1Kai Jėzus leidosi nuo kalno, Jį sekė didelės minios.
1ከተራራም በወረደ ጊዜ ብዙ ሕዝብ ተከተሉት።
2Ir štai priėjo raupsuotasis ir, pagarbinęs Jį, sakė: “Viešpatie, jei nori, Tu gali mane padaryti švarų”.
2እነሆም፥ ለምጻም ቀርቦ። ጌታ ሆይ፥ ብትወድስ ልታነጻኝ ትችላለህ እያለ ሰገደለት።
3Jėzus ištiesė ranką, palietė jį ir tarė: “Noriu, būk švarus!” Ir tuojau raupsai išnyko.
3እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰውና። እወዳለሁ፥ ንጻ አለው። ወዲያውም ለምጹ ነጻ።
4Jėzus pasakė jam: “Žiūrėk, niekam nepasakok, bet eik pasirodyti kunigui ir paaukok Mozės įsakytą atnašą jiems paliudyti”.
4ኢየሱስም። ለማንም እንዳትናገር ተጠንቀቅ፥ ነገር ግን ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፥ ለእነርሱም ምስክር እንዲሆን ሙሴ ያዘዘውን መባ አቅርብ አለው።
5Jėzui sugrįžus į Kafarnaumą, prie Jo priėjo šimtininkas, maldaudamas:
5ወደ ቅፍርናሆምም በገባ ጊዜ የመቶ አለቃ ወደ እርሱ ቀርቦ። ጌታ ሆይ፥
6“Viešpatie, mano tarnas guli namie paralyžiuotas ir baisiai kankinasi”.
6ብላቴናዬ ሽባ ሆኖ እጅግ እየተሣቀየ በቤት ተኝቶአል ብሎ ለመነው።
7Jėzus jam tarė: “Einu ir išgydysiu jį”.
7ኢየሱስም። እኔ መጥቼ እፈውሰዋለሁ አለው።
8Šimtininkas atsakė: “Viešpatie, nesu vertas, kad užeitum po mano stogu, bet tik tark žodį, ir mano tarnas pasveiks.
8የመቶ አለቃውም መልሶ። ጌታ ሆይ፥ በቤቴ ጣራ ከታች ልትገባ አይገባኝም፤ ነገር ግን ቃል ብቻ ተናገር፥ ብላቴናዬም ይፈወሳል።
9Juk ir aš, būdamas valdinys, turiu sau pavaldžių kareivių. Sakau vienam: ‘Eik!’, ir jis eina; sakau kitam: ‘Ateik!’, ir jis ateina; sakau tarnui: ‘Daryk tai!’, ir jis daro”.
9እኔ ደግሞ ለሌሎች ተገዥ ነኝና፥ ከእኔም በታች ጭፍራ አለኝ፤ አንዱንም። ሂድ ብለው ይሄዳል፥ ሌላውንም። ና ብለው ይመጣል፥ ባሪያዬንም። ይህን አድርግ ብለው ያደርጋል አለው።
10Tai girdėdamas, Jėzus stebėjosi ir kalbėjo einantiems iš paskos: “Iš tiesų sakau jums: net Izraelyje neradau tokio tikėjimo!
10ኢየሱስም ሰምቶ ተደነቀና ለተከተሉት እንዲህ አለ። እውነት እላችኋለሁ፥ በእስራኤል እንኳ እንዲህ ያለ ትልቅ እምነት አላገኘሁም።
11Todėl sakau jums: daugelis ateis iš rytų ir vakarų ir susės dangaus karalystėje su Abraomu, Izaoku ir Jokūbu.
11እላችኋለሁም፥ ብዙዎች ከምሥራቅና ከምዕራብ ይመጣሉ ከአብርሃምና ከይስሐቅ ከያዕቆብም ጋር በመንግሥተ ሰማያት ይቀመጣሉ፤
12O karalystės vaikai bus išmesti laukan į tamsybes. Ten bus verksmas ir dantų griežimas”.
12የመንግሥት ልጆች ግን በውጭ ወደ አለው ጨለማ ይጣላሉ፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።
13Šimtininkui Jėzus tarė: “Eik, ir tebūnie tau, kaip tikėjai!” Ir tą pačią valandą tarnas pagijo.
13ኢየሱስም ለመቶ አለቃ። ሂድና እንዳመንህ ይሁንልህ አለው። ብላቴናውም በዚያች ሰዓት ተፈወሰ።
14Atėjęs į Petro namus, Jėzus pamatė jo uošvę gulinčią ir karščiuojančią.
14ኢየሱስም ወደ ጴጥሮስ ቤት ገብቶ አማቱን በንዳድ ታማ ተኝታ አያት፤
15Jis palietė jos ranką, ir karštis praėjo. Toji atsikėlė ir patarnavo jiems.
15እጅዋንም ዳሰሰ፥ ንዳዱም ለቀቃት፤ ተነሥታም አገለገለቻቸው።
16Vakarui atėjus, žmonės sugabeno pas Jėzų daug demonų apsėstųjų. Jis išvarė dvasias žodžiu ir išgydė visus ligonius,
16በመሸም ጊዜ አጋንንት ያደረባቸውን ብዙዎችን ወደ እርሱ አመጡ፤ በነቢዩ በኢሳይያስ። እርሱ ድካማችንን ተቀበለ ደዌያችንንም ተሸከመ የተባለው ይፈጸም ዘንድ፥ መናፍስትን በቃሉ አወጣ፥ የታመሙትንም ሁሉ ፈወሰ።
17kad išsipildytų, kas buvo pasakyta per pranašą Izaiją: “Jis pasiėmė mūsų negalias ir nešė mūsų ligas”.
18ኢየሱስም ብዙ ሰዎች ሲከቡት አይቶ ወደ ማዶ እንዲሻገሩ አዘዘ።
18Matydamas aplinkui didžiulę minią, Jėzus įsakė irtis į kitą krantą.
19አንድ ጻፊም ቀርቦ። መምህር ሆይ፥ ወደምትሄድበት ሁሉ እከተልሃለሁ አለው።
19Tuomet priėjo vienas Rašto žinovas ir tarė Jam: “Mokytojau, aš seksiu paskui Tave, kur tik Tu eisi!”
20ኢየሱስም። ለቀበሮዎች ጉድጓድ ለሰማይም ወፎች መሳፈሪያ አላቸው፥ ለሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት የለውም አለው።
20Jėzus jam atsakė: “Lapės turi urvus, padangių paukščiailizdus, o Žmogaus Sūnus neturi kur galvos priglausti”.
21ከደቀ መዛሙርቱም ሌላው። ጌታ ሆይ፥ አስቀድሜ እንድሄድ አባቴን እንድቀብር ፍቀድልኝ አለው።
21Kitas Jo mokinys prašė: “Viešpatie, leisk man pirmiau pareiti tėvo palaidoti”.
22ኢየሱስም። ተከተለኝ፥ ሙታናቸውንም እንዲቀብሩ ሙታንን ተዋቸው አለው።
22Bet Jėzus atsakė: “Sek paskui mane ir palik mirusiems laidoti savo numirėlius”.
23ወደ ታንኳም ሲገባ ደቀ መዛሙርቱ ተከተሉት።
23Jėzus įlipo į valtį, ir mokiniai paskui Jį.
24እነሆም፥ ማዕበሉ ታንኳይቱን እስኪደፍናት ድረስ በባሕር ታላቅ መናወጥ ሆነ፤ እርሱ ግን ተኝቶ ነበር።
24Ir štai ežere pakilo smarki audra, ir bangos liejo valtį. O Jis miegojo.
25ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው። ጌታ ሆይ፥ አድነን፥ ጠፋን እያሉ አስነሡት።
25Mokiniai pripuolę ėmė Jį žadinti, šaukdami: “Viešpatie, gelbėk mus, žūvame!”
26እርሱም። እናንተ እምነት የጎደላችሁ፥ ስለ ምን ትፈራላችሁ? አላቸው፤ ከዚህ በኋላ ተነሥቶ ነፋሱንና ባሕሩን ገሠጸ፥ ታላቅ ጸጥታም ሆነ።
26Jis jiems tarė: “Kodėl jūs tokie bailūs, mažatikiai?” Paskui Jis atsikėlė, sudraudė vėjus bei ežerą, ir pasidarė visiškai ramu.
27ሰዎቹም። ነፋሳትና ባሕርስ ስንኳ የሚታዘዙለት፥ ይህ እንዴት ያለ ሰው ነው? እያሉ ተደነቁ።
27Žmonės stebėjosi ir kalbėjo: “Kas Jis per vienas, kad net vėjai ir ežeras Jo klauso?”
28ወደ ማዶም ወደ ጌርጋሴኖን አገር በመጣ ጊዜ፥ አጋንንት ያደሩባቸው ሁለት ሰዎች ከመቃብር ወጥተው ተገናኙት፤ እነርሱም ሰው በዚያ መንገድ ማለፍ እስኪሳነው ድረስ እጅግ ክፉዎች ነበሩ።
28Kai Jėzus priplaukė kitą krantą gergeziečių krašte, Jam priešais atbėgo du demonų apsėstieji, išlindę iš kapinių rūsių. Juodu buvo tokie pavojingi, kad niekas negalėjo praeiti anuo keliu.
29እነሆም። ኢየሱስ ሆይ፥ የእግዚአብሔር ልጅ፥ ከአንተ ጋር ምን አለን? ጊዜው ሳይደርስ ልትሣቅየን ወደዚህ መጣህን? እያሉ ጮኹ።
29Ir štai jiedu ėmė šaukti: “Ko Tau iš mūsų reikia, Jėzau, Dievo Sūnau?! Atėjai pirma laiko mūsų kankinti?”
30ከእነርሱም ርቆ የብዙ እሪያ መንጋ ይሰማራ ነበር።
30Toli nuo jų ganėsi didelė banda kiaulių.
31አጋንንቱም። ታወጣንስ እንደሆንህ፥ ወደ እሪያው መንጋ ስደደን ብለው ለመኑት። ሂዱ አላቸው።
31Demonai prašė: “Jeigu mus išvarysi, tai leisk sueiti kiaulių bandon”.
32እነርሱም ወጥተው ወደ እሪያዎቹ ሄዱና ገቡ፤ እነሆም፥ የእሪያዎቹ መንጋ ሁሉ ከአፋፉ ወደ ባሕር እየተጣደፉ ሮጡ በውኃም ውስጥ ሞቱ።
32Ir Jis jiems tarė: “Eikite!” Tuomet demonai išėjo ir apniko kiaules. Ir štai visa banda metėsi nuo skardžio į ežerą ir prigėrė vandenyje.
33እረኞችም ሸሹ፥ ወደ ከተማይቱም ሄደው ነገሩን ሁሉ አጋንንትም በአደሩባቸው የሆነውን አወሩ።
33Piemenys pabėgo ir, pasiekę miestą, viską išpasakojo, taip pat ir apie apsėstuosius.
34እነሆም፥ ከተማው ሁሉ ኢየሱስን ሊገናኝ ወጣ፥ ባዩትም ጊዜ ከአገራቸው እንዲሄድላቸው ለመኑት።
34Tada visas miestas išėjo pasitikti Jėzaus ir, Jį pamatę, maldavo pasišalinti iš jų krašto.