Lithuanian

Amharic: New Testament

Matthew

20

1“Su dangaus karalyste yra panašiai, kaip su šeimininku, kuris anksti rytą išėjo samdytis darbininkų savo vynuogynui.
1መንግሥተ ሰማያት ለወይኑ አትክልት ሠራተኞችን ሊቀጥር ማልዶ የወጣ ባለቤት ሰውን ትመስላለችና።
2Susiderėjęs su darbininkais po denarą dienai, jis nusiuntė juos į savo vynuogyną.
2ሠራተኞችንም በቀን አንድ ዲናር ተስማምቶ ወደ ወይኑ አትክልት ሰደዳቸው።
3Išėjęs apie trečią valandą, jis pamatė kitus, stovinčius aikštėje be darbo.
3በሦስት ሰዓትም ወጥቶ ሥራ የፈቱ ሌሎችን በአደባባይ ቆመው አየ፥
4Jis tarė jiems: ‘Eikite ir jūs į mano vynuogyną, ir, kas bus teisinga, aš jums užmokėsiu!’ Jie nuėjo.
4እነዚያንም። እናንተ ደግሞ ወደ ወይኔ አትክልት ሂዱ የሚገባውንም እሰጣችኋለሁ አላቸው። እነርሱም ሄዱ።
5Ir vėl išėjęs apie šeštą ir devintą valandą, jis taip pat padarė.
5ደግሞም በስድስትና በዘጠኝ ሰዓት ወጥቶ እንዲሁ አደረገ።
6Išėjęs apie vienuoliktą, jis rado dar kitus stovinčius be darbo ir sako jiems: ‘Ko čia stovite visą dieną be darbo?’
6በአሥራ አንደኛውም ሰዓት ወጥቶ ሌሎችን ቆመው አገኘና። ሥራ ፈትታችሁ ቀኑን ሁሉ በዚህ ስለ ምን ትቆማላችሁ? አላቸው።
7Jie atsakė: ‘Kad niekas mūsų nepasamdė’. Jis tarė jiems: ‘Eikite ir jūs į vynuogyną, ir, kas bus teisinga, jūs gausite’.
7የሚቀጥረን ስለ አጣን ነው አሉት። እርሱም። እናንተ ደግሞ ወደ ወይኔ አትክልት ሂዱ የሚገባውንም ትቀበላላችሁ አላቸው።
8Atėjus vakarui, vynuogyno šeimininkas liepė ūkvedžiui: ‘Pašauk darbininkus ir išmokėk jiems atlyginimą, pradėdamas nuo paskutiniųjų ir baigdamas pirmaisiais!’
8በመሸም ጊዜ የወይኑ አትክልት ጌታ አዛዡን። ሠራተኞችን ጥራና ከኋለኞች ጀምረህ እስከ ፊተኞች ድረስ ደመወዝ ስጣቸው አለው።
9Atėję pasamdytieji apie vienuoliktą valandą kiekvienas gavo po denarą.
9በአሥራ አንደኛው ሰዓትም የገቡ መጥተው እያንዳንዳቸው አንድ ዲናር ተቀበሉ።
10Prisiartinę pirmieji manė daugiau gausią, bet irgi gavo po denarą.
10ፊተኞችም በመጡ ጊዜ አብዝተው የሚቀበሉ መስሎአቸው ነበር፤ እነርሱም ደግሞ እያንዳንዳቸው አንድ ዲናር ተቀበሉ።
11Paėmę jie murmėjo prieš šeimininką,
11ተቀብለውም። እነዚህ ኋለኞች አንድ ሰዓት ሠሩ፥ የቀኑንም ድካምና ትኩሳት ከተሸከምን ከእኛ ጋር አስተካከልሃቸው ብለው በባለቤቱ ላይ አንጐራጐሩ።
12sakydami: ‘Šitie paskutinieji tedirbo vieną valandą, o tu sulyginai juos su mumis, nešusiais dienos ir kaitros naštą’.
13እርሱ ግን መልሶ ከእነርሱ ለአንዱ እንዲህ አለው። ወዳጄ ሆይ፥ አልበደልሁህም በአንድ ዲናር አልተስማማኸኝምን?
13Bet jis vienam iš jų atsakė: ‘Bičiuli, aš tavęs neskriaudžiu! Argi ne už denarą susiderėjai su manimi?
14ድርሻህን ውሰድና ሂድ፤ እኔ ለዚህ ለኋለኛው እንደ አንተ ልሰጠው እወዳለሁ፤ በገንዘቤ የወደድሁትን አደርግ ዘንድ መብት የለኝምን?
14Imk, kas tavo, ir eik sau. Aš noriu ir šitam paskutiniam duoti tiek, kiek tau.
15ወይስ እኔ መልካም ስለ ሆንሁ ዓይንህ ምቀኛ ናትን?
15Argi aš neturiu teisės daryti ką noriu su tuo, kas mano? Ar todėl tavo akis pikta, kad aš geras?’
16እንዲሁ ኋለኞች ፊተኞች፥ ፊተኞችም ኋለኞች ይሆናሉ፤ የተጠሩ ብዙዎች፥ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸውና።
16Taip paskutinieji bus pirmi, o pirmieji­paskutiniai; nes daug yra pašauktų, bet maža išrinktų”.
17ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ሊወጣ ሳለ፥ በመንገድ አሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርት ብቻቸውን ወደ እርሱ አቅርቦ።
17Išvykdamas į Jeruzalę, Jėzus pasiėmė skyrium dvylika mokinių ir kelyje kalbėjo jiems:
18እነሆ፥ ወደ ኢየሩሳሌም እንወጣለን፥ የሰው ልጅም ለካህናት አለቆችና ለጻፎች ይሰጣል፤ የሞት ፍርድም ይፈርዱበታል፥
18“Štai einame į Jeruzalę, ir Žmogaus Sūnus bus išduotas aukštiesiems kunigams bei Rašto žinovams. Jie nuteis Jį mirti,
19ሊዘባበቱበትም ሊገርፉትም ሊሰቅሉትም ለአሕዛብ አሳልፈው ይሰጡታል፥ በሦስተኛውም ቀን ይነሣል አላቸው።
19atiduos pagonims tyčiotis, nuplakti ir nukryžiuoti, ir trečią dieną Jis prisikels”.
20በዚያን ጊዜ የዘብዴዎስ ልጆች እናት ከልጆችዋ ጋር እየሰገደችና አንድ ነገር እየለመነች ወደ እርሱ ቀረበች።
20Tada prie Jėzaus priėjo Zebediejaus sūnų motina kartu su savo sūnumis ir, pagarbinusi Jį, ėmė kažko prašyti.
21እርሱም። ምን ትፈልጊያለሽ? አላት። እርስዋም። እነዚህ ሁለቱ ልጆቼ አንዱ በቀኝህ አንዱም በግራህ በመንግሥትህ እንዲቀመጡ እዘዝ አለችው።
21Jis paklausė jos: “Ko nori?” Toji atsakė: “Leisk, kad šitie abu mano sūnūs Tavo karalystėje sėdėtų vienas Tavo dešinėje, o kitas kairėje”.
22ኢየሱስ ግን መልሶ። የምትለምኑትን አታውቁም። እኔ ልጠጣው ያለውን ጽዋ ልትጠጡ እኔም የምጠመቀውን ጥምቀት ልትጠመቁ ትችላላችሁን? አለ። እንችላለን አሉት።
22Jėzus atsakė: “Nežinote, ko prašote. Ar galite gerti taurę, kurią Aš gersiu, ir būti krikštijami krikštu, kuriuo Aš krikštijamas?” Jie atsakė: “Galime”.
23እርሱም። ጽዋዬንስ ትጠጣላችሁ፤ በቀኝና በግራ መቀመጥ ግን ከአባቴ ዘንድ ለተዘጋጀላቸው ነው እንጂ እኔ የምሰጥ አይደለሁም አላቸው።
23Tuomet Jis tarė: “Mano taurę, tiesa, gersite, ir krikštu, kuriuo Aš krikštijamas, būsite pakrikštyti, bet vietą mano dešinėje ar kairėje ne Aš duodu; tai bus tiems, kuriems mano Tėvo paruošta”.
24አሥሩም ሰምተው በሁለቱ ወንድማማች ተቈጡ።
24Tai išgirdę, kiti dešimt mokinių supyko ant dviejų brolių.
25ኢየሱስ ግን ወደ እርሱ ጠርቶ እንዲህ አላቸው። የአሕዛብ አለቆች እንዲገዙአቸው ታላላቆቹም በላያቸው እንዲሠለጥኑ ታውቃላችሁ።
25O Jėzus, pasikvietęs juos pas save, tarė: “Jūs žinote, kad pagonių valdovai jiems viešpatauja ir didieji juos valdo.
26በእናንተስ እንዲህ አይደለም፤ ነገር ግን ማንም ከእናንተ ታላቅ ሊሆን የሚወድ የእናንተ አገልጋይ ይሁን፥
26Bet tarp jūsų taip neturi būti. Kas iš jūsų nori būti didžiausias, tebūnie jūsų tarnas,
27ከእናንተም ማንም ፊተኛ ሊሆን የሚወድ የእናንተ ባሪያ ይሁን፤
27ir kas nori būti pirmas tarp jūsų, tebūnie jūsų vergas.
28እንዲሁም የሰው ልጅ ሊያገለግል ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።
28Ir Žmogaus Sūnus atėjo, ne kad Jam tarnautų, bet pats tarnauti ir savo gyvybės atiduoti kaip išpirkos už daugelį”.
29ከኢያሪኮም ሲወጡ ብዙ ሕዝብ ተከተሉት።
29Jiems išeinant iš Jericho, paskui Jį sekė didelė minia.
30እነሆም፥ ሁለት ዕውሮች በመንገድ ዳር ተቀምጠው፥ ኢየሱስ እንዲያልፍ በሰሙ ጊዜ። ጌታ ሆይ፥ የዳዊት ልጅ፥ ማረን ብለው ጮኹ።
30Ir štai pakelėje sėdėjo du neregiai. Išgirdę praeinantį Jėzų, jie ėmė šaukti: “Viešpatie, Dovydo Sūnau, pasigailėk mūsų!”
31ሕዝቡም ዝም እንዲሉ ገሠጹአቸው፤ እነርሱ ግን። ጌታ ሆይ፥ የዳዊት ልጅ፥ ማረን እያሉ አብዝተው ጮኹ።
31Minia draudė juos, kad tylėtų, bet anie dar garsiau šaukė: “Viešpatie, Dovydo Sūnau, pasigailėk mūsų!”
32ኢየሱስም ቆሞ ጠራቸውና። ምን ላደርግላችሁ ትወዳላችሁ? አለ።
32Jėzus sustojo, pašaukė juos ir paklausė: “Ko norite, kad jums padaryčiau?”
33ጌታ ሆይ፥ ዓይኖቻችን ይከፈቱ ዘንድ አሉት።
33Neregiai Jam atsakė: “Viešpatie, kad atsivertų mūsų akys”.
34ኢየሱስም አዘነላቸውና ዓይኖቻቸውን ዳሰሰ፥ ወዲያውም አዩና ተከተሉት።
34Pasigailėjęs Jėzus palietė jų akis; jie tučtuojau praregėjo ir nusekė paskui Jį.