሁ፥ እኔ የምጠመቀውንም ጥምቀት ትጠመቃላችሁ፤
40Bet vietą savo dešinėje ar kairėje ne Aš duodu,­tai bus tiems, kuriems paskirta”.
40በቀኝና በግራ መቀመጥ ግን ለተዘጋጀላቸው ነው እንጂ የምሰጥ እኔ አይደለሁም አላቸው።
41Tai išgirdę, kiti dešimt labai supyko ant Jokūbo ir Jono.
41አሥሩም ሰምተው በያዕቆብና በዮሐንስ ይቈጡ ጀመር።
42O Jėzus, pasikvietęs juos, tarė: “Jūs žinote, kad tie, kurie laikomi pagonių valdovais, viešpatauja jiems, ir jų didieji juos valdo.
42ኢየሱስም ወደ እርሱ ጠርቶ እንዲህ አላቸው። የአሕዛብ አለቆች ተብሎ የምታስቡት እንዲገዙአቸው ታላላቆቻቸውም በላያቸው እንዲሠለጥኑ ታውቃላችሁ።
43Bet tarp jūsų taip neturi būti. Kas iš jūsų nori būti didžiausias, bus jūsų tarnas,
43በእናንተስ እንዲህ አይደለም፤ ነገር ግን ማንም ከእናንተ ታላቅ ሊሆን የሚወድ የእናንተ አገልጋይ ይሁን፥
44ir kas nori tarp jūsų būti pirmas, bus visų vergas.
44ከእናንተም ማንም ፊተኛ ሊሆን የሚወድ የሁሉ ባሪያ ይሁን፤
45Juk ir Žmogaus Sūnus atėjo, ne kad Jam tarnautų, bet pats tarnauti ir savo gyvybės atiduoti kaip išpirkos už daugelį”.
45እንዲሁ የሰው ልጅም ሊያገለግልና ነፍሱን ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።
46Jie atėjo į Jerichą. O iškeliaujant Jam su mokiniais ir gausia minia iš Jericho, neregys Bartimiejus, Timiejaus sūnus, sėdėjo šalikelėje elgetaudamas.
46ወደ ኢያሪኮም መጡ። ከደቀ መዛሙርቱና ከብዙ ሕዝብ ጋር ከኢያሪኮ ሲወጣ የጤሜዎስ ልጅ ዕውሩ በርጤሜዎስ እየለመነ በመንገድ ዳር ተቀምጦ ነበር።
47Išgirdęs, jog čia Jėzus iš Nazareto, jis pradėjo garsiai šaukti: “Jėzau, Dovydo Sūnau, pasigailėk manęs!”
47የናዝሬቱ ኢየሱስም እንደ ሆነ በሰማ ጊዜ። የዳዊት ልጅ ኢየሱስ ሆይ፥ ማረኝ እያለ ይጮኽ ጀመር።
48Daugelis jį draudė, kad nutiltų, bet jis dar garsiau šaukė: “Dovydo Sūnau, pasigailėk manęs!”
48ብዙዎችም ዝም እንዲል ገሠጹት፤ እርሱ ግን። የዳዊት ልጅ ሆይ፥ ማረኝ እያለ አብዝቶ ጮኸ።
49Jėzus sustojo ir tarė: “Pašaukite jį”. Žmonės pašaukė neregį, sakydami: “Pasitikėk! Kelkis, Jis tave šaukia”.
49ኢየሱስም ቆመና። ጥሩት አለ። ዕውሩንም። አይዞህ፥ ተነሣ፥ ይጠራሃል ብለው ጠሩት።
50Tas, nusimetęs apsiaustą, pašoko ir atėjo prie Jėzaus.
50እርሱም እየዘለለ ተነሣና ልብሱን ጥሎ ወደ ኢየሱስ መጣ።
51Jėzus jo paklausė: “Ko nori, kad tau padaryčiau?” Neregys atsakė: “Rabuni, kad praregėčiau!”
51ኢየሱስም መልሶ። ምን ላደርግልህ ትወዳለህ? አለው። ዕውሩም። መምህር ሆይ፥ አይ ዘንድ አለው።
52Tada Jėzus jam tarė: “Eik, tavo tikėjimas išgydė tave”. Jis tuoj pat praregėjo ir nusekė paskui Jėzų keliu.
52ኢየሱስም። ሂድ፤ እምነትህ አድኖሃል አለው። ወዲያውም አየ በመንገድም ተከተለው።