1Kai jie prisiartino prie Jeruzalės ir atėjo į Betfagę prie Alyvų kalno, Jėzus pasiuntė du mokinius,
1ወደ ኢየሩሳሌምም ቀርበው ወደ ደብረ ዘይት ወደ ቤተ ፋጌ ሲደርሱ፥ ያንጊዜ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለት ላከ፥
2liepdamas: “Eikite į priešais esantį kaimą ir tuojau rasite pririštą asilę su asilaičiu. Atriškite ir atveskite juos man.
2እንዲህም አላቸው። በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ፥ በዚያን ጊዜም የታሰረችን አህያ ውርንጫም ከእርስዋ ጋር ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁ አምጡልኝ።
3O jeigu kas imtų dėl to teirautis, atsakykite: ‘Jų reikia Viešpačiui’, ir iš karto juos paleis”.
3ማንም አንዳች ቢላችሁ። ለጌታ ያስፈልጉታል በሉ፤ ወዲያውም ይሰዳቸዋል።
4Tai įvyko, kad išsipildytų, kas per pranašą buvo pasakyta:
4ለጽዮን ልጅ። እነሆ፥ ንጉሥሽ የዋህ ሆኖ በአህያ ላይና በአህያይቱ ግልገል በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል በሉአት ተብሎ በነቢይ የተነገረው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሆነ።
5“Sakykite Siono dukrai: štai atkeliauja tavo karalius, romus, ir joja ant asilės, lydimas asilaičio, darbinio gyvulio jauniklio”.
6ደቀ መዛሙርቱም ሄደው ኢየሱስ እንዳዘዛቸው አደረጉ፥
6Mokiniai nuėjo ir padarė, kaip Jėzus jiems įsakė.
7አህያይቱንና ውርንጫዋንም አመጡለት፥ ልብሳቸውንም በእነርሱ ላይ ጫኑ፥ ተቀመጠባቸውም።
7Jie atvedė asilę su asilaičiu, apdengė juos savo apsiaustais, ir Jis užsėdo ant viršaus.
8ከሕዝቡም እጅግ ብዙዎች ልብሳቸውን በመንገድ ላይ አነጠፉ፥ ሌሎችም ከዛፍ ጫፍ ጫፉን እየቈረጡ በመንገድ ላይ ያነጥፉ ነበር።
8Didžiulė minia tiesė drabužius ant kelio. Kiti kirto ir klojo ant kelio medžių šakas.
9የሚቀድሙትም ሕዝብ የሚከተሉትም። ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር።
9Iš priekio ir iš paskos einančios minios šaukė: “Osana Dovydo Sūnui! Palaimintas, kuris ateina Viešpaties vardu! Osana aukštybėse!”
10ወደ ኢየሩሳሌምም በገባ ጊዜ መላው ከተማ። ይህ ማን ነው? ብሎ ተናወጠ።
10Jam įėjus į Jeruzalę, sujudo visas miestas ir klausinėjo: “Kas yra šitas?”
11ሕዝቡም። ይህ ከገሊላ ናዝሬት የመጣ ነቢዩ ኢየሱስ ነው አሉ።
11O minios kalbėjo: “Tai pranašas Jėzus iš Galilėjos Nazareto”.
12ኢየሱስም ወደ መቅደስ ገባና በመቅደስ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ሁሉ አወጣ፥ የገንዘብ ለዋጮችንም ገበታዎች የርግብ ሻጮችንም ወንበሮች ገለበጠና።
12Įėjęs į Dievo šventyklą, Jėzus išvarė visus parduodančius ir perkančius šventykloje, išvartė pinigų keitėjų stalus bei karvelių pardavėjų suolus
13ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች ተብሎ ተጽፎአል፥ እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት አላቸው።
13ir tarė jiems: “Parašyta: ‘Mano namai vadinsis maldos namai’, o jūs pavertėte juos ‘plėšikų lindyne!’ ”
14በመቅደስም ዕውሮችና አንካሶች ወደ እርሱ ቀረቡና ፈወሳቸው።
14Šventykloje prie Jo susirinko aklų ir luošų, ir Jis išgydė juos.
15ነገር ግን የካህናት አለቆችና ጻፎች ያደረገውን ድንቃ ድንቅ በመቅደስም። ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ እያሉ የሚጮኹትን ልጆች ባዩ ጊዜ፥ ተቈጥተው።
15O aukštieji kunigai ir Rašto žinovai, pamatę stebuklus, kuriuos Jis padarė, ir vaikus, šaukiančius šventykloje: “Osana Dovydo Sūnui!”, įpyko
16እነዚህ የሚሉትን አትሰማምን? አሉት። ኢየሱስም። እሰማለሁ፤ ከሕፃናትና ከሚጠቡት አፍ ምስጋናን ለራስህ አዘጋጀህ የሚለውን ቃል ከቶ አላነበባችሁምን? አላቸው።
16ir sakė Jam: “Ar girdi, ką jie sako?” Jėzus atsiliepė: “Girdžiu. Argi niekada neskaitėte: ‘Iš vaikų ir žindomų kūdikių lūpų Tu paruošei sau tobulą gyrių’?”
17ትቶአቸውም ከከተማ ወደ ቢታንያ ወጣ በዚያም አደረ።
17Ir, palikęs juos, Jis išėjo iš miesto į Betaniją ir ten apsinakvojo.
18በማለዳም ወደ ከተማ ሲመለስ ተራበ።
18Rytą, grįždamas į miestą, Jis išalko.
19በመንገድም አጠገብ በለስ አይቶ ወደ እርስዋ መጣ፤ ከቅጠልም ብቻ በቀር ምንም አላገኘባትምና። ለዘላለሙ ፍሬ አይገኝብሽ አላት። በለሲቱም ያንጊዜውን ደረቀች።
19Pamatęs pakelėje figmedį, priėjo prie jo, bet nieko nerado, vien tik lapus. Ir tarė jam: “Tegul per amžius ant tavęs neaugs vaisiai!” Ir figmedis kaipmat nudžiūvo.
20ደቀ መዛሙርቱም ይህን አይተው። በለሲቱ ያንጊዜውን እንዴት ደረቀች? ብለው ተደነቁ።
20Tai pamatę, mokiniai nustebo ir sakė: “Kaip tas figmedis taip greit nudžiūvo?!”
21ኢየሱስም መልሶ። እውነት እላችኋለሁ፥ እምነት ቢኖራችሁ ባትጠራጠሩም፥ በበለሲቱ እንደ ሆነባት ብቻ አታደርጉም፤ ነገር ግን ይህን ተራራ እንኳ። ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ብትሉት ይሆናል፤
21Jėzus atsakė: “Iš tiesų sakau jums: jeigu turėsite tikėjimą ir neabejosite, jūs ne tik padarysite taip su figmedžiu, bet ir jei pasakysite šitam kalnui: ‘Pasikelk ir meskis į jūrą!’, taip įvyks.
22አምናችሁም በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ ትቀበላላችሁ አላቸው።
22Ir visa, ko tik prašysite maldoje tikėdami,gausite”.
23ወደ መቅደስም ገብቶ ሲያስተምር የካህናት አለቆችና የሕዝብ ሽማግሎች ወደ እርሱ ቀረቡና። በምን ሥልጣን እነዚህን ታደርጋለህ? ይህንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ? አሉት።
23Kai Jėzus atėjo į šventyklą ir pradėjo mokyti, priėjo prie Jo aukštųjų kunigų ir tautos vyresniųjų, kurie klausė: “Kokią teisę turi taip daryti? Ir kas Tau davė šitą valdžią?”
24ኢየሱስም መልሶ። እኔ ደግሞ አንዲት ነገር እጠይቃችኋለሁ፤ እናንተም ያችን ብትነግሩኝ እኔ ደግሞ እነዚህን በምን ሥልጣን እንዳደርግ እነግራችኋለሁ፤
24Jėzus atsakė: “Aš irgi paklausiu jus vieno dalyko. Jei man atsakysite, ir Aš pasakysiu, kokia valdžia tai darau.
25የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነበረች? ከሰማይን ወይስ ከሰው? አላቸው። እነርሱም እርስ በርሳቸው ሲነጋገሩ። ከሰማይ ብንል። እንኪያስ ስለ ምን አላመናችሁበትም? ይለናል፤
25Iš kur buvo Jono krikštas? Iš dangaus ar iš žmonių?” Jie samprotavo tarpusavy: “Jei pasakysimeiš dangaus, Jis mums sakys: ‘Tai kodėl juo netikėjote?’
26ከሰው ግን ብንል፥ ዮሐንስን ሁሉም እንደ ነቢይ ያዩታልና ሕዝቡን እንፈራለን አሉ።
26O pasakytiiš žmonių, baisu prieš minią, nes visi laiko Joną pranašu”.
27ለኢየሱስም መልሰው። አናውቅም አሉት። እርሱም ደግሞ። እኔም በምን ሥልጣን እነዚህን እንዳደርግ አልነግራችሁም አላቸው።
27Todėl jie atsakė Jėzui: “Mes nežinome”. Tada Jis tarė: “Tai ir Aš jums nesakysiu, kokia valdžia tai darau”.
28ነገር ግን ምን ይመስላችኋል? አንድ ሰው ሁለት ልጆች ነበሩት፤ ወደ አንደኛው ቀርቦ። ልጄ ሆይ፥ ዛሬ ሂድና በወይኔ አትክልት ሥራ አለው።
28“Kaip jūs manote? Vienas žmogus turėjo du sūnus. Kartą, priėjęs prie pirmojo, tarė: ‘Sūnau, eik ir padirbėk šiandien mano vynuogyne’.
29እርሱም መልሶ። አልወድም አለ፤ ኋላ ግን ተጸጸተና ሄደ።
29Šis atsakė: ‘Nenoriu’, bet vėliau apsigalvojo ir nuėjo.
30ወደ ሁለተኛውም ቀርቦ እንዲሁ አለው እርሱም መልሶ። እሺ ጌታዬ አለ፤ ነገር ግን አልሄደም።
30Paskui tėvas kreipėsi į antrąjį sūnų tais pačiais žodžais. Šis jam atsakė: ‘Einu, viešpatie’, bet nenuėjo.
31ከሁለቱ የአባቱን ፈቃድ ያደረገ ማን ነው? ፊተኛው አሉት። ኢየሱስ እንዲህ አላቸው። እውነት እላችኋለሁ፥ ቀራጮችና ጋለሞቶች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በመግባት ይቀድሙአችኋል።
31Kuris iš jų įvykdė tėvo valią?” Jie atsakė: “Pirmasis”. Tada Jėzus jiems tarė: “Iš tiesų sakau jums: muitininkai ir paleistuvės pirma jūsų eina į Dievo karalystę.
32ዮሐንስ በጽድቅ መንገድ መጥቶላችሁ ነበርና፥ አላመናችሁበትም፤ ቀራጮችና ጋለሞቶች ግን አመኑበት፤ እናንተም ይህን አይታችሁ ታምኑበት ዘንድ በኋላ ንስሐ አልገባችሁም።
32Nes Jonas atėjo pas jus teisumo keliu, bet jūs netikėjote juo. O muitininkai ir paleistuvės juo tikėjo. Bet jūs, tai matydami, nė vėliau neatgailavote ir netikėjote juo”.
33ሌላ ምሳሌ ስሙ። የወይን አትክልት የተከለ ባለቤት ሰው ነበረ፤ ቅጥርም ቀጠረለት፥ መጥመቂያም ማሰለት፥ ግንብም ሠራና ለገበሬዎች አከራይቶ ወደ ሌላ አገር ሄደ።
33“Pasiklausykite kito palyginimo. Buvo vienas šeimininkas, kuris pasodino vynuogyną, aptvėrė jį tvora, įrengė spaustuvą, pastatė bokštą, išnuomojo vynininkams ir iškeliavo į tolimą šalį.
34የሚያፈራበትም ጊዜ ሲቀርብ፥ ፍሬውን ሊቀበሉ ባሮቹን ወደ ገበሬዎች ላከ።
34Atėjus vaisių metui, jis nusiuntė savo tarnus pas vynininkus atsiimti savo vaisių.
35ገበሬዎቹም ባሮቹን ይዘው አንዱን ደበደቡት አንዱንም ገደሉት ሌላውንም ወገሩት።
35Bet vynininkai, nutvėrę jo tarnus, vieną primušė, kitą nužudė, o trečią užmėtė akmenimis.
36ደግሞ ከፊተኞች የሚበዙ ሌሎች ባሮችን ላከ፥ እንዲሁም አደረጉባቸው።
36Jis vėl nusiuntė tarnų, daugiau negu pirma. Bet vynininkai ir su šitais pasielgė kaip su anais.
37በኋላ ግን። ልጄንስ ያፍሩታል ብሎ ልጁን ላከባቸው።
37Galiausiai jis išsiuntė pas juos savo sūnų, sakydamas: ‘Jie gerbs mano sūnų’.
38ገበሬዎቹ ግን ልጁን ባዩ ጊዜ እርስ በርሳቸው። ወራሹ ይህ ነው፤ ኑ፥ እንግደለውና ርስቱን እናግኝ ተባባሉ።
38Tačiau vynininkai, išvydę sūnų, ėmė kalbėtis: ‘Tai paveldėtojas! Eime, užmuškime jį ir pagrobkime palikimą’.
39ይዘውም ከወይኑ አትክልት አወጡና ገደሉት።
39Nutvėrę jie išmetė jį iš vynuogyno ir užmušė.
40እንግዲህ የወይኑ አትክልት ጌታ በሚመጣ ጊዜ በእነዚህ ገበሬዎች ምን ያደርግባቸዋል?
40Tad ką gi atvykęs vynuogyno šeimininkas padarys su tais vynininkais?”
41እነርሱም። ክፉዎችን በክፉ ያጠፋቸዋል፥ የወይኑንም አትክልት ፍሬውን በየጊዜው ለሚያስረክቡ ለሌሎች ገበሬዎች ይሰጠዋል አሉት።
41Jie atsakė Jam: “Jis žiauriai nužudys piktadarius ir išnuomos vynuogyną kitiems vynininkams, kurie, atėjus metui, atiduos vaisių”.
42ኢየሱስ እንዲህ አላቸው። ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ፤ ይህም ከጌታ ዘንድ ሆነ፥ ለዓይኖቻችንም ድንቅ ነው የሚለውን ከቶ በመጽሐፍ አላነበባችሁምን?
42Jėzus jiems tarė: “Ar niekada neskaitėte Raštuose: ‘Akmuo, kurį statytojai atmetė, tapo kertiniu akmeniu. Tai Viešpaties padaryta ir nuostabu mūsų akyse’.
43ስለዚህ እላችኋለሁ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት ከእናንተ ትወሰዳለች ፍሬዋንም ለሚያደርግ ሕዝብ ትሰጣለች።
43Todėl sakau jums: Dievo karalystė bus iš jūsų atimta ir duota tautai, kuri neš jos vaisių.
44በዚህም ድንጋይ ላይ የሚወድቅ ይቀጠቀጣል፤ ድንጋዩ ግን የሚወድቅበትን ሁሉ ይፈጨዋል።
44Kas kris ant to akmens, tas suduš, o ant ko tas akmuo užgrius, tą sutriuškins”.
45የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያንም ምሳሌዎቹን ሰምተው ስለ እነርሱ እንደ ተናገረ አስተዋሉ፤
45Išgirdę Jo palyginimus, aukštieji kunigai ir fariziejai suprato, kad Jis kalbėjo apie juos.
46ሊይዙትም ሲፈልጉት ሳሉ ሕዝቡ እንደ ነቢይ ስላዩት ፈሩአቸው።
46Jie stengėsi Jį suimti, tačiau bijojo minios, nes ji laikė Jį pranašu.