Lithuanian

Amharic: New Testament

Matthew

11

1Baigęs nurodymus dvylikai savo mokinių, Jėzus iškeliavo toliau mokyti ir pamokslauti kituose miestuose.
1ኢየሱስም አሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርቱን ማዘዝ በፈጸመ ጊዜ በከተሞቻቸው ሊያስተምርና ሊሰብክ ከዚያ አለፈ።
2Jonas, išgirdęs kalėjime apie Kristaus darbus, nusiuntė du savo mokinius
2ዮሐንስም በወህኒ ሳለ የክርስቶስን ሥራ ሰምቶ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለት ላከና።
3Jo paklausti: “Ar Tu esi Tas, kuris turi ateiti, ar mums laukti kito?”
3የሚመጣው አንተ ነህን? ወይስ ሌላ እንጠብቅ? አለው።
4Jėzus jiems atsakė: “Eikite ir pasakykite Jonui, ką girdite ir matote:
4ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው። ሄዳችሁ ያያችሁትን የሰማችሁትንም ለዮሐንስ አውሩለት፤
5aklieji praregi, luošieji vaikščioja, raupsuotieji apvalomi, kurtieji girdi, mirusieji prikeliami, vargšams skelbiama Evangelija.
5ዕውሮች ያያሉ አንካሶችም ይሄዳሉ፥ ለምጻሞችም ይነጻሉ ደንቆሮችም ይሰማሉ፥ ሙታንም ይነሣሉ
6Ir palaimintas, kas nepasipiktina manimi”.
6ለድሆችም ወንጌል ይሰበካል፤ በእኔም የማይሰናከለው ሁሉ ብፁዕ ነው።
7Jiems nueinant, Jėzus ėmė kalbėti minioms apie Joną: “Ko išėjote į dykumą pažiūrėti? Ar vėjo linguojamos nendrės?
7እነዚያም ሲሄዱ ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ ዮሐንስ ሊናገር ጀመረ እንዲህም አለ። ምን ልታዩ ወደ ምድረ በዳ ወጣችሁ?
8Ko gi išėjote pamatyti? Ar švelniais drabužiais vilkinčio žmogaus? Švelniais drabužiais vilkintys gyvena karaliaus rūmuose.
8ነፋስ የሚወዘውዘውን ሸምበቆን? ወይስ ምን ልታዩ ወጣችሁ? ቀጭን ልብስ የለበሰ ሰውን? እነሆ፥ ቀጭን ልብስ የለበሱ በነገሥታት ቤት አሉ።
9Tai ko gi išėjote pamatyti? Ar pranašo? Taip, sakau jums, ir kur kas daugiau negu pranašo!
9ወይስ ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይን? አዎን እላችኋለሁ፥ ከነቢይም የሚበልጠውን።
10Jis yra tas, apie kurį parašyta: ‘Štai Aš siunčiu pirma Tavęs savo pasiuntinį, kuris nuties prieš Tave kelią’.
10እነሆ፥ መንገድህን በፊትህ የሚጠርግ መልክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ
11Iš tiesų sakau jums: tarp gimusių iš moterų nepakilo didesnis už Joną Krikštytoją, bet ir mažiausias dangaus karalystėje didesnis už jį.
11ተብሎ የተጻፈለት ይህ ነውና። እውነት እላችኋለሁ፥ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም፤ በመንግሥተ ሰማያት ግን ከሁሉ የሚያንሰው ይበልጠዋል።
12Nuo Jono Krikštytojo dienų iki dabar dangaus karalystė grobiama, ir stiprieji ją jėga ima.
12ከመጥምቁም ከዮሐንስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ መንግሥተ ሰማያት ትገፋለች፥ ግፈኞችም ይናጠቋታል።
13Visi pranašai ir Įstatymas pranašavo iki Jono
13ነቢያት ሁሉና ሕጉ እስከ ዮሐንስ ድረስ ትንቢት ተናገሩ፤
14ir, jeigu norite priimti, tai jis ir yra Elijas, kuris turi ateiti.
14ልትቀበሉትስ ብትወዱ፥ ይመጣ ዘንድ ያለው ኤልያስ ይህ ነው።
15Kas turi ausis klausyti­teklauso!”
15የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።
16“Su kuo galėčiau palyginti šią kartą? Ji panaši į vaikus, kurie sėdi prekyvietėje ir šaukia savo draugams:
16ነገር ግን ይህን ትውልድ በምን እመስለዋለሁ? በገበያ የሚቀመጡትን ልጆች ይመስላሉ፥ እነርሱም ባልንጀሮቻቸውን እየጠሩ።
17‘Mes jums grojome, o jūs nešokote. Mes giedojome raudas, o jūs neraudojote’.
17እንቢልታ ነፋንላችሁ ዘፈንም አልዘፈናችሁም ሙሾ አወጣንላችሁ ዋይ ዋይም አላላችሁም ይሉአቸዋል።
18Atėjo Jonas, nevalgus ir negeriantis, tai jie sako: ‘Jis demono apsėstas’.
18ዮሐንስ ሳይበላና ሳይጠጣ መጣ፥ እነርሱም። ጋኔን አለበት አሉት።
19Atėjo Žmogaus Sūnus, valgantis ir geriantis, tai jie sako: ‘Štai rijūnas ir vyno gėrėjas, muitininkų ir nusidėjėlių bičiulis’. Bet išmintį pateisina jos vaikai”.
19የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ መጣ፥ እነርሱም። እነሆ፥ በላተኛና የወይን ጠጅ ጠጭ፥ የቀራጮችና የኃጢአተኞች ወዳጅ ይሉታል። ጥበብም በልጆችዋ ጸደቀች።
20Tada Jis pradėjo priekaištauti miestams, kuriuose buvo padaryta daugumas Jo stebuklų, kad jie neatgailavo:
20በዚያን ጊዜ የሚበዙ ተአምራት የተደረገባቸውን ከተማዎች ንስሐ ስላልገቡ ሊነቅፋቸው ጀመረ እንዲህም አለ።
21“Vargas tau, Chorazine! Vargas tau, Betsaida! Jeigu Tyre ir Sidone būtų įvykę tokių stebuklų, kokie padaryti pas jus, jie seniai būtų atgailavę su ašutine bei pelenuose.
21ወዮልሽ ኮራዚ፤ ወዮልሽ ቤተ ሳይዳ፤ በእናንተ የተደረገው ተአምራት በጢሮስና በሲዶና ተደርጎ ቢሆን፥ ማቅ ለብሰው አመድም ነስንሰው ከብዙ ጊዜ በፊት ንስሐ በገቡ ነበርና።
22Todėl sakau jums: Tyrui ir Sidonui bus lengviau teismo dieną negu jums!
22ነገር ግን እላችኋለሁ፥ በፍርድ ቀን ከእናንተ ይልቅ ለጢሮስና ለሲዶና ይቀልላቸዋል።
23Ir tu, Kafarnaume, išaukštintas iki dangaus, nugarmėsi iki pragaro! Jeigu Sodomoje būtų įvykę tokių stebuklų, kokių įvyko tavyje, ji būtų išlikusi iki šios dienos.
23አንቺም ቅፍርናሆም፥ እስከ ሰማይ ከፍ አልሽን? ወደ ሲኦል ትወርጃለሽ፤ በአንቺ የተደረገው ተአምራት በሰዶም ተደርጎ ቢሆን፥ እስከ ዛሬ በኖረች ነበርና።
24Todėl sakau jums: Sodomos žemei bus lengviau teismo dieną negu tau”.
24ነገር ግን እላችኋለሁ፥ በፍርድ ቀን ከአንቺ ይልቅ ለሰዶም አገር ይቀልላታል።
25Anuo metu Jėzus kalbėjo: “Aš šlovinu Tave, Tėve, dangaus ir žemės Viešpatie, kad paslėpei tai nuo išmintingųjų ir gudriųjų, o apreiškei mažutėliams.
25በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለ። አባት ሆይ፥ የሰማይና የምድር ጌታ፥ ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግንሃለሁ፤
26Taip, Tėve, nes Tau taip patiko.
26አዎን፥ አባት ሆይ፥ ፈቃድህ በፊትህ እንዲህ ሆኖአልና።
27Viskas man yra mano Tėvo atiduota; ir niekas nepažįsta Sūnaus, tik Tėvas, nei Tėvo niekas nepažįsta, tik Sūnus ir kam Sūnus nori apreikšti.
27ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ የለም፥ ከወልድም በቀር ወልድም ሊገለጥለት ከሚፈቅድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም።
28Ateikite pas mane visi, kurie vargstate ir esate prislėgti, ir Aš jus atgaivinsiu.
28እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።
29Imkite ant savęs mano jungą ir mokykitės iš manęs, nes Aš romus ir nuolankios širdies, ir jūs rasite savo sieloms atgaivą.
29ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤
30Nes mano jungas švelnus ir mano našta lengva”.
30ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና።