1Anuo metu sabato dieną Jėzus ėjo per javų lauką. Jo mokiniai buvo išalkę, tad skynė varpas ir valgė.
1በዚያን ጊዜ ኢየሱስ በሰንበት ቀን በእርሻ መካከል አለፈ፤ ደቀ መዛሙርቱም ተራቡና እሸት ይቀጥፉ ይበሉም ጀመር።
2Tai pamatę, fariziejai Jam sakė: “Žiūrėk, Tavo mokiniai daro, kas per sabatą draudžiama”.
2ፈሪሳውያንም አይተው። እነሆ፥ ደቀ መዛሙርትህ በሰንበት ማድረግ ያልተፈቀደውን ያደርጋሉ አሉት።
3Jis jiems atsakė: “Ar neskaitėte, ką darė Dovydas ir jo palydovai, būdami išalkę?
3እርሱ ግን እንዲህ አላቸው። ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩት በተራቡ ጊዜ፥ እርሱ ያደረገውን፥ ወደ እግዚአብሔር ቤት እንደ ገባ ካህናትም ብቻ እንጂ እርሱና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሊበሉት ያልተፈቀደውን የመሥዋዕቱን ኅብስት እንደ በላ አላነበባችሁምን?
4Kaip jie įėjo į Dievo namus ir valgė padėtinės duonos, nors nevalia buvo jos valgyti nei jam, nei jo palydovams, o vien tik kunigams.
5ካህናትም በሰንበት በመቅደስ ሰንበትን እንዲያረክሱ ኃጢአትም እንዳይሆንባቸው በሕጉ አላነበባችሁምን?
5Arba, ar neskaitėte Įstatyme, jog per sabatą kunigai šventykloje pažeidžia sabatą ir nenusikalsta?
6ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ከመቅደስ የሚበልጥ ከዚህ አለ።
6Bet sakau jums: čia daugiau negu šventykla!
7ምሕረትን እወዳለሁ መሥዋዕትንም አይደለም ያለው ምን እንደሆነ ብታውቁስ ኃጢአት የሌለባቸውን ባልኰነናችሁም ነበር።
7Jei būtumėte supratę, ką reiškia ‘Aš noriu gailestingumo, o ne aukos’, nebūtumėte pasmerkę nekaltų.
8የሰው ልጅ የሰንበት ጌታ ነውና።
8Žmogaus Sūnus yra ir sabato Viešpats”.
9ከዚያም አልፎ ወደ ምኩራባቸው ገባ።
9Iš ten išėjęs, Jis atėjo į jų sinagogą.
10እነሆም፥ እጁ የሰለለች ሰው ነበረ፤ ይከሱትም ዘንድ። በሰንበት መፈወስ ተፈቅዶአልን? ብለው ጠየቁት።
10Ir štai ten buvo žmogus padžiūvusia ranka. Jie paklausė Jėzų (kad galėtų apkaltinti): “Ar leistina sabato dieną gydyti?”
11እርሱ ግን። ከእናንተ አንድ በግ ያለው በሰንበት በጉድጓድ ቢወድቅበት፥ ይዞ የማያወጣው ሰው ማን ነው?
11Jis jiems atsakė: “Kas iš jūsų, turėdamas vieną avį, jeigu ji per sabatą įkris į duobę, nestvers ir neištrauks?
12እንግዲህ ሰው ከበግ ይልቅ እንደምን አይበልጥም! ስለዚህ በሰንበት መልካም መሥራት ተፈቅዶአል አላቸው።
12O kaip daug brangesnis už avį žmogus! Todėl leistina daryti gera sabato dieną”.
13ከዚያም በኋላ ሰውየውን። እጅህን ዘርጋ አለው። ዘረጋትም፥ እንደ ሁለተኛይቱም ደህና ሆነች።
13Tada Jis tarė žmogui: “Ištiesk ranką!” Tas ištiesė, ir ji tapo sveika kaip ir antroji.
14ፈሪሳውያን ግን ወጥተው እንዴት አድርገው እንዲያጠፉት ተማከሩበት።
14Tuomet išėję fariziejai tarėsi, kaip Jėzų pražudyti.
15ኢየሱስም አውቆ ከዚያ ፈቀቅ አለ። ብዙ ሰዎችም ተከተሉት፥ ሁሉንም ፈወሳቸው፥ እንዳይገልጡትም አዘዛቸው፤
15Tai sužinojęs, Jėzus pasitraukė iš ten. Didelės minios sekė paskui Jį, ir Jis visus išgydė,
16በነቢዩ በኢሳይያስ የተባለው ይፈጸም ዘንድ እንዲህ ሲል።
16bet įspėjo, kad Jo negarsintų.
18እነሆ የመረጥሁት ብላቴናዬ፥ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ወዳጄ፤ መንፈሴን በእርሱ ላይ አኖራለሁ፥ ፍርድንም ለአሕዛብ ያወራል።
17Kad išsipildytų, kas buvo pasakyta per pranašą Izaiją:
19አይከራከርም አይጮህምም፥ ድምፁንም በአደባባይ የሚሰማ የለም።
18“Štai mano išrinktasis tarnas, mano mylimasis, kuriuo gėrisi mano siela. Aš duosiu Jam savo Dvasią, ir Jis skelbs pagonims teisingumą.
20ፍርድን ድል ለመንሣት እስኪያወጣ፥ የተቀጠቀጠን ሸምበቆ አይሰብርም የሚጤስን የጥዋፍ ክርም አያጠፋም።
19Jis nesiginčys, nešauks, ir niekas gatvėje negirdės Jo balso.
21አሕዛብም በስሙ ተስፋ ያደርጋሉ።
20Jis nenulauš palūžusios nendrės ir neužgesins rusenančio dagčio, kol nenuves teisingumo į pergalę;
22ከዚህም በኋላ ጋኔን ያደረበትን ዕውር ዲዳም ወደ እርሱ አመጡ፤ ዕውሩም ዲዳውም እስኪያይና እስኪናገር ድረስ ፈወሰው።
21o Jo vardas teiks viltį pagonims!”
23ሕዝቡም ሁሉ ተገረሙና። እንጃ ይህ ሰው የዳዊት ልጅ ይሆንን? አሉ።
22Tuomet atvedė pas Jį demono apsėstąjį, kuris buvo aklas ir nebylys. Jėzus išgydė jį, ir šis prakalbo ir praregėjo.
24ፈሪሳውያን ግን ሰምተው። ይህ በብዔል ዜቡል በአጋንንት አለቃ ካልሆነ በቀር አጋንንትን አያወጣም አሉ።
23Ištisos minios netvėrė iš nuostabos ir klausinėjo: “Ar nebus šitas Dovydo Sūnus?!”
25ኢየሱስ ግን አሳባቸውን አውቆ እንዲህ አላቸው። እርስ በርስዋ የምትለያይ መንግሥት ሁላ ትጠፋለች፥ እርስ በርሱ የሚለያይ ከተማም ሁሉ ወይም ቤት አይቆምም።
24Tai išgirdę, fariziejai sakė: “Jis išvaro demonus ne kitaip, kaip tik demonų valdovo Belzebulo jėga”.
26ሰይጣንም ሰይጣንን የሚያወጣ ከሆነ፥ እርስ በርሱ ተለያየ፥ እንግዲህ መንግሥቱ እንዴት ትቆማለች?
25Žinodamas jų mintis, Jėzus tarė: “Kiekviena suskilusi karalystė bus nusiaubta, ir joks suskilęs miestas ir namas neišsilaikys.
27እኔስ በብዔል ዜቡል አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ፥ ልጆቻችሁ በማን ያወጡአቸዋል? ስለዚህ እነርሱ ፈራጆች ይሆኑባችኋል።
26Jeigu tad šėtonas išvarinėtų šėtoną, irgi būtų savyje susiskaldęs. Kaipgi tada galėtų išsilaikyti jo karalystė?
28እኔ ግን በእግዚአብሔር መንፈስ አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ፥ እንግዲህ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ ደርሳለች።
27Ir jeigu Aš išvarau demonus Belzebulo jėga, tai kieno jėga išvaro jūsų sūnūs? Todėl jie bus jūsų teisėjai.
29ወይስ ሰው አስቀድሞ ኃይለኛውን ሳያስር ወደ ኃይለኛው ቤት ገብቶ እቃውን ሊነጥቀው እንዴት ይችላል? ከዚያም ወዲያ ቤቱን ይበዘብዛል።
28Bet jeigu Aš išvarau demonus Dievo Dvasia, tai tikrai pas jus atėjo Dievo karalystė.
30ከእኔ ጋር ያልሆነ ይቃወመኛል፥ ከእኔ ጋርም የማያከማች ይበትናል።
29Argi gali kas nors įeiti į galiūno namus ir pasigrobti jo turtą, pirmiau nesurišęs galiūno? Tik tada jis apiplėš jo namus.
31ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ኃጢአትና ስድብ ሁሉ ለሰዎች ይሰረይላቸዋል፥ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን ለሰደበ አይሰረይለትም።
30Kas ne su manimi, tas prieš mane, ir kas su manimi nerenka, tas barsto”.
32በሰው ልጅ ላይ ቃል የሚናገር ሁሉ ይሰረይለታል፤ በመንፈስ ቅዱስ ላይ ግን የሚናገር ሁሉ በዚህ ዓለም ቢሆን ወይም በሚመጣው አይሰረይለትም።
31“Sakau jums: kiekviena nuodėmė ir piktžodžiavimas bus žmonėms atleisti, bet piktžodžiavimas Dvasiai nebus jiems atleistas.
33ዛፍ ከፍሬዋ ትታወቃለችና ዛፍዋን መልካም፥ ፍሬዋንም መልካም አድርጉ፥ ወይም ዛፍዋን ክፉ ፍሬዋንም ክፉ አድርጉ።
32Jei kas tartų žodį prieš Žmogaus Sūnų, tam bus atleista, o kas kalbėtų prieš Šventąją Dvasią, tam nebus atleista nei šiame, nei būsimajame amžiuje.
34እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ክፉዎች ስትሆኑ መልካም ለመናገር እንዴት ትችላላችሁ? በልብ ሞልቶ ከተረፈው አፍ ይናገራልና።
33Arba sakykite medį esant gerą ir jo vaisių gerą, arba sakykite medį esant blogą ir jo vaisių blogą, nes medis pažįstamas iš vaisių.
35መልካም ሰው ከልቡ መልካም መዝገብ መልካም ነገርን ያወጣል፥ ክፉ ሰውም ከክፉ መዝገብ ክፉ ነገርን ያወጣል።
34Angių išperos, kaip jūs galite kalbėti gera, būdami blogi?! Juk lūpos kalba tai, ko pertekusi širdis.
36እኔ እላችኋለሁ፥ ሰዎች ስለሚናገሩት ስለ ከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ ቀን መልስ ይሰጡበታል፤
35Geras žmogus iš gero širdies lobyno iškelia gera, o blogas iš blogo lobyno iškelia bloga.
37ከቃልህ የተነሣ ትጸድቃለህና ከቃልህም የተነሣ ትኰነናለህ።
36Todėl sakau jums: teismo dieną žmonės turės duoti apyskaitą už kiekvieną pasakytą tuščią žodį.
38በዚያን ጊዜ ከጻፎችና ከፈሪሳውያን አንዳንዶቹ መለሱና። መምህር ሆይ፥ ከአንተ ምልክት እንድናይ እንወዳለን አሉ።
37Pagal savo žodžius būsi išteisintas ir pagal savo žodžius būsi pasmerktas”.
39እርሱ ግን መልሶ እንዲህ አላቸው። ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል፥ ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም።
38Tada kai kurie Rašto žinovai ir fariziejai sakė: “Mokytojau, norime, kad parodytum ženklą”.
40ዮናስ በዓሣ አንባሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ፥ እንዲሁ የሰው ልጅ በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል።
39Jis jiems atsakė: “Pikta ir svetimaujanti karta ieško ženklo, bet nebus jai duota kito ženklo, kaip tik pranašo Jonos ženklas.
41የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥተው ይፈርዱበታል፤ በዮናስ ስብከት ንስሐ ገብተዋልና፥ እነሆም፥ ከዮናስ የሚበልጥ ከዚህ አለ።
40Kaip Jona išbuvo tris dienas ir tris naktis banginio pilve, taip ir Žmogaus Sūnus išbus tris dienas ir tris naktis žemės širdyje.
42ንግሥተ ዓዜብ በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥታ ትፈርድበታለች፤ የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳር መጥታለችና፥ እነሆም፥ ከሰሎሞን የሚበልጥ ከዚህ አለ።
41Ninevės žmonės teismo dieną prisikels drauge su šia karta ir ją pasmerks, nes jie atgailavo, išgirdę Jonos pamokslą, o štai čia daugiau negu Jona.
43ርኩስ መንፈስ ግን ከሰው በወጣ ጊዜ፥ ዕረፍት እየፈለገ ውኃ በሌለበት ቦታ ያልፋል፥ አያገኝምም።
42Pietų šalies karalienė teismo dieną prisikels drauge su šia karta ir ją pasmerks, nes ji atkeliavo nuo žemės pakraščių pasiklausyti Saliamono išminties, o štai čia daugiau negu Saliamonas”.
44በዚያን ጊዜም። ወደ ወጣሁበት ቤቴ እመለሳለሁ ይላል፤ ቢመጣም ባዶ ሆኖ ተጠርጎና አጊጦ ያገኘዋል።
43“Netyroji dvasia, išėjusi iš žmogaus, klaidžioja bevandenėse vietose, ieškodama poilsio, ir neranda.
45ከዚያ ወዲያ ይሄድና ከእርሱ የከፉትን ሰባት ሌሎችን አጋንንት ከእርሱ ጋር ይወስዳል፥ ገብተውም በዚያ ይኖራሉ፤ ለዚያም ሰው ከፊተኛው ይልቅ የኋለኛው ይብስበታል። ለዚህ ክፉ ትውልድ ደግሞ እንዲሁ ይሆንበታል።
44Tada ji sako: ‘Grįšiu į savo namus, iš kur išėjau’. Sugrįžusi randa juos tuščius, iššluotus ir išpuoštus.
46ገናም ለሕዝቡ ሲናገር፥ እነሆ፥ እናቱና ወንድሞቹ ሊነጋገሩት ፈልገው በውጭ ቆመው ነበር።
45Tada eina, pasiima kitas septynias dvasias, dar piktesnes už save, ir įėjusios jos ten apsigyvena. Ir paskui tam žmogui darosi blogiau negu pirma. Taip atsitiks ir šiai piktai kartai”.
47አንዱም። እነሆ፥ እናትህና ወንድሞችህ ሊነጋገሩህ ፈልገው በውጭ ቆመዋል አለው።
46Jam tebekalbant minioms, štai Jo motina ir broliai stovėjo lauke ir norėjo su Juo pasikalbėti.
48እርሱ ግን ለነገረው መልሶ። እናቴ ማን ናት? ወንድሞቼስ እነማን ናቸው? አለው።
47Tada kažkas pranešė Jam: “Štai Tavo motina ir broliai stovi lauke ir nori su Tavim pasikalbėti”.
49እጁንም ወደ ደቀ መዛሙርቱ ዘርግቶ። እነሆ እናቴና ወንድሞቼ፤
48Jis atsakė pranešusiam: “Kas yra mano motina ir kas yra mano broliai?”
50በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ፥ እርሱ ወንድሜ እኅቴም እናቴም ነውና አለ።
49Ir, ištiesęs ranką į savo mokinius, tarė: “Štai mano motina ir mano broliai!
50Kiekvienas, kas vykdo mano dangiškojo Tėvo valią, yra mano brolis, ir sesuo, ir motina”.