Lithuanian

Amharic: New Testament

Matthew

9

1Įlipęs į valtį, Jėzus persikėlė per ežerą ir sugrįžo į savo miestą.
1በታንኳም ገብቶ ተሻገረና ወደ ገዛ ከተማው መጣ።
2Ir štai Jam atnešė paralyžiuotą žmogų, paguldytą ant gulto. Pamatęs jų tikėjimą, Jėzus tarė paralyžiuotajam: “Būk drąsus, sūnau, tavo nuodėmės atleistos!”
2እነሆም፥ በአልጋ የተኛ ሽባ ወደ እርሱ አመጡ። ኢየሱስም እምነታቸውን አይቶ ሽባውን። አንተ ልጅ፥ አይዞህ፥ ኃጢአትህ ተሰረየችልህ አለው።
3Kai kurie Rašto žinovai ėmė murmėti: “Jis piktžodžiauja!”
3እነሆም፥ ከጻፎቹ አንዳንዱ በልባቸው። ይህስ ይሳደባል አሉ።
4Žinodamas jų mintis, Jėzus tarė: “Kam piktai mąstote savo širdyje?
4ኢየሱስም አሳባቸውን አውቆ እንዲህ አለ። ስለ ምን በልባችሁ ክፉ ታስባላችሁ?
5Kas gi lengviau­ar pasakyti: ‘Tavo nuodėmės atleistos!’, ar liepti: ‘Kelkis ir vaikščiok!’?
5ኃጢአትህ ተሰረየችልህ ከማለት ወይስ። ተነሣና ሂድ ከማለት ማናቸው ይቀላል?
6Ir todėl, kad žinotumėte Žmogaus Sūnų turint galią žemėje atleisti nuodėmes,­čia Jis kreipėsi į paralyžiuotąjį:­Kelkis, pasiimk savo gultą ir eik namo!”
6ነገር ግን በምድር ላይ ኃጢአትን ያስተሰርይ ዘንድ ለሰው ልጅ ሥልጣን እንዳለው እንድታውቁ፥ በዚያን ጊዜ ሽባውን። ተነሣ፤ አልጋህን ተሸከምና ወደ ቤትህ ሂድ አለው።
7Šis atsikėlė ir nuėjo į savo namus.
7ተነሥቶም ወደ ቤቱ ሄደ።
8Visa tai pamačiusios, minios stebėjosi ir šlovino Dievą, suteikusį tokią galią žmonėms.
8ሕዝቡም አይተው ተደነቁ፥ ለሰውም እንዲህ ያለ ሥልጣን የሰጠ እግዚአብሔርን አከበሩ።
9Iškeliaudamas iš ten, Jėzus pamatė muitinėje sėdintį žmogų, vardu Matą, ir tarė jam: “Sek paskui mane!” Šis atsikėlė ir nusekė paskui Jį.
9ኢየሱስም ከዚያ አልፎ በመቅረጫው ተቀምጦ የነበረ ማቴዎስ የሚባል አንድ ሰው አየና። ተከተለኝ አለው። ተነሥቶም ተከተለው።
10Kai Jėzus sėdėjo namuose prie stalo, ten susirinko daug muitininkų bei nusidėjėlių, kurie susėdo šalia Jo ir Jo mokinių.
10በቤቱም በማዕድ ተቀምጦ ሳለ፥ እነሆ፥ ብዙ ቀራጮችና ኃጢአተኞች መጥተው ከኢየሱስና ከደቀ መዛሙርቱ ጋር አብረው ተቀመጡ።
11Fariziejai, tai išvydę, sakė Jo mokiniams: “Kodėl jūsų Mokytojas valgo su muitininkais ir nusidėjėliais?”
11ፈሪሳውያንም አይተው ደቀ መዛሙርቱን። መምህራችሁ ከቀራጮችና ከኃጢአተኞች ጋር አብሮ ስለ ምን ይበላል? አሉአቸው።
12Tai išgirdęs, Jėzus atsiliepė: “Ne sveikiesiems reikia gydytojo, o ligoniams.
12ኢየሱስም ሰምቶ። ሕመምተኞች እንጂ ባለ ጤናዎች ባለ መድኃኒት አያስፈልጋቸውም፤
13Eikite ir pasimokykite, ką reiškia žodžiai: ‘Aš noriu gailestingumo, o ne aukos’. Aš atėjau šaukti ne teisiųjų, bet nusidėjėlių atgailai”.
13ነገር ግን ሄዳችሁ። ምሕረትን እወዳለሁ መሥዋዕትንም አይደለም ያለው ምን እንደ ሆነ ተማሩ፤ ኃጢአተኞችን ወደ ንስሐ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁምና አላቸው።
14Tada priėjo Jono mokiniai ir paklausė: “Kodėl mes ir fariziejai daug pasninkaujame, o Tavo mokiniai nepasninkauja?”
14በዚያን ጊዜ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ ቀርበው። እኛና ፈሪሳውያን፥ ብዙ ጊዜ የምንጦመው፥ ደቀ መዛሙርትህ ግን የማይጦሙት ስለ ምንድር ነው? አሉት።
15Jėzus jiems atsakė: “Argi gali vestuvininkai gedėti, kol su jais yra jaunikis? Bet ateis dienos, kai jaunikis iš jų bus atimtas, ir tada jie pasninkaus.
15ኢየሱስም እንዲህ አላቸው። ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉን? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል፥ በዚያ ጊዜም ይጦማሉ።
16Niekas sudėvėto drabužio nelopo naujo audinio lopu, nes toks lopinys atplėšia drabužio gabalą, ir pasidaro dar didesnė skylė.
16በአረጀ ልብስ አዲስ እራፊ የሚያኖር የለም፤ መጣፊያው ልብሱን ይቦጭቀዋልና፥ መቀደዱም የባሰ ይሆናል።
17Taip pat niekas nepila jauno vyno į senus vynmaišius, nes antraip vynmaišiai plyštų, vynas išsilietų ir vynmaišiai niekais nueitų. Bet jaunas vynas pilamas į naujus vynmaišius, ir abeji išsilaiko”.
17በአረጀ አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን፥ አቁማዳው ይፈነዳል፥ የወይን ጠጁም ይፈሳል አቁማዳውም ይጠፋል፤ ነገር ግን አዲሱን የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ያኖረዋል፥ ሁለቱም ይጠባበቃሉ።
18Jam taip bekalbant, prisiartino vienas vyresnysis, pagarbino Jį ir tarė: “Ką tik mirė mano dukrelė. Bet ateik, uždėk ant jos ranką, ir ji atgis”.
18ይህንም ሲነግራቸው፥ አንድ መኰንን መጥቶ። ልጄ አሁን ሞተች፤ ነገር ግን መጥተህ እጅህን ጫንባት፥ በሕይወትም ትኖራለች እያለ ሰገደለት።
19Jėzus atsikėlė ir nuėjo paskui jį kartu su savo mokiniais.
19ኢየሱስም ተነሥቶ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ተከተለው።
20Ir štai moteris, dvylika metų serganti kraujoplūdžiu, prisiartino iš paskos ir palietė Jo apsiausto apvadą.
20እነሆም፥ ከአሥራ ሁለት ዓመት ጀምሮ ደም የሚፈስሳት ሴት በኋላው ቀርባ የልብሱን ጫፍ ዳሰሰች፤
21Mat ji pati sau kalbėjo: “Jei tik palytėsiu Jo drabužį­išgysiu”.
21በልብዋ። ልብሱን ብቻ የዳሰስሁ እንደ ሆነ፥ እድናለሁ ትል ነበረችና።
22Jėzus, atsigręžęs ir ją pamatęs, tarė: “Pasitikėk, dukra, tavo tikėjimas išgydė tave”. Ir tą pačią akimirką moteris pagijo.
22ኢየሱስም ዘወር ብሎ አያትና። ልጄ ሆይ፥ አይዞሽ፤ እምነትሽ አድኖሻል አላት። ሴቲቱም ከዚያች ሰዓት ጀምራ ዳነች።
23Atėjęs į vyresniojo namus ir pamatęs vamzdininkus bei šurmuliuojančią minią,
23ኢየሱስም ወደ መኰንኑ ቤት በደረሰ ጊዜ፥ እምቢልተኞችንና የሚንጫጫውን ሕዝብ አይቶ።
24Jėzus paliepė: “Pasitraukite, nes mergaitė ne mirus, o miega”. Jie tik šaipėsi iš Jo.
24ብላቴናይቱ ተኝታለች እንጂ አልሞተችምና ፈቀቅ በሉ አላቸው። በጣምም ሳቁበት።
25Kai minia buvo išvaryta, Jis įėjo vidun, paėmė mergaitę už rankos, ir ji atsikėlė.
25ሕዝቡን ግን ከአስወጡ በኋላ ገብቶ እጅዋን ያዛት፥ ብላቴናይቱም ተነሣች።
26Garsas apie tai pasklido po visą aną kraštą.
26ያም ዝና ወደዚያ አገር ሁሉ ወጣ።
27Jėzui išeinant, du neregiai sekė paskui Jį ir šaukė: “Pasigailėk mūsų, Dovydo Sūnau!”
27ኢየሱስም ከዚያ ሲያልፍ ሁለት ዕውሮች። የዳዊት ልጅ ሆይ፥ ማረን ብለው እየጮሁ ተከተሉት።
28Kai Jis pasiekė namus, neregiai užėjo pas Jį. Jėzus paklausė: “Ar tikite, kad Aš galiu tai padaryti?” Šie atsakė: “Taip, Viešpatie!”
28ወደ ቤትም በገባ ጊዜ ዕውሮቹ ወደ እርሱ ቀረቡ፥ ኢየሱስም። ይህን ማድረግ እንድችል ታምናላችሁን? አላቸው። አዎን፥ ጌታ ሆይ አሉት።
29Tada Jis palietė jų akis ir tarė: “Tebūna jums pagal jūsų tikėjimą”.
29በዚያን ጊዜ። እንደ እምነታችሁ ይሁንላችሁ ብሎ ዓይኖቻቸውን ዳሰሰ።
30Ir jų akys atsivėrė. Jėzus griežtai jiems įsakė: “Žiūrėkite, kad niekas nesužinotų!”
30ዓይኖቻቸውም ተከፈቱ።
31Tačiau tie išėję išgarsino Jį po visą tą kraštą.
31ኢየሱስም። ማንም እንዳያውቅ ተጠንቀቁ ብሎ በብርቱ አዘዛቸው። እነርሱ ግን ወጥተው በዚያ አገር ሁሉ ስለ እርሱ አወሩ።
32Jiems išėjus, štai atvedė pas Jį demono apsėstą nebylį.
32እነርሱም ሲወጡ እነሆ፥ ጋኔን ያደረበትን ዲዳ ሰው ወደ እርሱ አመጡ።
33Išvarius demoną, nebylys prakalbo. Minios stebėjosi ir sakė: “Dar niekad Izraelyje nebuvo tokių dalykų”.
33ጋኔኑንም ካወጣው በኋላ ዲዳው ተናገረ። ሕዝቡም። እንዲህ ያለ በእስራኤል ዘንድ ከቶ አልታየም እያሉ ተደነቁ።
34O fariziejai kalbėjo: “Jis išvaro demonus jų valdovo jėga”.
34ፈሪሳውያን ግን። በአጋንንት አለቃ አጋንንትን ያወጣል አሉ።
35Jėzus ėjo per visus miestus ir kaimus, mokydamas jų sinagogose, skelbdamas karalystės Evangeliją ir gydydamas visas žmonių ligas bei negalias.
35ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ፥ የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ፥ በሕዝብም ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ፥ በከተማዎችና በመንደሮች ሁሉ ይዞር ነበር።
36Matydamas minias, Jis gailėjosi žmonių, nes jie buvo suvargę ir išsklaidyti lyg avys be piemens.
36ብዙ ሕዝብም ባየ ጊዜ፥ እረኛ እንደ ሌላቸው በጎች ተጨንቀው ተጥለውም ነበርና አዘነላቸው።
37Tuomet Jis tarė savo mokiniams: “Pjūtis didelė, o darbininkų maža.
37በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን። መከሩስ ብዙ ነው፥ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው፤
38Todėl melskite pjūties Viešpatį, kad siųstų darbininkų į savo pjūtį”.
38እንግዲህ የመከሩን ጌታ ወደ መከሩ ሠራተኞች እንዲልክ ለምኑት አላቸው።